Skip to main content

ሲዳማን ጨምሮ የ12ኛ ክፍል ፈተና ካስፈተኑ ትምህርት ቤቶች ውስጥ 39.2 በመቶው ያህሉ “አንድም ተፈታኝ” ለዩኒቨርስቲ አለማሳለፋቸው ተገለጸ

በዘንድሮው ዓመት መደበኛ ተማሪዎቻቸውን የ12ኛ ክፍል ፈተና ካስፈተኑ በመላው አገሪቱ ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች ውስጥ፤ በ39.2 በመቶው ያህሉ “አንድም ተፈታኝ” የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት እንዳላመጣ ትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ። ከመደበኛ ውጪ ያሉ ተማሪዎችን ያስተፈኑ ትምህርት ቤቶች ስሌት ውስጥ ሲገቡ፤ ምንም ተማሪ ያላለፈባቸው ትምህርት ቤቶች ብዛት ወደ 56 በመቶ ከፍ እንደሚል ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ይህንን ያስታወቁት፤ በተያዘው ዓመት በሁለት ዙር የተሰጠውን የ12ተኛ ክፍል ፈተና ውጤት አስመልክተው ዛሬ አርብ ጥር 19፤ 2015 በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው። የክልል ትምህርት ቢሮ አመራሮች በተገኙበት በተሰጠው የዛሬው መግለጫ ላይ ሚኒስትሩ የፈተናውን ውጤት እና ተያያዥ መረጃዎችን ለጋዜጠኞች በዝርዝር ገልጸዋል። ፕሮፌሰር ብርሃኑ “የሚሳዝን” ብለው በጠሩት የዘንድሮው 12ኛ ክፍል ውጤት፤ ፈተናውን በትክክል ከወሰዱት 896,520 ተማሪዎች ውስጥ የዩኒቨርስቲ መግቢያ የሆነውን 50 በመቶ ውጤት ያመጡት፤ 3.3 በመቶው ብቻ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

በመላው አገሪቱ ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ያስፈተኗቸውን ተማሪዎች ሙሉ ለሙሉ ማሳለፍ የቻሉት ሰባት ትምህርት ቤቶች ብቻ መሆናቸውንም ሚኒስትሩ ተናግረዋል። ከእነዚህ ትምህርት ቤቶች ውስጥ “ደሴ” እና “ኦዳ” ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም የወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት በትምህርት ሚኒስትሩ መግለጫ በምሳሌነት ተጠቅሰዋል። ከግል ትምህርት ቤቶች ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ተማሪዎቹ ያለፉለት 41 ተማሪዎችን ያስተፈተነው ለባዊ አካዳሚ መሆኑንም አክለዋል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ በመደበኛ የትምህርት አሰጣጥ ስርዓት ያስተማሯቸውን የቀን ተማሪዎች ለፈተና ያስቀመጡ ትምህርት ቤቶች ብዛት 2,959 እንደሆኑ በዛሬው መግለጫ ተጠቅሷል። “ከእነዚህ ውስጥ 1,798ቱ ቢያንስ አንድ ተማሪ አሳልፈዋል” ያሉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ፤ 60.7 በመቶው ያህሉ ትምህርት ቤቶች ከግማሽ በላይ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች እንዳሏቸው አስረድተዋል።

በቀሪዎቹ 39.2 በመቶ ያህል ትምርት ቤቶች ግን አንድም የ12ኛ ክፍል ተማሪ ከ50 በመቶ በላይ ውጤት እንዳላመጣ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል። ይህ ቁጥር በመደበኛ ትምህርት የወሰዱ ተማሪዎች የተፈተኑባቸው ትምህርት ቤቶችን ብቻ እንደሚያካትት ፕሮፌሰር ብርሃኑ አስታውሰዋል። “መደበኛ ተማሪዎችን ብቻ ሳይሆን ሌሎቹንም ጨምረን ካደረግን፤ የጠቅላላ የትምህርት ቤቶች ብዛት እኛ ዳታ ላይ 5,040 ነው የሚመጡት። ከዚህ ውስጥ 56 በመቶው ምንም ተማሪ አላሳለፉም” ሲሉ በሀገሪቱ ካሉት ትምህርት ቤቶች ከግማሽ በላይ በሚሆኑት አንድም ተማሪ የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት እንዳላመጣ አብራርተዋል።

በ12ኛ ክፍል ፈተና ላይ የታየው ይህ አነስተኛ ውጤት “እንደ ሀገር ትምህርት ቤቶች ምን እንደሚመስሉ የሚያሳይ ነው” ሲሉ ፕሮፌሰር ብርሃኑ በዛሬው መግለጫቸው ተናግረዋል። “ይህ ፈተና ማንነታችንን፣ የትምህርት ስርዓታችን ያለበትን ደረጃ፤ በግላጭ፣ ልንደብቀው በማንችለው መልኩ፣ በወሬና በአሉባልታ ሳይሆን በዳታ እንድናገኝ አድርጎናል” ሲሉም በአጽንኦት ተናግረዋል።

“[ለዚህ ውጤት] እውነተኛ ተጠያቂው የወደቁት ተማሪዎቻችን ብቻ አይደሉም። የወደቅነው እንደ ሀገር ነው። ኃላፊነቱም የጋራ እና የሁላችን ነው” ያሉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ፤ መምህራን፣ ርዕሰ መምህራን፣ መንግስት፣ ወላጅ እና ባለሀብቶች ተጠያቂነት እንዳለባቸው ጠቁመዋል። “ተማሪዎች በሚገባቸው ዲሲፕሊን፣ ትምህርትን ከቁም ነገር ወስደው ትምህርታቸውን መከታተል አለመቻላቸው በተወሰነ ደረጃ ተጠያቂ ያደርጋቸዋል” ያሉት ሚኒስትሩ፤ መምህራን እና ርዕሰ መምህራንም በአደራ የተቀበሏቸው ተማሪዎች ይህንን ውጤት በማስመዘገባቸው ተጠያቂ መሆናቸውን አንስተዋል።

“መንግስት እንደ መንግስት ያለበትን ኃላፊነት በምንም አይነት ተወጥቷል ማለት አይቻልም” ሲሉም “የትኛውንም መንግስት ሳይለይ” ሁሉም አገዛዝ ለተማሪዎች ውጤት ተጠያቂነት እንዳለበት አመልክተዋል። “ትምህርት ከካድሬ፣ ከፖለቲካ ጋር ተያይዞ እዚህ ደረጃ እስከሚደርስ መጠበቁ፤ በመንግስት ደረጃ ሁላችንም መንግስት ላይ ያለን ሰዎች ኃላፊነት የምንወስድበት ነው” ሲሉ ለውጤት ማሽቆለቆሉ የመንግስት ባለስልጣናት ጭምር ተጠያቂ እንደሆኑ ተናግረዋል። ከፌደራል እስከ ክልል ያሉ የትምህርት ዘርፍ አመራሮች ተጠያቂነቱን እንደሚጋሩም አስረድተዋል።

ልጆችን ስነ ምግባር በማስተማር ረገድም ወላጆች፣ እንዲሁም ትምህርት ቤቶች ኃላፊነታቸውን እንዳልተወጡም ፕሮፌሰር ብርሃኑ በመግለጫው ላይ አንስተዋል። “የግል ትምህርት ቤቶች እውነተኛ ትምህርት፣ ትክክለኛ ዲሲፕሊን ያለው ትምህርት ለልጆቻችን ይሰጣሉ ወይ? የመንግስት ትምህርት ቤቶችስ ይህንን ይሰጣሉ ወይ? ሁሉም ጋር ነው ውድቀት ያለው” በማለትም ወቀሳቸውን አሰምተዋል። “ሀብት በአቋራጭ የሚገኝበት ሀገር ሲሆን፤ [ተማሪ] ለምንድነው ትምህርት በትክክል የሚማረው?” የሚል ትችት አዘል ጥያቄም ሰንዝረዋል።

(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

Comments

Popular Posts

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የመንግሥት ስልጠና የምርጫ ቅስቀሳ አካል ነው ብሏል  የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ለምን ወጣ መባሉ ተገቢ አይደለም - ምርጫ ቦርድ ምርጫ ቦርድ ከኢህአዴግ ተፅዕኖ ሙሉ ለሙሉ ነፃ መሆኑ ሳይረጋገጥና የምርጫ አፈፃፀም ችግሮች ሳይወገዱ የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ለማወጅ መዘጋጀቱ ተገቢ አይደለም ሲል ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ የሚመሩት ኢማዴ-ደህአፓ ተቃወመ፡፡ መንግስት፤ የዩኒቨርሲቲ መምህራንና ተማሪዎችን ጨምሮ ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየሰጠ ያለው ስልጠና የምርጫ ቅስቀሳ አካል ነው ሲልም ፓርቲው ኮንኗል፡፡  የኢትዮጵያ ማህበረ ዴሞክራሲ ደቡብ ህዝቦች አንድነት ፓርቲ ሰሞኑን ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ባስገባው ግልፅ ደብዳቤ፤ ያለፉት አገር አቀፍና የአካባቢ ምርጫዎች ከመካሄዳቸው በፊት በምርጫ ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው ዙሪያ ኢህአዴግ ከተቃዋሚዎች ጋር የሚወያይበት መድረክ እንዲዘጋጅ በተደጋጋሚ ብንጠይቅም እስካሁን ከቦርዱ የተሰጠ ተግባራዊ ምላሽ የለም ብሏል፡፡  ሃገሪቱ “በአንድ አውራ ፓርቲ” ብቸኛ ቁጥጥር ስር መውደቋ አደገኛና አሳሳቢ ነው ያለው ፓርቲው፤ የመድብለ ፓርቲ ስርአት የመገንባት ተስፋችን ጨርሶ እንዳይከስም ቦርዱ ሃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት አሳስቧል፡፡ ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ የሚካሄድበትን ሁኔታ ለመፍጠር ገዥው ፓርቲና ሃቀኛ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚወያዩበት መድረክ እንዲያመቻች በህግ ስልጣን የተሰጠው ምርጫ ቦርድ የገባውን ቃል በማጠፍ መድረኩን ሳያመቻች የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማዘጋጀቱ ፋይዳ የለውም ብሏል - ፓርቲው፡፡  ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ በተሻሻለው የምርጫ ህግ፣ ለቦርዱ የተሰጠውን የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ መድረክ የማስተባበር ስልጣን ለመቀማት ታማኝ ፓርቲዎችን በተቃዋሚ ስም አሰባስቦ “የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ መድረክ” በመፍጠር የምርጫ ውድድር አሯሯጭ አሰልፏል ሲ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

የለበሰው ያደፈ ቁምጣና ሹራብ ከቅዝቃዜው አላዳነውም፡፡ ካፊያው ልብሱን አርሶታል፡፡ ሽው እያለ ከሐይቁ የሚነሳው ነፋስ የሚፈጥረው ቅዝቃዜ ያንቀጠቅጠዋል፡፡ የተጫማው ያረጀ ሲሊፐር እግሩን ከምንም አላዳነውም፡፡ በባዶ እግሩ የሚራመድ ያህል ጨቅይቷል፡፡ ተደባዳቢ ይመስል ፊቱ የተሞነጫጨረ ነው፡፡ ገና 12 ዓመቱ ቢሆንም፣ ቁመናው እንደ ትልቅ ሰው ግዙፍ ነው፡፡ የሚለብሰውን እንደ ልቡ ባያገኝም፣ የሚያስፈልገውን ነገር ለማሟላት ቤሳቢስቲን የሌላቸው ወላጆቹን አያስቸግርም፡፡ ከቤተሰቦቹ ጋር ከሚኖሩበት ታቦር ተራራ ጀርባ ወዳለው ሐዋሳ ሐይቅ ከወረደ እንኳንስ የራሱን የቤተሰቦቹንም የዕለት ጉርስ የሚሸፍንበት ገንዘብ አያጣም፡፡ የአስጎብኚነት ዕውቀት፣ ከሐይቁም ውስጥ ዓሳ የሚያጠምድበት መረብም ሆነ ፈቃድ የለውም፡፡ ሙሉቀን (ስሙ ተቀይሯል) እና ጓደኞቹ ሐይቁን ለመጎብኘት የሚሄዱ ጎብኚዎች በካሜራቸው ጥሩ ፎቶ እንዲያስቀሩ ድባቡን የማሳመር ሥራ ይሠራሉ፡፡ ካሜራውን ይዞ ቁጭ ብድግ እያለ ጥሩ ፎቶ ለማንሳት ጥረት የሚያደርግ ሲያዩ፣ ቆርጠው የያዙትን የዓሳ ሥጋ ይዘው ጠጋ ጠጋ ይላሉ፡፡ ቁርጥራጩን የዓሳ ሥጋ ምግብ ለሚቀሙት አባኮዳዎች ሻሞ ይላሉ፡፡ የተወረወረላቸውን ቀድመው ለመቅለብ አባኮዳዎቹ ክንፋቸውን እየመቱ ወደ ላይ ብድግ ይላሉ፡፡ የናሽናል ጆግሪፊ የፎቶግራፍ ባለሙያዎች ያነሱት ዓይነት ፎቶዎች ሳያስቡት ያነሳሉ፡፡ በሁኔታው ተደስተው ደጋግመው ድንቅ ፎቶዎችን ለመውሰድ ሲዘጋጁ እነ ሙሉቀንም አጀንዳቸውን ይፋ ማድረግ ይጀምራሉ፡፡ አቶ ዳዊት አብርሃም ‹‹አንዱን ዓሳ በአሥር ብር ገዝቼ ነው እንዲህ የማዘጋጀው፤›› በማለት በቅድሚያ  መረጃ ይሰጣሉ፡፡ ለቀጣዩ ዜና በዚህ መልኩ እንዲዘጋጁ ካደረጉ በኋላ፣ ሌሎች ሰዎች መቶም ሁለት መቶም ብር እንደሚሰጧቸው ቀለል

Sidama: the Luwa and the Anga Culture and their Social Implications

By Wolassa Kumo 1. Introduction In my previous articles, I mentioned the Sidama grand social constitution Seera, and various sub constitutions which derive from this grand constitution. We have also seen that all social constitutions or Seera in Sidama were based on the Sidama moral code of halale, the true way of life. In this socio-cultural and socio-political system, the role of the elders was very important. Elders were bestowed with the power of enforcing the Seera and referring the recalcitrant to Magano or God if he/she refuses to abide by the Seera. The power of elders in the Sidama society was not based on a simple age count as is the case in most modern societies. The Sidama elder is more the product of various social processes through which he passes than the product of a simple aging. For a person to become a recognised elder with authority in Sidama, he has to become a Cimeessa (respected elder with authority) or Cimeeyye for many respected elders. There are three importa