በሲዳማ ክልል ያለውን ዕምቅ የቱሪዝም አቅም ጥቅም ላይ ለማዋል በትኩረት እንደሚሰራ ተገለጸ -------------------------- በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ያለውን ዕምቅ የቱሪዝም አቅም በተገቢው ጥቅም ላይ ለማዋል በትኩረት እንደሚሰራ ተገለጸ፡፡ በክልሉ 33ኛውን የዓለም የቱሪዝም ቀን “ቱሪዝም ለገጠር ልማት በሚል መሪ ቃል” ተከብሯል፡፡ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ደስታ ሌዳሞ በዚህን ወቅት እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ ከቱሪዝም ዘርፍ ባላት አቅም ልክ ተጠቃሚ አልነበረችም፡፡ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ዘርፉ በተሰጠው ልዩ ትኩረት ከፍተኛ ዕሴት የሚጨምሩ ታላላቅ ፕሮጀክቶች በሀገር ደረጃ ተጀምረው በመጠናቀቅ ላይ ናቸው ያሉት አቶ ደስታ፣ ፕሮጀክቶቹ ወደ ክልሎች የሚደረግ የቱሪዝም ፍሰትን ከማሳደግ ረገድ ጉልህ ድርሻ እንዳላቸው እና በክልል ደረጃም በዘርፉ ለውጥ ማምጣት የሚያስችሉ ታላላቅ ፕሮጀክቶችን ይፋ በማድረግ ወደ ስራ መገባቱንም ገልጸዋል፡፡ ክልሉ በርካታ የዓለምን ህዝብ ቀልብ የሚስቡ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ የቱሪዝም ሀብት መገኛ እንደሆነ ገልጸው፣ በቅንጅት እና በጋራ በመስራት በቱሪዝም ዘርፍን ለማሳደግ ይሰራል ብለዋል፡፡ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጀጎ አገኘሁ በበኩላቸው፣ የአቃፊነት እና የአብሮነት ተምሳሌት የሆነው የሲዳማ ብሔራዊ ክልል ዕምቅ የቱሪዝም አቅም እንዳለው እና በዘርፉ የሚታዩ ውስጣዊ እና ውጫዊ ችግሮች ተለይተው በአጠረ ጊዜ ውስጥ ለመፍታት የሚያስችል ዕቅድ ተይዞ ወደ ተግባር እንደተገባ ተናግረዋል፡፡ በተለይ በቱሪዝም መዳረሻዎች አከባቢ የሚታዩ ችግሮችን በመፍታት የቱሪዝም ዘርፉ ተገቢውን ጥቅም እንዲሰጥ በሚደረገው ጥረት በየደረጃው ያለ አመራር እና ባለድርሻ አካል ኃላፊነቱን በተገቢው መወጣት
It's about Sidaama!