Skip to main content

Posts

የ2013 የትምህርት ዘመን የኮቪድ በሸታን በመከላከል የመማር ማስተማር ሂደት ለመቀጠል አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት መደረጉ ተገለፀ

የ2013 የትምህርት ዘመን የኮቪድ በሸታን በመከላከል የመማር ማስተማር ሂደት ለመቀጠል አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት መደረጉ ተገለፀ
ይህ የተገለፀው የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ 2013 ዓ/ም የትምህርት ሥራ የህዝብ ንቅናቄ መድረክ ባካሄደበት ወቅት ነው።
በመድረኩ የ2012 ዓ/ም የትምህርት ዘመን የኮቪድ በሸታ በመከሠቱ ምክንያት የመማር ማስተማሩ መቋረጡን የተገለፀ ሲሆን ለተማሪዎች በሚያመች መንገድ ትምህርት በመስጠት ከ8ኛ እና 12 ክፍል ውጪ ካሉበት ክፍል ወደ ሚቀጠለው እንዲዛወሩ መደረጉን አቶ መልካሙ ወርቁ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ እና ቤቶችና ኮንስትራክሽን መምሪያ ሀላፊ ገልፀዋል ።
ም/ከንቲባው አክለውም በሸታው አብሮ በመቆየቱ ምክንያት አንደ ሀገር በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት በልዩ ጥንቃቄ ባስገዳጅ ሁኔታ የማር ማስተማሩ ህደት መቀጠል እንደሚገባ አስረድተዋል ።  
ይህን በሸታ በመንግሥት ብቻ መከላከል ስለማይቻል ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መሠራት እንደሚገባ አክለዋል። 
የ2013 የትምህርት ዘመን እደበፊቱ ቅደመ ዝግጅት ሳይደረግ ሳይሆን ት/ቤቶች በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት መሟላት መዘጋጀት እንደሚገባ የትምህርት መምሪያ ሀላፊ አቶ ደስታ ገልፀዋል። 
በመማር ማስተማሩ ወቅት ትምህርት በፈረቃ በመሆኑ መግቢያ እና መውጫ ሰአት የተሻሻለ ሲሆን የተማሪዎች በሳምንት በፈረቃ 3 ቀን በግሩፕ ተከፍለው እንደሚማሩም ነው ሀላፊው ያስረዱት።
በዚህም አንደኛው ግሩፕ ሰኞ፣ ረቡዕ እና አርብ ጥዋትና ከሰዓት በፈረቃ የሚማሩ ሲሆን በተመሳሳይም ሌላኛው ግሩፕ ማክሰኞ፣ ሀሙስና ቅዳሜ ትምህርታቸውን የሚከታተሉ እንደሆነም አቶ ደስታ አስረድተዋል።
የመማሪያ ክፍሎችን በተመከተ የክፍል ስፋታቸው 56 ካሬ የሆነ 25 ተማሪ ብቻ የሚማር ሆኖ በአንድ መቀመጫ አንድ …

Sacred sites and ancestor veneration in Sidama, southwest Ethiopia: A socio-ecological perspective

Abstract This paper attempts to show the importance of sacred natural sites (SNS) among indigenous peoples and local communities serving as the locus of maintenance, continuity and expressions of religious identity drawing lessons from Sidama nation of Southern Nations, Nationalities and Peoples’ Regional State of Ethiopia. The paper further addresses the relationship between SNS and ancestor veneration and their mutual interdependence and preservation, exploring the socio-ecological and biocultural foundations of the interrelationship between the two systems, the dynamics of religious syncretism, and the resilience and challenges of threat facing the two systems. The paper argues that SNS and ancestor worship systems and the mutual interrelationships that exist therein are resilient social-ecological systems, created and maintained dynamically as biocultural diversity realities in historical ecological framework through human–environment interactions over millennia; and that SNS are, …

የ2020 የኖቤል የሰላም ሽልማትን የዓለም የምግብ ፕሮግራም አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የ2020 የኖቤል የሰላም ሽልማትን የዓለም ምግብ ፕሮግራም አሸነፈ፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አንዱ አካል የሆነው የዓለም የምግብ ፕሮግራም የዘንድሮውን የሰላም ሽልማት የወሰደው ረሃብን ለመዋጋት ባደረገው ጥረት መሆኑን ኮሚቴው አስታውቋል፡፡ በዚህም የዓለም የምግብ ፕሮግራም ከኮሚቴው 1 ነጥብ 1 ሚሊየን ዶላር ተበርክቶለታል፡፡ ፕሮግራሙ ይህንን የኖቤል ሽልማት ሲያሸንፍ 101ኛ ነው ተብሏል፡፡ የፕሮግራሙ ቃል አቀባይ የሽልማቱን ይፋ መሆን ተከትሎ ደስታቸውን ገልጸዋል፡፡ የዓለም ምግብ ፕሮግራም በ88 ሃገራት ውስጥ የሚገኙ 97 ሚሊየን ሰዎችን እንደሚደግፍ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ማህበራዊ ድረ-ገጽን በአግባቡ አለመጠቀም ከ50 ሺህ ብር እስከ አምስት ዓመት እስራት ያስቀጣል

ማህበራዊ ድረ-ገጽን በአግባቡ አለመጠቀም ከ50 ሺህ ብር እስከ አምስት ዓመት እስራት ያስቀጣል
አዲስ አበባ ፣መስከረም 29፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ማህበራዊ ድረ-ገጽን በአግባቡ አለመጠቀም የህግ ተጠያቂነትን እንደሚያስከትል ተገለጸ፡፡ በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ህግ የሰውዘር አበበ እንዳሉት÷ የማህበራዊ ድረ-ገጽ አጠቃቀምን አስመልክቶ በህግ የተቀመጡ ገደቦችን ሳያልፉ ለታለመለት አላማ ብቻ መጠቀም ተገቢ ነው፡፡ ነገር ግን የማህበራዊ ድረ-ገጽን ላልተፈለገ እኩይ ተግባር በማዋል የሀሰተኛ መረጃና የጥላቻ ንግግር ለማስተላለፊያነት በመጠቀም የሌሎችን ሰብዓዊ ክብር የሚነኩ እንዲሁም ባልተጨበጠ መረጃ ህብረተሰቡ ግራ እንዲጋባ ለማድረግ ያለአግባብ የሚጠቀሙ አካላትን ተጠያቂ የሚያደርግ የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትና የጥላቻ ንግግርን የሚከለክል አዋጅ ወጥቶ ስራ ላይ እንደዋለም አስታውሰዋል፡፡ በአዋጁ ከተካተቱት መካከልም የጥላቻ ንግግርን በብሮድካስት፣ በህትመት ወይም በማህበራዊ ሚዲያ ወይንም ሌላ ተመሳሳይ ዘዴዎችን በመጠቀም ያስተላለፈ እስከ 2 አመት በሚደርስ እስራትና 100 ሺህ ብር እንደሚያስቀጣ አብራርተዋል፡፡ በተላለፈው የጥላቻ ንግግር ምክንያት በግለሰብ ወይም በቡድን ላይ ጥቃት ደርሶ እንደሆነ የቅጣቱ ጊዜ እስከ 5 ዓመት የሚደርስ ቅጣት ሊተላለፍ ይችላል ብለዋል፡፡ እንዲሁም ሀሰተኛ መረጃዎችን በአደባባይ ስብሰባዎች፣ በብሮድካስት፣ በማህበራዊ ሚዲያ ወይም በሌላ ተመሳሳይ ዘዴዎች አማካኝነት በምስል፣ በጽሁፍ ወይም በቪዲዮ በመጠቀም ያሰራጨ 1 ዓመት በሚደርስ እስራት ወይም የ50 ሺህ ብር ቅጣት ሊተላለፍበት ይችላል ነው ያሉት ዐቃቤ ህጓ፡፡ በተጨማሪም መረጃው ከ5 ሺህ በላይ ተከታይ ባለው ማህበራዊ ድረ-ገጽ የተላለፈና ጉዳት የደረሰ እንደሆነ ግን የቅጣ…

በኢትዮጵያ 8 ዩኒቨርሲቲዎች የምርምር ልህቀት ማዕከል ተብለው ተለዩ

በኢትዮጵያ ስምንት የመንግሰት ዩኒቨርሲቲዎች የምርምር ልህቀት ማዕከል በመባል መለየታቸውን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በተመረጡ ትምህርት ቤቶች በትምህርት ጥራት ዙሪያ ያካሄደውን የምርምር ግኝቶች ላይ ትላንት ከባለድርሻዎች ጋር ተወያይቷል። የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አማካሪ ዶክተር ወርቁ ነጋሽ በወቅቱ እንደገለጹት በሃገሪቱ የሚገኙ 46 ዩኒቨርሲቲዎች በምርምር፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ እንዲሁም በአጠቃላይ ትምህርት በሚል በሶስት ደረጃዎች ተለይተዋል፡፡ ባለፉት አመታት በርካታ ችግር ፈቺ የምርምር ውጤቶችን ሲያበረክቱ የቆዩና ወደፊትም አስተዋጽኦ ይኖራቸዋል የተባሉ ስምንት ዩኒቨርሲቲዎች በምርምር ዘርፍ የልህቀት ማእከል እንዲሆኑ መለየታቸውን ተናግረዋል፡፡ “ጎንደር፣ አዲስ አበባ፣ ባህርዳር፣ መቀሌ፣ ጅማ፣ ሃዋሳ፣ አርባምንጭና ሀሮማያ ዩኒቨርሲቲዎች የምርምር ልህቀት ማእከል እንዲሆኑ ተለይተዋል” ብለዋል። ለአንድ ሀገር ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ችግር ፈቺ ምርምር ቁልፍ ሚና እንዳለው የገለጹት ዶክተር ወርቁ “ያደጉ ሃገሮች የእድገት ሚስጥርም ከዚህ የመነጨ ነው” ብለዋል፡፡ የምርምር ዩኒቨርሲቲዎቹ በአለም አቀፍ ደረጃ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር አቻ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ አቅማቸውን ለመገንባት በትኩረት እንደሚሰራ አመላክተዋል፡፡ ሌሎች 15 የመንግሰት ዩኒቨርሲቲዎች ደግሞ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ትምህርትና ስልጠና እንዲሰጡ መለየታቸውን ተናግረዋል ። ዩኒቨርሲቲዎቹ በቂ እውቀትና ክህሎት ያዳበረ ዜጋ ማፍራት እንዲችሉ ተከታታይ ድጋፍ እንደሚደረግላቸው አመላክተዋል። ቀሪዎቹ 23 ዩኒቨርሲቲዎች ደግሞ አጠቃላይ ትምህርትና ስልጠና እንዲሰጡ የተለዩ መሆኑን ዶክተር ወርቁ አስታውቀዋል ። የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬ…

በተያዘው በጀት ዓመት የህብረተሰቡን የመሰረተ ልማት ጥያቄዎችን ለመመለስ እየተሰራ ነው

Ugandan Reacts To Hawassa Industrial Park The Only Kind In Africa'

በተለያዩ አደጋዎች ለተጠቁ ወገኖች በሲዳማ ክልል መንግስት የሚደረገው የገንዘብ ድጋፍ ከቤት ቢጀምር ጥሩ ነው ተባለ

የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር ከሰሞኑ በአፋር የጎርፍ አደጋ ለተጠቁ ወገኖች የ5 ሚልዮን ብር ድጋፍ ያደረገ ሲሆን በዛሬው እለት ደግሞ በቅርቡ በሻሸመኔው ጥቃት ለተጎዱ መልሶ ማቋቋምያ የ3.5 ሚልዮን ብር ድጋፍ አድርጓል።የሲዳማ ክልል እያደረገ ያለው ድጋፍ ከሞራልም ሆነ ከዲፕሎማሲ አንጻር ሲታይ ትክክለኛ እና የሚበረታታ ተግባር ነው።ሆኖም ግን ለተጎዱት ድጋፍ የማድረጉ ስራ ከቤት ቢጀመር የበለጠ ጥሩ ይሆናል።
ለምሳሌ:- *በ1971-73 ዓም ሱማሊያ ሞቃዲሾ ድረስ በእግር ተጉዘው ወታደራዊ ስልጠና ወስደው በመመለስ ከአምባገነኑ የደርግ ሰራዊ ጋር እልህ አስጨራሽ ትግል በማድረግ ሲዳማን ነጻ ያወጡ የቀድሞ የሲዓን አባላት/ወታደሮች እና ቤተሰቦቻቸው። *በ1994 የሲዳማን የክልል ጥያቄ አንግበው ሀዋሳ ሎቄ ላይ ሰላማዊ ሰልፈው ወጥተው በፌደራል ፖሊስ ቶክስ ተከፍቶባቸው ለሞቱ እና ለቆሰሉ የሎቄ ሰማዕታት እና ቤተሰቦቻቸው። *በ11/11/11 ህዝባዊ ተቃውሞ ወቅት በመንግስት ወታደሮች ለተገደሉ እና ለቆሰሉ ሰማዕታት እና ቤተሰቦቻቸው። *ከአጎራባች ክልል ተፈናቅለው በበሌላ መጠልያ ካምፕ ውስጥ ለ3 ዓመታት ተጠልለው ለሚገኙ 39,000 የሲዳማ ተወላጆች። *በሎካ አባያ እና በሀዋሳ ሀይቅ ዙርያ የሚገኙ መኖርያ ቤታቸው እንዲሁም የእርሻ መሬታቸው በውሀ መሙላት ለተጥለቀለቀባቸው እና ሌሎች መሰል እርዳታ ለሚሹ ወገኖቻችንም ትኩረት ቢሰጥ እንላለን። ©ማሳንቱ

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የሱፐርቪዥንና ዩኒቨርሲቲዎችን ጎብኚ ቡድን ሥራውን በይፋ ጀመረ

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የሱፐርቪዥንና ዩኒቨርሲቲዎችን ጎብኚ ቡድን ሥራውን በይፋ ጀመረ፡፡ ቡድኑ ባሁኑ ሰዓት በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በመገኘት ከዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንትና ከፍተኛ አመራር ጋር ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
MoSHE supervision team has officially started its supervision and campus visit. HU top management is holding discussion with the team.
We will be back soon for more... Source© the H.University

Hawassa/የሐዋሳ ሐይቅ በዘንድሮ ክረምት እንዲህ ሞልቷል