Skip to main content

Posts

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ጸብ ሕይወት አጠፋ

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ጸብ ሕይወት አጠፋ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በተማሪዎች መካከል በተነሳ ጸብ የአንድ ተማሪ ሕይወት ማለፉን ዩኒቨርሲቲው አስታወቀ። ትናንት ምሽት በዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ በተከሰተው ጸብ የአንደኛ ዓመት የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ ሕይወት ማለፉን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አየለ አዳቶ ለዶቼ ቬለ (DW) ገልጸዋል። የተማሪው አስክሬን በአዲስ አበባ ምንሊክ ሆስፒታል ምርመራ ከተደረገለት በኋላ ወደ ትውልድ ስፍራው ወልዲያ መላኩንም የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ ተናግረዋል። የነገሩ መነሻ የሁለት ተማሪዎች ጸብ መሆኑን የጠቀሱት አቶ አየለ ከጀርባው ሌላ ተልኮ ይኑረው ወይንም አይኑረው እየተጣራ ይገኛል ብለዋል። አክለውም « በአሁኑ ወቅት ከግድያው ጋር በተያያዘም 44 ተማሪዎች በቁጥጥር ሰር ውለው በፖሊስ ምርመራ እየተደረገባቸው ይገኛል።» ብለዋል። «የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብም በተፈጠረው ሁኔታ በከፍተኛ ሀዘን ውስጥ ቢገኝም የመማር ማስተማሩ ሂደት ግን ሳይቋረጥ ቀጥሏል» ሲሉም አክለዋል። የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ እስካሁን ሰላማዊ ድባብ ከሚስተዋልባቸው ጥቂት የአገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል አንዱ በመሆን ይታወቃል። አሁን የተባለው ጸብ የተነሳውና የሰው ሕይወትም ያለፈው ተማሪዎቹ ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ የአንደኛ ወሰነ ትምህርት ፈተና ለመውሰድ በዝግጅት ላይ ባሉበት ወቅት መሆኑ ታውቋል። ምንጭ ።  ዶቼ ቬለ (DW)

Ethiopia passes gun control law to stem ethnic violence

ADDIS ABABA. –  Ethiopia’s parliament passed legislation yesterday aimed at curbing gun ownership after a surge in regional ethnic violence blamed on a proliferation of small arms in private hands. Prime Minister Abiy Ahmed’s government said last April that it had seized 21 machine guns, more than 33 000 handguns, 275 rifles and 300 000 bullets in different parts of the Horn of Africa country over the previous year. In October security forces confiscated a further 2 221 handguns and 71 Kalashnikov assault rifles in Gonder in the Amhara region, one of the areas particularly affected by ethnic strife, domestic media said. The rifles had been smuggled into the country in oil trucks from Sudan, they said. The spread of small arms has been partly blamed for hundreds of killings in various ethnic conflicts over the past two years that have displaced more than 2,7 million people. ‘‘There is a significant number of guns in our society since the previous government and the law wil

የታኅሳስ ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 19.5 በመቶ ደረሰ

በታኅሳስ ወር 2012 ዓ.ም. የተመዘገበው አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር ሲነፃፀር በ19.5 በመቶ ከፍ ማለቱን፣ ማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ በየወሩ በሚያወጣው የዋጋ ግሽበት ሁኔታ መረጃ አስታወቀ፡፡ ኤጀንሲው ሰኞ ታኅሳስ 27 ቀን 2012 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ የታኅሳስ ወር 2012 ዓ.ም. የምግብ ዋጋ ግሽበት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር ሲነፃፀር በ22.7 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡ በታኅሳስ ወር የአብዛኞቹ የእህል ዓይነቶች በተለይ ሩዝ፣ ጤፍ፣ ስንዴ፣ በቆሎ፣ ገብስና ማሽላ ዋጋ ካለፈው ወር ጋር ሲነፃፀር መጠነኛ ቅናሽ ማሳየቱን፣ የሥጋ ዋጋ  ጭማሪው ግን እንደ ቀጠለ መሆኑን አስረድቷል፡፡ በተጨማሪም አንዳንድ የምግብ ዓይነቶች በተለይም ቲማቲም፣ ቀይ ሽንኩርት፣ ነጭ ሽንኩርት፣ ጎመን፣ ካሮት፣ ቅቤ፣ የምግብ ዘይት፣ ወተት፣ አይብና ዕንቁላል ቅናሽ ማሳየታቸውን ኤጀንሲው ገልጿል፡፡ ይሁን እንጂ ያለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር ዋጋ ከአሁኑ ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር በንፅፅር ዝቅተኛ ስለነበር፣ የዋጋ ግሽበቱ በታኅሳስ ወር ከፍ ብሏል ሲል ኤጀንሲው አክሏል፡፡  በሌላ በኩል ምግብ ነክ ያልሆኑ የኢንዴክሱ ክፍሎች የዋጋ ግሽበት የታኅሳስ ወር 2012 ዓ.ም. ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር ሲነፃፀር የ15.8 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱ፣ በኤጀንሲው መግለጫ ተካቷል፡፡ ካለፉት ጥቂት ወራት ጀምሮ ምግብ ነክ ያልሆኑ የኢንዴክሱ ክፍሎች የዋጋ ግሽበት በተከታታይ ጭማሪ እያሳየ ነው ተብሏል፡፡ ምግብ ነክ ያልሆኑ የኢንዴክሱ ክፍሎች የዋጋ ግሽበት ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከፍ እንዲል ካደረጉት ዋና ምክንያቶች ውስጥ በተለይ ልብስና መጫሚያ፣ የቤት ኪራይ፣ የቤት እንክብካቤና ኢነርጂ (ማገዶና ከሰል)፣ የቤት

ፕሬዝዳንት ዶላንድ ትራንፕ በኢራን ጥቃት አንድም የአሜሪካ ወታደር ጉዳት አልደረሰበትም አሉ

ኢራን ኢራቅ በሚገኘው ሁለት የአሜሪካ የጦር ሰፈር ላይ በሰነዘረችው የባልስቲክ ሚሳኤል ጥቃት ምንም አይነት የሰው ጉዳት እንዳልደረሰ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስታወቁ፡፡ በጥቃቱ በጦር ሰፈሮቹ ላይ መጠነኛ ጉዳት ከመድረሱ ባለፈ በስፍራው የሚገኝ የአሜሪካም ሆነ በኢራቅ ወታደር ላይ ምንም አይነት ጉዳት አለመድረሱን በመግለፅም ለአሜሪካውያን እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡ በጥቃቱ ምንም ጉዳት ያልደረሰው አስቀድሞ በተወሰደው የጥንቃቄ እርምጃ መሆኑንን በመግለፅ የአሜሪካ የጦር ኃይል ለማንኛውም አይነት ግዳጅ በተጠንቀቅ እንደሚገኝም ነው ፕሬዝዳንቱ የገለፁት፡፡ ፕሬዝዳንት ዶላንድ ትራንፕ ዛሬ በሰጡት መግለጫ "እኔ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት እስከሆንኩ ጊዜ ድረስ ኢራን ፈፅሞ የኒኩሌር መሳሪያ እንዲኖራት አይፈቀድላትም!!" በማለት ንግግራቸውን የጀመሩት ፕሬዝዳንቱ አሜሪካ በኢራን ላይ ተጨማሪ ጠንካራ የኢኮኖሚ ማእቀቦች እንደምትጥልም አስታውቀዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው አሜሪካ ከየትኛውም አገር የበለጠ የጦር መሳሪያ እና የጦር አቅም እንዳላት በማስታወስ ያላትን አቅም እና መሳሪያ ግን አውጥታ ለመጠቀም ፍላጎት እንደሌላት ገልፀዋል፡፡ የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን ድርጅት/ኔቶ/ በመካከለኛው ምስራቅ በከፍተኛ ደረጃ ተሳትፎ እንዲያደርግ ጥሪም አቅርበዋል ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፡፡ ኢራን በአሜሪካ የድሮን ጥቃት የተገደለባትን ከፍተኛ የጦር መሪ ለመበቀል በወሰደችው በዚህ ጥቃት 15 ሚሳኤሎች በአሜሪካ የጦር ሰፈር ላይ ማስወንጨፏ ተነግሯል፡፡

ቦርዱ በቀጣዩ ምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ላይ በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ከባለድርሻ አካላት ጋር ሊወያይ ነው

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 29 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በቀጣዩ ምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ላይ በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ጨምሮ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር እንደሚወያይ አስታወቀ። የውይይቱ ዓላማም የጊዜ ሰሌዳውን ለማዳበር የሚያስችል ግብዓትን መሰብሰብ መሆኑንም ነው ያመለከተው። የቦርዱ የኮሙዩኒኬሽን አማካሪ ወይዘሪት ሶሊያና ሽመልስ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ ከባለድርሻ አካላቱ ጋር በረቂቅ የጊዜ ሰሌዳው ላይ ውይይት ተደርጎ በሚገኘው ግብዓት ከዳበረ በኋላ ይፋ ይሆናል። የተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን የቀጣዩ ብሄራዊ ምርጫ መረጃ ደርሶናል በሚል ያወጡት ዘገባ ትክክል አለመሆኑንም ቦርዶ አመላክቷል።

Sidaamu daga gashshooti qara qara ikkitino yannate hajubba aana odeessaanote xawishsha uyi.

Gashshootunnihu qaru gashshaanchi kalaa Desti Ledamohu techo barra babbaxxitino yannate hajubba lainohunni odeessaanote hala’lado xawishsha uyiino. Xawishsha uyinohuno sase qara qara hajubba aana ikkanna kurino: 1. Haaru qoqqowi safonna tantano hajo lainohunni 2. Babbaxxitino poletiku huluullonni usurantino mannanke lainohunni 3. Nookkimale duduwo daganke seekkite agadha hasiissannota  lainohunninna hattono wole kuriuu hajubba ledo amadisiisaminori qooxeessiraati. Haaru qoqqowinke safonna tantano lainohunni: xaa yannara babbaxxitino qoqqowu hajo tantano lawishshaho:qoqqowu hajo jeefissannota pirojektete borro mine, taskifoorsete uurrinshanna wolootano looso jeefissanno fullahaanote tantano; deerru deerrunkunni uurrinseenna loosu giddora e’e loossanni leeltannota qaru gashshaanchi xawise tini uurrinsoonni tantanonna borro mini; haaru qoqqowikera looso harisate horoonsi’nanni babbaxitino seeranna lallawa qixxeessatenni harancho yanna giddo balaxote loosi baalu mucci yee goofeenn

የሲዳማ ዳያስፖራ ማህበር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የሰጠው መግለጫ

የሲዳማ ሕዝብ ለዘመናት ሲጠይቀው የነበረ የራስ አስተዳደር የክልል ጥያቄ የሕዝብ ውሳኔ የተሰጠው መሆኑ ይታወቃል። በሂደቱ አዎንታዊ ሚና የነበራቸውን ሁሉንም አካላት የሲዳማ ዳያስፖራ ማህበር ማመስገኑም ይታወሳል። ሆኖም የሕዝቡን ውሳኔ ተከትሎ መሰራት ያለባቸው የሽግግር ስራዎች በመንግስት ባለመከናወናቸው ህዝቡ ውስጥ እያደር ሌላ ጥርጣሬ ፈጥሯል። በሀገራችን ሕዝቦች እንዲሁም በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ በፍጹም ሠላማዊነቱ እና ሁሉን አካታች በሆነ መልኩ መከናወኑ የተመሰከረለት ህዝበ ውሳኔ ቢደረግም ሽግግሩን አስመልክቶ መቼ እና እንዴት ይከናወናል በሚሉ ጉዳዮች ላይ ግልጽ መግለጫ ለሕዝቡ አለመሰጠቱ አግባብነት የሌለው መሆኑን ማ ህበራችን ያምናል። ከዚህም ባሻገር በሲዳማ ሕዝብ ላይ የሚደርሰው ግፍ እና በደል አሁንም መቀጠሉን የሚያመላክቱ በርካታ ማስረጃዎች በማህበሩ እጅ እንደገቡ፣ በእነዚህ እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የማህበሩ ስራ አስፈጻሚ እና አባላት በ 12/ 29/2019 ዓ. ም ባካሄዱት አስቸኳይ የምክክር ስብሰባ የሚከተለውን ባለ ስድስት ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥቷል። 1ኛ. የሲዳማ ሕዝብ እጅግ ውድ መስዋዕትነት ከፍሎ ያገኘውን ድል በልመና እንዲፈጸም ለማድረግ የሚደረግ አሻጥር በፍጥነት እንድቆም እና የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ለአዲሱ ለሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አስፈላጊውን የርክክብ ስነ ስርዓት የሚፈጽምበትን የጊዜ ገደብ እንዲያስቀምጥ እንጠይቃለን፤ አተገባበሩም ቶሎ እንዲገባደድ እናሳስባለን። 2ኛ. ሕዝባችን ራሱን በራሱ የሚያስተዳድርበት ክልላዊ አስተዳደር እንዲመሰረት በመጠየቃቸው እና ሕዝቡን በማስተባበራቸው ብቻ በህገወጥ መንግስታዊ ድርጊት ያለወንጀላቸው ለወራት በእስር ላይ የሚንገላቱ የሚዲያ ሰወች፣ ምሁራኖ