በሲዳማ ክልል ለዘመንናት በነበርው የትኩረት ማነስ የተነሳ፣ በክልሉ ባሉ ትምህርት ቤቶች ትምህርታቸውን ተከታትሎ በአገር አቀፍ ደረጃ በሚሰጡት ፈተናዎች ላይ የሚቀመጡ ተማሪዎች ዝቅተኛ ውጤን በማስመዝገብ የክልሉን የትምህርት ጥራት ችግር በአደባባይ ማስጣታቸውን ተከትሎ፤ የክልሉ መንግስት በጀመረው የትምህርትን ጥራት ከመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ጀምሮ ለማስተካከል፣ በመማሪ ማስተማሪያ ህደቶችን ለማቀላጠፍ የሚያስችሉ ጥራት ያላቸው የመማሪያ ትምህርት ቤቶችን የመገንባት እና ለዚሁም ስራ ከመንግስት ብቻ ሳይሆን የክልሉ ባለሃብቶችን ተሳታፍ መድረጉን ተከትሎ፣ በርካታ የክልሉ ባለሃብቶች በራሳቸው ተነሳሽነት ትምህርት ቤቶችን በመገንባት ለህዝብ ለመስረከብ ቃል በመግባት ወደ ስራ መግባታቸው ይታወቃል።
በክልሉ የትምህርት ጥራት ላይ የራሳቸውን አሻራ ለማሳረፍ ተነሳሽነትን ወስደው ወደ ስራ ከገቡት ባለሃብቶች መካከል፣ ባለሃብት ዱካሌ ዋቃዮ በሸበዲዮ ወረዳ በቦሮያ ምሪዴ ቀበሌ ሙሉ በሙሉ የግንባታ ወጭውን በመሸፈን ያሰሩትን የKindergarden (ለጀማሪ) ተማሪዎች የሚሆን ት/ቤት ፣ ጥራቱን በጠበቀ መልኩ ገንብተው ለአገልግሎት ዝግጁ ማድረጋቸውን ሰምተናል።
ባለሃብት ካላ ዱካሌ በገቡት ቃል መስረት ትምህርት ቤቱን መስራታቸው ብቻ ሳይሆን፤ እንደ አንድ የክልሉ ተወላጆ በክልሉ ትምህርት ጥራት ላይ ይህን የመሰለ አሻራ ማሳረፋቸውን ከፍተኛ አድናቆት እና ክብር ይገባቸዋል።
በሌላ መልኩ የክልሉ መንግስት ከባለሃብቶች በተጨማሪ የክልሉን የትምህርት ጥራትን በዘላቂነት ለማሻሻል የተለያዩ ተግባትን እና እርምጃዎችን ለመወሰድ ቃል የገባ ቢሆንም እስከ አሁን ድረስ ከንግግር ባለፈ የተሰራ ስራ አለመኖሩ ይታወቃል። ሰለዚህም የክልሉ ባለሃብቶች ቃላቸውን አክብረው ወደ ስራ ከመግባታቸው በላይ፤ ሰርተውም በማሳየት ላይ በመሆናቸው የክልሉም መንግስት ቃሉን አክብረው በክልሉ ትምህርት ጥራት ላይ ስራ ሰርቶ እንዲያሳይ የክልሉ ህዝብ በመጠየቅ ላይ ይገኛል።


Comments
Post a Comment