( ኢዜአ ) ዓለም አቀፉ የአረንጓዴ ልማት ኢንስቲትዩት የኢትዮጵያ ቢሮ ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በደን ልማትና በአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ላይ ያተኮሩ ተግባራትን በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ። ስምምነቱን ዛሬ በሀዋሳው የኃይሌ ሪዞርት የተፈራረሙት የቢሮው ኃላፊ ዶክተር ገመዶ ዳሌ እና የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር አያኖ በራሶ ናቸው። በስምምነቱ ወቅት ዶክተር ገመዶ ዳሌ በተለይ ለኢዜአ እንዳሉት፤ ዓለም አቀፉ የአረንጓዴ ልማት ኢንስቲትዩት ላለፉት 10 ዓመታት የኢትዮጵያን መንግሥት በተለያየ ደረጃ ሲደግፍ ቆይቷል። ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ስትራቴጂ ከመቅረጽ ጀምሮ የቴክኒክ፣ የፋይናንስ እና የአቅም ግንባታ ድጋፍ በመስጠት ከፍተኛ ሚና መጫወቱን አስታውሰዋል። አሁንም ከኮሪያ መንግሥት በተገኘ የ 9 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዶላር የፋይናንስ ድጋፍ የ 5 ዓመት ፕሮጀክት ተቀርፆ በዚህ ዓመት ወደ ትግበራ መገባቱን አመላክተዋል። ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር የተደረገው ይህ ስምምነትም የፕሮጀክቱ አካል መሆኑን ጠቁመው፤ በአብዛኛው ፕሮጀክቱ በሲዳማና ኦሮሚያ ክልሎች አዋሳኝ በሆኑ ወረዳዎች የሚተገበር መሆኑን አስታውቀዋል። በአለታ ወንዶ፣ ሻሸመኔ እና አርቤጎና ወረዳዎች ውስጥ በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ አደጋ የተጎዳ 13 ሺህ ሄክታር መሬት እንዲያገግምና ወደ ምርታማነት እንዲመለስ የሚሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል። እንዲሁም ያለውን የደን ሀብት መጠበቅና መንከባከብ፣ የህብረተሰቡን የኢኮኖሚና የገቢ ምንጭ አማራጮችን ለ
It's about Sidaama!