Skip to main content

Posts

በሲዳማ ክልል ከ156 ሺህ ለሚበልጡ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ይሰራል

ሀዋሳ  ጥቅምት 1/2013 (ኢዜአ) በሲዳማ ክልል ከ156 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል ለመፍጠር  እንደሚሰራ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ደስታ ሌዳሞ ገለፁ።  አቶ ደስታ ይህን የገለፁት እየተካሄደ ባለው የክልሉ ምክር ቤት 5ኛ ዙር 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ባቀረቡት ዋና ዋና የ2013 በጀት ዓመት የሥራ ዕቅድ ነው ። እንደ ርዕሰ መስተዳደሩ ገለፃ ሲዳማ ክልል ሆኖ ከተቋቋመ በኋላ የአደረጃጀት መዋቅሩን በሰው ኃይል የማጠናከር ሥራ እንዲሁም የክልሉን ፀጥታና ሠላም አስጠብቆ የማስቀጠል ሰፊ ተግባር ሲከናወን ቆይቷል። የኮሮና ወረርሽኝ የከፋ ተጽዕኖ ሳያሳድር የክልሉን የልማትና ሌሎች ሥራዎች ለማስቀጠልም ሰፊ ርብርብ መደረጉንም ተናግረዋል። በቀጣይ እንቅስቃሴ ዙሪያ ከየአካባቢው ህዝብ ጋር ሲደረግ የቆየው ውይይትም ውጤታማ እንደነበርና በ2013 በትኩረት ከሚከናወኑ ዋና ዋና ሥራዎች መካከል የሥራ ዕድል ፈጠራ አንዱ መሆኑንም ጠቁመዋል። በክልሉ በርካታ ሥራ አጥ ወጣቶች መኖራቸውን የጠቆሙት አቶ ደስታ ይሁን እንጂ እነዚህ ወጣቶች ሰርተው የሚለወጡበት በቂ ኢንቨስትመንት ማስፋፋትና በቂ ሀብት ማፍራት ባለመቻሉ ላለው የሰው ኃይል ሥራ መፍጠር እንዳልተቻለ አስረድተዋል፡፡ ይህን ችግር ደረጃ በደረጃ ለመፍታት የክልሉን ሠላም በማስጠበቅ ኢንቨስተሮችን በስፋት መሳብና የሥራ ዕድልን ማስፋፋት በበጀት ዓመቱ ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ መሆኑን አስታውቀዋል። በተያዘው በጀት ዓመት ለ103 ሺህ 920 ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል እንዲሁም ለ52 ሺህ 149 ዜጎች ጊዜዊ የሥራ ዕድል ለመፍጠር እንደሚሰራና ዋናው ትኩረት ለሴቶችና ወጣቶች መሆኑን ባቀረቡት ዕቅድ ጠቁመዋል። ለዚህ የስራ ዕድል ፈጠራ ከቁጠባ፣ ከዕዳ ማስመለስ እንዲሁም ከመንግስት ድጋፍ ከ7

ምክንያታዊ የሆኑ ሥጋቶችና የደቡብ ኢትዮጵያ እንቆቅልሽ

  በደስታ ሄሊሶ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ እንደ አገረ መንግሥት በጥልቅ ችግር ውስጥ ነች የሚለው አገላለጽ ያለችበትን ሁኔታ አሳንሶ ቢገልጸው ነው። በቅርቡ አንድ ሰው ኢትዮጵያን ‹‹ዝግ ባለ ፍጥነት በመከስከስ ላይ ያለ አውሮፕላን›› በማለት ገልጿታል። የትግራይ ክልላዊ አስተዳደር ከፌዴራል መንግሥት ጋር ኃይል ለመፈታተሽ እየተዘጋጀ በሚመስልበት፣ የኦሮሚያ ክልል በቀውስና ግራ አጋቢ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ እያለፈ፣ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ተደጋጋሚ የሆኑ ብሔር ተኮር ውጥረቶች እየተስተዋሉ ባሉበትና ከሃጫሉ ግድያ በኋላ መንግሥት የወሰዳቸው ዕርምጃዎች አገሪቱን የበለጠ በከፋፈሏት በዚህ ጊዜ የሰውየው አባባል የተጋነነ ሊሆን አይችልም። በእነዚህ ሁሉ ክስተቶች መካከል ‹‹እናት አገር [ኢትዮጵያ]›› የሚለውን የዶ/ር ዓብይን ግጥምና ለኢትዮጵያ ያላቸውን ህልም በትዊተር ሰሌዳቸው ላይ አንብቤ ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደሚስማሙበት “እናት አገር” የሚለው ምሥል ‹‹የኢትዮጵያ ሕዝቦችን›› የሚያመላክት ነው፣ ይህም የአንድ ቤተሰብ አካልነትን ወይም ልጅነትን የሚጠቁም ነው። ሆኖም በዚህ ዘመን በዚህ የአካልነት ወይም ልጅነት ጉዳይ ላይ ሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝቦች ጥሩ ስሜት እንደሚሰማቸው እርግጠኛ መሆን አይቻልም። እንዲያውም በደቡብ ያሉ ብዙዎች ይህች “እናት አገር” የሥጋ እናታችን ወይስ የእንጀራ እናታችን ናት? ብለው ሊጠይቁ ይችላሉ።  ይህ ጥያቄ በዚህ ጊዜ በተለየ ሁኔታ ለወላይታ ሕዝቦች ፋይዳ ያለው ጥያቄ ነው። በመለስ ዜናዊ የአስተዳደር ዘመን በብሔረሰቦች መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት ምክንያት ብዙ ወላይታዎች በሐዋሳ ተገድለዋል፡፡ እንዲሁም መተዳደሪያቸውን አጥተዋል። በኃይለ ማርያም አስተዳደር ጊዜም በኦሮሚያ ክልል ብዙ ንፁኃን የወላይታ ተወላጆች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከወላይታ ብሔር

Splitting Southern Nations region into four can promote peace

  For  more than two decades, the question of statehood formation has been  raised  by identiy-based zones in the Southern Nations Nationalities and Peoples’ Regional State (SNNPRS). In particular, the issue proliferated after the collapse of the authority of the Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front (EPRDF) and the  arrival  of Prime Minister Abiy Ahmed in 2018. Consequently, the question has been  raised  by the Wolayta, Keffa, Gurage, Gamo, Gofa, and Sidama ethnic groups. Given this political context and the House of Federation’s  approval  this week of the zonal councils of Dawro, Bench Sheko, Sheka, West Omo and Keffa’s request to form a single region, it is important to assess this new approach to regional statehood in Ethiopia. Fresh thinking During Ethiopia’s last transition, Southern Nations Nationalities and People’s Regional State (SNNPRS) was formed by  merging  five districts following regional council elections in 1992. Furthermore, as a region of  more than 5

የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ለ2013 ዓ.ም 10.7 ቢሊዮን ብር በጀት አፀደቀ

የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ለ2013 ዓ.ም 10.7 ቢሊዮን ብር በጀት አፀደቀ  ****************** የሲዳማ ክልል ምክር ቤት የ2013 የስራ ዘመን የክልሉ በጀትን 10.7 ቢሊየን ብር አድርጎ በሙሉ ድምፅ አፀደቀ። ምክር ቤቱ ትናንት በሀዋሳ ማካሄድ በጀመረው 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤው ዛሬ ቀጥሎ ሲውል የ2013 ዓ.ም የክልሉ በጀት 10 ቢሊዮን 725 ሚሊዮን 142 ሺህ ብር እንዲሆን የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ በሙሉ ድምፅ አፅድቆታል።  በጀቱ ከፌደራል እና ከውስጥ ገቢ የሚገኝ እንደሆነ ታውቋል። በቅርቡ በሀገሪቱ 10ኛ ክልል በመሆን የተዋቀረው የሲዳማ ክልል ምክር ቤት የመጀመሪያ ጉባኤውን በማካሄድ ላይ ነው የሚገኘው። ምክር ቤቱ ዛሬ በሚጠናቀቀው ጉባኤው ከሰዓት በሗላም የጠቅላይ ፍርድ ቤት እና በዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የ2013 ዕቅድ ዙሪያ የሚመክር ሲሆን በተለያዩ አዋጆች እና ሹመቶች ላይም ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል። ©Ebc

የሲዳማ እጅግ አስደማሚው የቄጣላ ጭፈራ በሰላማዊ ሰልፍ፤ ለመሆኑ የሲዳማ ጥያቄ በክልሉ መንግስት ተመልሰው ይሁን??

Ethiopian Sidama Culture - እጅግ አስደማሚው የሲዳማ ባህልና የሲዳማ ቤት አሰራርን ይመልከቱ

yehawaasa zuriya worede tefenakewoch