Skip to main content

Posts

የህዳሴ ግድብ እስኪጠናቀቅ ድረስ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ገለፁ

በሐዋሳ የኮቪድ 19ኝ ወረርሽኝን ለመከላከል ተገቢውን ጥንቃቄ በማያደርጉ ግለሰቦች፣ ተቋማትና አገልግሎት ሰጪዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ የመውሰዱ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለፀ

በሐዋሳ የኮቪድ 19ኝ ወረርሽኝን ለመከላከል ተገቢውን ጥንቃቄ በማያደርጉ ግለሰቦች፣ ተቋማትና አገልግሎት ሰጪዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ የመውሰዱ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለፀ። ወረርሽኙን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ተገቢውን ጥንቃቄ በማያደርጉ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ የመውሰዱ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙንጠሻ ብርሀኑ እና ኮማንደር ደረሰ ቡሳሮ የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ገልፀዋል። በከተማ ደረጃ የኮቪድ 19ኝ ወረርሽኝ ስርጭት አሳሳቢ ደረጃ መድረሱን የገለፁት የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙንጣሻ ብርሀኑ በተለያየ ጊዜ የተሰራው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ ብቻውን የሚፈለገውን ውጤት አለማምጣቱን ገልፀዋል። በከተማ ደረጃ የበሽታውን ስርጭት ለመከላከል በሚደረገው ጥረት የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ ቢሆንም በህብረተሰቡ ዘንድ የሚስተዋለው መዘናጋት ትልቅ ዋጋ እያስከፈለ መሆኑንም ኃላፊዎቹ ጠቁመዋል። በዚህም ከጊዜ ወደ ጊዜ የቫይረሱ የስርጭትና በበሽታው ምክንያት ህይወታቸው የሚያልፍ ሰዎች ቁጥርም እየጨመረ መምጣቱን አቶ ሙንጠሻ አመላክተዋል። ከዚህ ባለፈም ባለፉት ተከታታይ 5 ቀናት የተደረገ ምርመራ ከተመረመሩት 100 ሰዎች በአማካይ 59 ሰዎች ቫይረሱ እንዳለባቸው የሚያሳይ መሆኑንም የጤና መምሪያው ኃላፊ ገልፀዋል። የሐዋዳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ደረሰ ቡሳሮ በበኩላቸው ግንዛቤ ከማስጨበጥ ባለፈ ህጋዊ እርምጃ በመውሰድ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግና የቫይረሱን ስርጭት መከላከል እንዲችል የወጡ መመሪያዎችን ተግባራዊ በማያደርጉ ግለሰቦች,ተቋማትና ሌሎች አገልግሎት ሰጪዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን ጠቁመዋል። የመንግስትና የግል ተቋማት፣ሆቴሎችና መዝናኛ ስፍራዎች፣

የሲዳማ ብሔራዊ ክልል በ9 ወራት ውስጥ ከመደበኛ ገቢ ወደ 80% እንዲሁም ከማዘጋጃዊ ገቢ ወደ 68% የሚጠጋ ገቢ መሰብሰቡ ተገለጸ

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገቢዎች ባለስልጣን (ቢሮ) የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በባለስልጣኑ 9 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ውይይት ተደርጓል። የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገቢዎች ባለስልጣን (ቢሮ) የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በባለስልጣኑ 9 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ውይይት ተደርጓል። በአፈፃፀም ግምገማ ላይ በመገኘት መድረኩን በይፋ የከፈቱት የዕለቱ የክብር እንግዳ የሲዳማ ክልል ብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ አሸናፊ ኤልያስ እንደተናገሩት በኮቪድ ፕሮቶኮል ምክንያት ሁሉንም ባለድርሻ አካላትን ማሳተፍ አለመቻሉን በማንሳት በተወሰኑ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት መድረኩ ለማካሄድ ግድ መሆኑን በማንሳት የ9 ወራት አፈፃፀም እንደ ክልል ምን ደረጃ ላይ እንዳለ ለመገምገም የተዘጋጀ መድረክ መሆኑን አንስተዋል። አክለውም የገቢ ማሰባሰብ ሥራችን እንደ ክልል ለምንሰራቸው የልማትም ሆነ ለሌሎች ስራዎች የጀርባ አጥንት መሆኑን አንስተው አሁን በክልል ደረጃ ያለንበትን ነባራዊ ሁኔታ ተመልክተን ለቀጣይ ቀሪ ወራቶች በተጠናከረ አግባብ የምንሄድበትን ዕድል የሚፈጥር መድረክ ነው ብለዋል። የክልሉ ገቢዎች ባለስልጣን ቢሮ ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ሙሉወርቅ ደረሰ ያለፋትን የዘጠኝ ወራት የገቢ አፈፃፀም ሪፓርት ባቀርቡበት ወቅት እንዳሉት ከመደበኛ ገቢ ወደ 80% እንዲሁም ከማዘጋጃዊ ገቢ ወደ 68% የሚጠጋ ገቢ መሰብሰብ እንደተቻለ አንስተዋል።  አክለውም እስካሁን ያለው የገቢ አፈፃፀም የሚበረታታ እንደሆነ ያነሱ ቢሆንም ቀጣይ የገቢ አሰባሰብ ዘዴያችንን በማዘመን ከዚህም በላይ የሆነ ገቢ መሰብሰብ እንዳለበት አንስተዋል። በአፈፃፀም ግምገማ መድረኩም ላይ የሁሉም ወረዳ እና ከተማ አስተዳደር አስተዳዳሪዎች፣የገቢዎች ጽ/ቤት ኃላፊዎ

የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮ ህብረተሰቡ ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ እንዲያገኝ የራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የማቋቋም አላማ እንዳለው ገለጸ

የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮ ህብረተሰቡ ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ እንዲያገኝ የራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የማቋቋም አላማ እንዳለው ገለጸ።  የሲዳማ ክልል የመንግስት የኮሙኒኬሽን ቢሮ ዛሬ በሀይሌ ሪዞርት የዘጠኝ ወር እቅድ አፈጻጸም ግምገማና የሚዲያ ፎረም ማቋቋሚያ መድረክ አካሂዷል።  የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ አቶ ፊሊጶስ ናሆም ሴክተሩ ከቢሮ ጀምሮ እስከታችኛው መዋቅር ድረስ ዘርፉ የተመራበን አግባብ የተሻለ የሚባል ነው ሲሉ ገልጸዋል። አቶ ፊሊጶስ አክለውም ክልሉ አዲስ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በሰው ሀይል፣ በክህሎት ውስንነትና በቁሳቁስ እጥረት የሚፈለገውን ያክል እንዳልተሰራም ተናግረዋል።  ክልሉ ያለበትን የሚዲያ ደረጃ በመገምገም የሚዲያ ፎረም የሚቋቋም መሆኑን የገለጹት አቶ ፊሊጶስ በቀጣይ በክልሉ ተአማኒነት ያለው መንግስትንና ህዝብን የሚያቀራርብ፣ ለሀሰተኛ መረጃዎች አጸፋ የሚሰጥ የተጠናከረ የሚዲያ ተቋም የማቋቋም ዓላማ መኖሩን ገልጸዋል።  የሐ/ከ/መ/ኮ/ጉ/መምሪያ

33ነጥብ 8 ሚሊዮን ህዝብ በምስራቅ አፍሪካ አገራት የምግብ ዋስትና ችግር ውስጥ ያለ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ ውስጥ የምግብ ዋስትና ስጋት ካለባቸው ክልሎች አንዱ የሲዳማ ክልል ነው።

 

የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የባለሀብቶች ማህበር የ3 መቶ ሺህ ብር ግምት ያላቸው የአፍንጫና የአፍ መሸፈኛ ....

የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የባለሀብቶች ማህበር የ3 መቶ ሺህ ብር ግምት ያላቸው የአፍንጫና የአፍ መሸፈኛ ማስክ ለሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ ድጋፍ አደረገ።

የሲዳማ ክልል መንግስት የኮሮና ወረርሽንን በተመለከተ በመከተል ላይ ያለው የላላ ቁጥጥር ዋጋ ማስከፈሉ የማይቀር ነው

የሲዳማ ክልል መንግስት በኮሮና ወረርሽን ቁጥጥር ላይ ያለው የላላ አቋም፤ የክልሉን ነዋሪዎች የህይወት መስዋእትነት ከማብዛቱ በላይ፤ አሁኑ ካለው የቫይረሱ ስርጭት አንጻር የእያንዳንዱን ነዋሪ ቤት ማንኳኳቱ የማይቀር ነው። በአገሪቱ ደረጃ በበሽታው ስርጭት አንደኛ የሆነ ክልል እንዴት ብለው ነው፤ ይህን መሰል የሰዎች ስብስብ የምታገሱት??

ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች እና ኮሌጆች ተምሮ ተመርቀው ሥራ ላጡ ዜጎች በ50 ማህበር ተቀናጅተው በገጠር መንገድ ሥራ ላይ እንዲሰማሩ ማድረግ መቻሉን የሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ሥራ እድል ፈጠራ፣ እንዱስትሪ ልማትና ኢንተርፕራይዝ ቢሮ ገለፀ።

  የቢሮው ኃላፊ አቶ ሠላሙ ቡላዶ ለተመረጡ ማህበራት የሥራ ገለጻ በሰጡበት ወቅት የክልሉ መንግስት ከተለያዩ ከፍተኛ ትምህርት ተቋሚ ትምህርታቸውን ተከታትለው የተመረቁ ዜጎች የሥራ እድል ለመፍጠር ከተለያዩ ተቋማት ጋር ተቀናጅተው በመስራት ላይ እንደሚገኝ ጠቁመው የሥራ እድል ሲፈጠር ህጉን በጠበቀና ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ብቻ እንደሚሆን ተናግረዋል። ማህበራቱን ማቀናጀት ሲጀምሩ 92 ማህበራት ልየታ የተደረገ ሲሆን ከነዚህ መካከል የተለያዩ ችግሮች ያለባቸውን በመረጃ ተደግፈው 20 ማህበራትን የለዩ ሲሆን የተቀሩት 72 ማህበራት ሥራ ለመፍጠር እቅድ መያዙን አውስተው የነዚህ ማህበራት አባላት በኢንጂነሪንግ ፣ በኮንስትራክሽን እና በኢኮኖሚክስ ትምህርት መስኮች የተመረቁ እንደሆነም አስረድተዋል። አቶ ሰላሙ በተጨማሪ ሥራ እያላቸው በማህበራት ውስጥ በመቀናጀት ሌላ ጥቅም ለማግኘት በሞከሩ ግለሰቦችና በግብራበሮቻቸው ላይ ህጋዊ ኢርምጃ የሚወሰድ መሆኑን ጠቅሰው በመሠል ተግባር ላይ የሚሠማሩ ዜጎችን ሁሉም ህብረተሰብ ክፍል በመንግስት ጎን በመሆን መታገል እንደሚገባ ተናግረዋል። በሥራ እድል ፈጠራ፣ እንዱስትሪ ልማትና ኢንተርፕራይዝ ቢሮ ምክትልና የገጠር ሥራ እድል ፈጠራ ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ ከፍያለው ከበደ ከተለዩ ማህበራት መካከል 50 ለሚሆኑ ማህበራት በገጠር መንገድ ዘርፍ ተሰማርተው የሥራ እድል እንዲያገኙ የተደረገ ሲሆን ተለይተው የቀሩት በመንግስት ሥራ ላይ ተሠማርተው የነበሩ፤ ከዚህ በፊት በኮንስትራክሽን ፍቃድ የነበራቸው እና እየሠሩ ተጠቃሚ የሆኑ እንዲሁም በተለያዩ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የጽ/ቤት ኃላፊ የነበሩ በማህበር የተቀላቀሉ መገኘታቸውን ተናግረዋል። እነዚህም ከ17 ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች በማጣራት ሂደት የተለዩ 59 የሚሆኑ ግለሰቦች ከዚህ በፊት

የፖለቲካ ፓርቲዎች በቀጣይ ሀገራዊ ምርጫ ስነ-ምግባርን አክብረው በኃላፊነት ሊንቀሳቀሱ እንደሚገባ ተገለፀ

የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪሜየሊግ የመጨረሻውን ዙር ውድድር ለማስተናገድ ሀዋሳ እራሷን እያዘጋጀች ነው ዘጋቢ ፡ ነጻ...

Popular posts from this blog

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

የለበሰው ያደፈ ቁምጣና ሹራብ ከቅዝቃዜው አላዳነውም፡፡ ካፊያው ልብሱን አርሶታል፡፡ ሽው እያለ ከሐይቁ የሚነሳው ነፋስ የሚፈጥረው ቅዝቃዜ ያንቀጠቅጠዋል፡፡ የተጫማው ያረጀ ሲሊፐር እግሩን ከምንም አላዳነውም፡፡ በባዶ እግሩ የሚራመድ ያህል ጨቅይቷል፡፡ ተደባዳቢ ይመስል ፊቱ የተሞነጫጨረ ነው፡፡ ገና 12 ዓመቱ ቢሆንም፣ ቁመናው እንደ ትልቅ ሰው ግዙፍ ነው፡፡ የሚለብሰውን እንደ ልቡ ባያገኝም፣ የሚያስፈልገውን ነገር ለማሟላት ቤሳቢስቲን የሌላቸው ወላጆቹን አያስቸግርም፡፡ ከቤተሰቦቹ ጋር ከሚኖሩበት ታቦር ተራራ ጀርባ ወዳለው ሐዋሳ ሐይቅ ከወረደ እንኳንስ የራሱን የቤተሰቦቹንም የዕለት ጉርስ የሚሸፍንበት ገንዘብ አያጣም፡፡ የአስጎብኚነት ዕውቀት፣ ከሐይቁም ውስጥ ዓሳ የሚያጠምድበት መረብም ሆነ ፈቃድ የለውም፡፡ ሙሉቀን (ስሙ ተቀይሯል) እና ጓደኞቹ ሐይቁን ለመጎብኘት የሚሄዱ ጎብኚዎች በካሜራቸው ጥሩ ፎቶ እንዲያስቀሩ ድባቡን የማሳመር ሥራ ይሠራሉ፡፡ ካሜራውን ይዞ ቁጭ ብድግ እያለ ጥሩ ፎቶ ለማንሳት ጥረት የሚያደርግ ሲያዩ፣ ቆርጠው የያዙትን የዓሳ ሥጋ ይዘው ጠጋ ጠጋ ይላሉ፡፡ ቁርጥራጩን የዓሳ ሥጋ ምግብ ለሚቀሙት አባኮዳዎች ሻሞ ይላሉ፡፡ የተወረወረላቸውን ቀድመው ለመቅለብ አባኮዳዎቹ ክንፋቸውን እየመቱ ወደ ላይ ብድግ ይላሉ፡፡ የናሽናል ጆግሪፊ የፎቶግራፍ ባለሙያዎች ያነሱት ዓይነት ፎቶዎች ሳያስቡት ያነሳሉ፡፡ በሁኔታው ተደስተው ደጋግመው ድንቅ ፎቶዎችን ለመውሰድ ሲዘጋጁ እነ ሙሉቀንም አጀንዳቸውን ይፋ ማድረግ ይጀምራሉ፡፡ አቶ ዳዊት አብርሃም ‹‹አንዱን ዓሳ በአሥር ብር ገዝቼ ነው እንዲህ የማዘጋጀው፤›› በማለት በቅድሚያ  መረጃ ይሰጣሉ፡፡ ለቀጣዩ ዜና በዚህ መልኩ እንዲዘጋጁ ካደረጉ በኋላ፣ ሌሎች ሰዎች መቶም ሁለት መቶም ብር እንደሚሰጧቸው ቀለል

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የመንግሥት ስልጠና የምርጫ ቅስቀሳ አካል ነው ብሏል  የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ለምን ወጣ መባሉ ተገቢ አይደለም - ምርጫ ቦርድ ምርጫ ቦርድ ከኢህአዴግ ተፅዕኖ ሙሉ ለሙሉ ነፃ መሆኑ ሳይረጋገጥና የምርጫ አፈፃፀም ችግሮች ሳይወገዱ የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ለማወጅ መዘጋጀቱ ተገቢ አይደለም ሲል ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ የሚመሩት ኢማዴ-ደህአፓ ተቃወመ፡፡ መንግስት፤ የዩኒቨርሲቲ መምህራንና ተማሪዎችን ጨምሮ ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየሰጠ ያለው ስልጠና የምርጫ ቅስቀሳ አካል ነው ሲልም ፓርቲው ኮንኗል፡፡  የኢትዮጵያ ማህበረ ዴሞክራሲ ደቡብ ህዝቦች አንድነት ፓርቲ ሰሞኑን ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ባስገባው ግልፅ ደብዳቤ፤ ያለፉት አገር አቀፍና የአካባቢ ምርጫዎች ከመካሄዳቸው በፊት በምርጫ ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው ዙሪያ ኢህአዴግ ከተቃዋሚዎች ጋር የሚወያይበት መድረክ እንዲዘጋጅ በተደጋጋሚ ብንጠይቅም እስካሁን ከቦርዱ የተሰጠ ተግባራዊ ምላሽ የለም ብሏል፡፡  ሃገሪቱ “በአንድ አውራ ፓርቲ” ብቸኛ ቁጥጥር ስር መውደቋ አደገኛና አሳሳቢ ነው ያለው ፓርቲው፤ የመድብለ ፓርቲ ስርአት የመገንባት ተስፋችን ጨርሶ እንዳይከስም ቦርዱ ሃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት አሳስቧል፡፡ ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ የሚካሄድበትን ሁኔታ ለመፍጠር ገዥው ፓርቲና ሃቀኛ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚወያዩበት መድረክ እንዲያመቻች በህግ ስልጣን የተሰጠው ምርጫ ቦርድ የገባውን ቃል በማጠፍ መድረኩን ሳያመቻች የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማዘጋጀቱ ፋይዳ የለውም ብሏል - ፓርቲው፡፡  ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ በተሻሻለው የምርጫ ህግ፣ ለቦርዱ የተሰጠውን የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ መድረክ የማስተባበር ስልጣን ለመቀማት ታማኝ ፓርቲዎችን በተቃዋሚ ስም አሰባስቦ “የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ መድረክ” በመፍጠር የምርጫ ውድድር አሯሯጭ አሰልፏል ሲ

የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል ማለፊያ ነጥብ ውጤት ነገ ይፋ ይሆናል

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 23 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) የ10ኛ ክፍል ማጠቃለያና የ12ኛ ክፍል መሰናዶ ማለፊያ ነጥብ ውጤትን ነገ ይፋ እንደሚያደርግ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። የዩኒቨርስቲ መግቢያና ወደ መሰናዶ ማለፊያ ነጥብን ለመወሰን  ፥ የዩኒቨርስቲዎችን ቀጣይ የመቀበል አቅም ከግምት ውስጥ በማስገባት መወሰኑንም ነው ሚኒስቴሩ የገለጸው። በአጠቃላይ 548 ሺህ 138 ተማሪዎች የ10 ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተናውን ወስደው 70 በመቶዎቹ 2 ነጥብ እና ካዛ በላይ ውጤት ሲያስመዘግቡ ፥ በተመሳሳይም የ12ኛ ክፍልን የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተናን ከወሰዱት መካከል 70 በመቶ የሚሆኑት ተፈታኞች ከ350 ነጥብ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውን ቀደም ሲል  የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና የፈተናዎች ኤጀንሲ አስታውሷል ። በነገው እለትም የሁለቱም ፈተናዎች የመቁረጫ ውጤት ይፋ ይደረጋል ተብሏል።