11ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ቅዳሜ እና እሁድ በሚደረጉ ጨዋታዎች ቀጥሎ ይውላል። ቅዳሜ በአዲስ አበባው የአበበ ቢቂላ ስታዲየም ንግድ ባንክ ከወላይታ ዲቻ 8 ሰዓት ላይ የሚጫወቱ ሲሆን፥ ሙገር ስሚንቶ ከሀዋሳ ከነማ 10 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ። እሁድ በሚደረጉ ጨዋታዎች በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ሁለት ጨዋታዎች የሚካሄዱ ሲሆን፥ መብራት ሀይል ከአዳማ ከነማ በስምንት ሰዓት እንዲሁም ኢትዮጵያ ቡና ከመከላከያ 10 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያካሂዳሉ። ክልል ላይ በሚደረጉ ጨዋታዎች ዳሽን ቢራ ከደደቢት፣ አርባምንጭ ከነማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ እንዲሁም ሲዳማ ከወልዲያ በተመሳሳይ 9 ሰዓት ላይ የየሚጋጠሙ ይሆናል። ፕሪሚየር ሊጉን ሲዳማ ቡና 10 ጨዋታዎች አድርጎ በ20 ነጥብ ሲመራ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ9 ጨዋታ 18 ነጥብ ይዞ ሁለተኛ ላይ ይገኛል እንዲሁም መከላከያ በ10 ጨዋታ በ16 ነጥብ በሶስተኝነት ይከተላል።
It's about Sidaama!