Skip to main content

Posts

ለደቡብ ክልል አፈ-ጉባዔ ጽ/ቤት ሀዋሳ፤ ጉዳዩ፡- በህገ-መንግስቱ መሠረት የሥልጣን ርክክብ እንዲደረግ ስለማሳሰብ፤ ========= አንደሚታወቀው ሁሉ የሲዳማ ህዝብ ለዚህች አገር ሰላም፣መረጋጋትና አንድነት የራሱን የታሪክ አሻራ ያኖረና በአንፃሩም ደግሞ በየዘመኑ የሚፈራረቁ አምባገነን የኢትየጵያ ገዢዎች የሚያደርሱበትን በደልና አፈና በጽናት ስታገል የቆየ ህዝብ እንደሆነ ታሪካዊ ሀቅ ነው፡፡ በተለያዩ ጊዜያት የሀገሪቷን ሥልጣን ኮርቻ የሚቆናጠጡ ገዢዎች ሲዳማን ሳይሆን የሲዳማን ሀብት ለመቀራመት ካላቸው ከፍተኛ ፍላጎት የህዝቡን ቋንቋ፣ታሪክ፣ ባህልና ማኅበራዊ አሻራና ማንነት ለመናድ ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡የሀገር ግንባታ ሂደት የማንነት ፈተና በማይሆንበት መልኩ መስራት ይቻላል የሚል ጠንካራ አቋም ማራመድ የጀመሩት የሲዳማ ቀደምት ታጋዮችና ሌሎች የትግል አርበኞች በከፈሉት የህይወት ዋጋ ላለፉት 28 አመታት ስራ ላይ የዋለው ህገ-መንግስታዊ ሥርዓት እውን ሆኗል፡፡ ምንም እንኳን የሲዳማ ህዝብ የጭቁን ብሔሮችን ድምጽ አስተጋብቶና ታግሎ ለ1987 ዓ.ም ህገ-መንግስት ታሪክ የማይረሳ አሻራውን ለማሳረፍ ቢበቃም የሲዳማ ምድር እንጅ የሲዳማ ህዝብን አምርረው በሚጠሉ ገዢ መደቦች በተጠነሰሰ ሴራዎች ህዝባችን የህገ-መንግስቱ ትሩፋት ተቋዳሽ እንዳይሆን በመታገዱ ምክንያት ለቀጣይ ሰላማዊ የትግል ምዕራፍ ለመቀጠል ተገዶአል፡፡ በገዛ ሀገሩ ወደ ዳር የተገፋና በይ ተመልካች ሆኖ ለዘመናት የቆየው ሰፊው የሲዳማ ህዝብ በደሙና ባጥንቱ የተጻፈው ህገ-መንግስት ሊታደገው ባለመቻሉ ለሞት፣ ለስደትና ለእስራት ቢዳረግም ቅሉ ህዝብን ግን ከትግል ወደ ኋላ ሊያስቀረው አልቻለም ፡፡ በመሆኑም ከአባቶች የተወረሰ መብትን የማስከበር የትግል ወኔ ለዚህ ዘመን ትውልድ በመድረሱ አዲሱ ትውልድም የትግል

“ኤጄቶ የለወጥ ሃይል እንጂ አልቃይዳ ወይም አልሸባብ አይደለም”፤ ዛሬ ከእስር የተፈቱ የኤጄቶ መሪዎች

ኤጄቶ የለወጥ ሃይል እንጂ አልቃይዳ ወይም አልሸባብ አይደለም”፤ ዛሬ ከእስር የተፈቱ የኤጄቶ መሪዎች “ የተወሰኑ የሲዳማ ኤጄቶ መሪዎች ዛሬ ከእስር መፈታታቸውን ተከትሎ ከፍተኛ ቀጥር ያለው ህዝብ ደማቅ አቀባበል ያደረገላቸው ሲሆን፤ በሀዋሳ አለም አቀፍ ስታዲዬም ለተገኝተው ህዝብን ኤጄቶዎቹ ምስጋና አቅርበዋል። በእስር ላይ በነበሩነት ወራት ከጎናቸው በመሆን ያበረታቷቸውን የቀድሞ ሲዳማ አመራሮችን አመስግነዋል። “ኤጄቶ የለወጥ ሃይል እንጂ አልቃይዳ ወይም አልሸባብ አይደለም” ብለዋል። አክለውም ለዶክተር አብይ አህመድ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን፤ የአሁኑ የሲዳማ ዞን አስተዳደር የስልጣን ርክክቡን እንዲያፋጥኑ አሳስበዋል።

ሀዋሳ ከተማ ያለ ሀዋሳ ሀይቅ ማሰብ ከባድ ነው።

የሲዳማዋን ሀዋሳ ከተማ ያለ የፍቅር ሀይቋ ማሰብ በእርግጥም ከባድ ነው። የሲዳማ ክልል አስተዳደር እና የከተማዋ ነዋሪዎች በሀይቁ ላይ የተጋረጠውን አደጋ ለመቅረፍ በአንድነት መስራት ለነገ የሚባል ጉዳይ አይደለም!!  

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ ዛሬ በደረሰው የአፈር መደርመስ አደጋ ህይወታቸውን ላጡ እና ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገለፁ

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ ዛሬ በደረሰው የአፈር መደርመስ አደጋ ህይወታቸውን ላጡ እና ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገለፁ፡፡ በድንጋይ ካባ ላይ በደረሰ የአፈር መደርመስ በስራ ላይ የነበሩ የ 2 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ 3 ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡ በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር በሀዌላ ቱላ ክፍለከተማ በሀዌላ ወንዶ ቀበሌ ልዩ ስሙ ኩዌ እየተባለ በሚጠራው የድንጋይ ካባ ላይ በደረሰ የአፈር ናዳ አደጋው መከሰቱን የገለፁት የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ ኮሎኔል ሮዳሞ ኪአ አደጋው በደረሰበት ሰዓት በስራ ላይ የነበሩ 5 ሰራተኞች ላይ ካባው ተንዶ 2ቱ ወዲያውኑ ህይወታቸው ሲያልፍ በ3ቱ ላይ ጉዳት ደርሶ ሆስፒታል መወሰዳቸውን ገልፀዋል፡፡ አቶ ጥራቱ በየነ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ በተፈጠረው ድንገተኛ የአፈር መደርመስ ሕይወታቸውን ላጡ እና ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልፀው ከተማ አስተዳደሩ የጉዳቱን መጠን ለመቀነስ ጥረት እያደረገ ይገኛልም ብለዋል፡፡ መንግስት ተመሳሳይ ችግር ዳግም እንዳይከሰት የጥንቃቄ እርምጃዎችን እንደሚወስድ ያመላከቱት ም/ከንቲባው በአደጋው ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች ቤተሰቦቻቸው እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን ተመኝተዋል፡፡ ምንጩ: የከተማዋ አስተዳደር 

የሲዳማ የፖለቲካ ኃይሎች አሠላለፍና የመንፃት አስተሳሰብ ፈተና

በሀላሌ ሲዳማ የሲዳማ ብሔር አሁን በሚኖርበት አካባቢ የሰፈረው በ16ኛው ክፍለ ዘመን እንደነበረ የተለያዩ ጸሐፊዎች ያነሳሉ (Brogger 1986፣ 26፣ Hamer 1987፣ Braukamper 1977, Haileyesus Seba 2003)። የሲዳማ ብሔር በዚህ አካባቢ ከሠፈረበት ጊዜ ጀምሮ በአካባቢው ከነበሩ ሌሎች ማኅበረሰቦች ጋር መልካም ግንኙነት ነበረው። ሆኖም በ17ኛው ክፍለ ዘመን የራሱን የአስተዳደርና የአምልኮ ሥርዓት ለማከናወን በተደጋጋሚ ሙከራ ቢያደርግም፣ በአከባቢው ይኖሩ የነበሩ ማኅበረሰቦች አዎንታዊ ምላሽ ባለመስጠታቸው ምክንያት ወደ ትግል ሊገባ ተገልዷል። ባደረገው ትግልም በአሸናፊነት በመውጣት የራሱን የአስተዳደር ሥርዓት መመሥረቱ ይነገራል (ቤታና ሆጤሳ 2013፣ 63)። በዚያን ጊዜ በትግሉ ግንባር ቀደም ነን ያሉና ትውልዳቸውን ከቡሼ የዘር ሐረግ የሚመዙት የሼቤዲኖ፣ ያናሴ፣ ዊጋ፣ ማልጋ፣ ሆሎ፣ ጋርብቾና ሃርቤጎና ጎሳዎች “የመሬቾ” የተባለና በአንጋ (Anga) የመንፃት (Wolapho) ፍልስፍና የሚመራ የባህል፣ የሃይማኖትና የአስተዳደር ሥርዓት እንደ መሠረቱ ይነገራል (Hamer 1987፣ 32)። በዚህ ሥርዓት ያልታቀፉ “የአለታ” ቡድን አባላት ይህን አደረጃጀት ተቃውመው የተሠለፉ ሲሆን፣ በሁለቱም ቡድን ያልተሳተፉ ሌሎች የሲዳማ ጎሳዎች በሦስተኛ ቡድንነት በመፈረጃቸው ምክንያት፣ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ በሲዳማ ውስጥ የሦስት ቡድኖች ክፍፍል እንደ ተመሠረተ ይነገራል። የየመሬቾ ኃይል በሲዳማ ውስጥ የባህል፣ የሃይማኖትና የአስተዳደር ሥርዓት ላይ ከፍተኛ ሚና የነበረው ቢሆንም በአለታ ቡድን ሊሸነፍ ችሏል። ይህም ለሁለቱም ቡድኖች መፍረስና በፍልስፍናው ስም ለሚጠራ የወላዊቾ (Wolawichcho) ቡድን መመሥረት ምክንያት በመሆን የኃይል አሠላለፉን ከሦስት ወ

Honey Producers Cooperative at Sidama Shebedino