Skip to main content

Posts

Showing posts from January, 2023

የሀዋሳ ከተማ ሰላም በዘላቂነት ለማረጋገጥና የጎብኚዎችን ቁጥር ለመጨመር በትኩረት እየሰራ መሆኑን የከተማዋ ፖሊስ መመሪያ አስታወቀ

በሀገራዊና ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ሕብረ-ብሔራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት ለብልጽግና ጉዞ ስኬት በሚል መሪ ቃል በሀዋሳ ከተማ ውይይት መካሄዱን ሰምተናል

ሲዳማ ክልል ከጎሮቤት ክልል ልምድ በመቅሰም በቡና ላይ የተከሰተዉ የግንድ አድርቅ በሽታ በብዛት እየተስፋፋ በመሆኑ በቡና ምርት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሳያስከትል የመከላከሉን ስራ መስራት ይጠበቅበታል ተባለ

በ2014 በጀት ዓመት ከ2 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን በገቢዎች ሚኒስቴር የሀዋሳ ቅርንጫፍ ገለጸ

ሲዳማን ጨምሮ የ12ኛ ክፍል ፈተና ካስፈተኑ ትምህርት ቤቶች ውስጥ 39.2 በመቶው ያህሉ “አንድም ተፈታኝ” ለዩኒቨርስቲ አለማሳለፋቸው ተገለጸ

በዘንድሮው ዓመት መደበኛ ተማሪዎቻቸውን የ12ኛ ክፍል ፈተና ካስፈተኑ በመላው አገሪቱ ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች ውስጥ፤ በ39.2 በመቶው ያህሉ “አንድም ተፈታኝ” የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት እንዳላመጣ ትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ። ከመደበኛ ውጪ ያሉ ተማሪዎችን ያስተፈኑ ትምህርት ቤቶች ስሌት ውስጥ ሲገቡ፤ ምንም ተማሪ ያላለፈባቸው ትምህርት ቤቶች ብዛት ወደ 56 በመቶ ከፍ እንደሚል ሚኒስቴሩ አስታውቋል። የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ይህንን ያስታወቁት፤ በተያዘው ዓመት በሁለት ዙር የተሰጠውን የ12ተኛ ክፍል ፈተና ውጤት አስመልክተው ዛሬ አርብ ጥር 19፤ 2015 በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው። የክልል ትምህርት ቢሮ አመራሮች በተገኙበት በተሰጠው የዛሬው መግለጫ ላይ ሚኒስትሩ የፈተናውን ውጤት እና ተያያዥ መረጃዎችን ለጋዜጠኞች በዝርዝር ገልጸዋል። ፕሮፌሰር ብርሃኑ “የሚሳዝን” ብለው በጠሩት የዘንድሮው 12ኛ ክፍል ውጤት፤ ፈተናውን በትክክል ከወሰዱት 896,520 ተማሪዎች ውስጥ የዩኒቨርስቲ መግቢያ የሆነውን 50 በመቶ ውጤት ያመጡት፤ 3.3 በመቶው ብቻ መሆናቸውን አስታውቀዋል። በመላው አገሪቱ ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ያስፈተኗቸውን ተማሪዎች ሙሉ ለሙሉ ማሳለፍ የቻሉት ሰባት ትምህርት ቤቶች ብቻ መሆናቸውንም ሚኒስትሩ ተናግረዋል። ከእነዚህ ትምህርት ቤቶች ውስጥ “ደሴ” እና “ኦዳ” ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም የወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት በትምህርት ሚኒስትሩ መግለጫ በምሳሌነት ተጠቅሰዋል። ከግል ትምህርት ቤቶች ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ተማሪዎቹ ያለፉለት 41 ተማሪዎችን ያስተፈተነው ለባዊ አካዳሚ መሆኑንም አክለዋል። በሀገር አቀፍ ደረጃ በመደበኛ የትምህርት አሰጣጥ ስርዓት ያስተማሯቸውን የቀን ተማሪዎች ለፈተና ያስቀመጡ ትምህርት ቤቶች ብዛት 2,959

በ12ኛ ክፍል ፈተና ከ50 በመቶ በላይ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች፤ 3.3 በመቶ ብቻ መሆናቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ

  የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን ከወሰዱ ተፈታኞች ውስጥ ከ50 በላይ ውጤት ያመጡት፤ 3.3 በመቶ መሆናቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። ፈተናውን በትክክል ከወሰዱት 896,520 ተማሪዎች ውስጥ ከግማሽ በላይ ውጤት ያመጡት፤ 29,909 መሆናቸውን ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል። ሚኒስትሩ ይህን ያሉት በትላንትናው ዕለት ይፋ የተደረገውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤትን አስመልክቶ ዛሬ አርብ ጥር 19፤ 2015 በሰጡት መግለጫ ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ በዩኒቨርስቲዎች የተሰጠው የ12ተኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የተካሄደው በሁለት ዙር ነበር፡፡ ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 18፤ 2015 በተሰጠው በዚህ ሀገር አቀፍ ፈተና፤ የማህበራዊ ሳይንስ እና የተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ተማሪዎች ፈተናውን የወሰዱት በተለያየ ጊዜ ነው። ከሁለቱ የትምህርት ዘርፎች ውስጥ የተሻለ ውጤት የተመዘገበው በተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች መሆኑን ፕሮፌሰር ብርሃኑ በዛሬው መግለጫቸው ላይ ገልጸዋል። በተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ ፈተናውን ከወሰዱት 339,642 ተማሪዎች ውስጥ፤ ከ50 በመቶ በላይ ውጤት ያመጡት 6.8 በመቶው ናቸው። በማህበራዊ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ ደግሞ 556,878 ተማሪዎች ፈተናውን የወሰዱ ሲሆን፤ ከ50 በመቶ በላይ ውጤት ያመጡት 1.3 በመቶው ብቻ መሆናቸውን ፕሮፌሰር ብርሃኑ አስታውቀዋል። ከ50 በመቶ በላይ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ቁጥር አነስተኛ በመሆኑ የትምህርት ሚኒስቴር አዲስ አሰራር ለመከተል ማቀዱን ፕሮፌሰር ብርሃኑ ተናግረዋል። በዚህም መሰረት ከግማሽ በላይ ያመጡት 30 ሺህ ገደማዎቹ ተማሪዎች በሚቀጥለው ዓመት በቀጥታ ወደ ዩኒቨርስቲ ገብተው የአንደኛ ዓመት ተማሪ ይሆናሉ። ቀሪዎቹ ደግሞ የዩኒቨርሲቲዎችን የመቀበል አቅም መሰረት በማድረግ፤ የተ

የኢትዮጵያ ህገ መንግስት መሻሻል ላይ ምክክር ለማድረግ የሚያስችል መድረክ ማዘጋጀቱን

ኤፓክ፣መድረኩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ላይ፣ዋናው እና በአንደኛ ደረጃ ሊጠቀስ የሚገባዉ የኢትዮጵያ ችግር፣አሁን በሀገሪቱ ያለው ህገ መንግስት ነው ብሎ እንደሚያምን ገልጿል። የኢትዮጵያ ህገ መንግስት መሻሻል ላይ ምክክር ለማድረግ የሚያስችል መድረክ ማዘጋጀቱን የአሜሪካ ኢትዮጵያ የህዝብ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ-ኤፓክ አስታወቀ። የኤፓክ ሊቀመንበር፣አቶ መስፍን ተገኑ በተለይ ለዶይቸ ቨለ እንደገለፁት፣የውይይት መድረኩ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን፣ህገ መንግሥቱ እንዴት ይሻሻል በሚለው ዐሳብ ላይ ድምጽ እንዲኖራቸው ያስችላል። አቶ መስፍን እንደሚሉት፣ የሚካሄደው ውይይት መድረክ፣በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ ሊካሄድ በታቀደው ብሄራዊ ምክክር የመካፈል ዕድል እንዲያገኙ በሚል የተዘጋጀ ነው። "የዲያስፖራው ሚና ምድነው? ኢትዮጵያ አሜሪካውያን እንዲሁም፣በዓለም ላይ ያለው ጠቅላላው ኢትዮጵያዊ ሕዝብ ምንድነው ማበርከት ያለበት የሚለውን እና ያንንስ እንዴት ነዉ የሚያደርገዉ? የሚለው ነገር ካሰብንበት በኋላ፣ገንቢ በሆነ መንገድ ለምክክር ኮሚሽኑ የሚረዳ ስራ መስራት ይቻላል በሚል፣ያንንም በዚህ አጋጣሚ ዲያስፖራው በዓለም ላይ ያለውን ሐሳብ ያካተተ ጠቀም ያለ ሥራ ሰርቶ፣ ለምክክር ኮሚሽኑ በመላክ ለሚያደርጉት ሥራ አስተዋጽኦ ይሰጣል በሚል እምነት የተጀመረ ነው።" ኤፓክ፣ለእዚህ ፕሮጀክት አማካሪና አደራጅ ኮሚቴዎች በቅርቡ እንደሚያቋቋም አቶ መስፍን ጠቁመዋል። "ህግ የኮንስቲትውሽን እና እንደዚሁም ህግ አወጣጥን ልምድ ያላቸው የሶሻል ሳይንስ እንደዚሁም ይህን የመሳሰሉ ህገ መንግስት ማውጣት ላይ ሊረዱ የሚችሉ ኤክስፐርቲዝ ያላቸው ሰዎች የሚያካትት ኮሚቴ ይሆናል።እንግዲህ ይህም ኮሚቴ የሚቋቋመው በሰ

የገጠር መሬት ማሻሻያና የመሬት ባለቤትነት ጥያቄ በኢትዮጵያ

  በኢትዮጵያ ከቅርብ ወራት ወዲህ መሬትን በተመለከተ ጠንከር ያሉ የለውጥ ግፊቶች እየታዩ ነው፡፡ የለውጥ ግፊቱ እየመነጨ ያለው በራሱ በመንግሥት ተነሳሽነት መሆኑ ደግሞ፣ የዘርፉን ጥያቄ ሥር ነቀል በሆነ ሁኔታ ሊቀይር ይችላል የሚል ግምት እያሳደረ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መሬት በነባሩ የመሬት ሕግ እየተዳደረ መቀጠሉ ዘርፉን ጥቅም አልባ እንዳደረገው በቅርቡ ጠንከር አድርገው ተናግረው ነበር፡፡ መሬት በሕገ መንግሥቱ ‹‹የሕዝብና የመንግሥት›› ነው ቢባልም፣ ካድሬና ደላላ መሬትን በመቀራመት እየከበሩበት እንደሆነ መናገራቸውም ይታወሳል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መሬት ለታለመለት ዓላማ አለመዋሉን፣ እንዲያውም የሙስናና ምዝበራ ምንጭ መሆኑን አጠንክረው ማንሳታቸው አይዘነጋም፡፡ አያይዘውም ቢያንስ የከተማ መሬት ይዞታን ወደ ግል በማዞር፣ በመሬት ሥሪቱ ላይ ለውጥ ማድረግ እንደሚያስፈልግ አስገንዝበው ነበር፡፡ ይህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ደግሞ መንግሥት የመሬት ፖሊሲውን ለማስተካከል ትልቅ ፍላጎት እንዳለው ግምት እያሳደረ ነው፡፡ ይህ ግምት ሳይቀዘቅዝ እንደተሰማው ከሆነ ደግሞ የገጠር መሬትን መሸጥና መለወጥ የሚያስችል አሠራር ለመተግበር መንግሥት መዘጋጀቱ ታውቋል፡፡ በሁለተኛው አገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ውስጥ ተካቶ መቅረቡ በተነገረው በዚህ የገጠር መሬት አጠቃቀም ማሻሻያ ውስጥ ደግሞ፣ በግል ብቻ ሳይሆን በጋራ የመሬት ባለቤት መሆንን የሚፈቅድ አሠራር ተካቷል፡፡ መሬትን አስይዞ የመበደር አሠራርን ጨምሮ የመሸጥና የመለወጥ መብቶች መካተታቸው ተሰምቷል፡፡ ይህ ዕርምጃ መሬት በኢትዮጵያ ትርጉም ያጣ ሀብት ወይም የካፒታል ምንጭ መሆን ያልቻለ ንብረት ሆኗል እየተባለ ሲቀርብ ለቆየው ትችት፣ አንፃራዊ ምላሽ የሰጠ መሆኑን የሚናገሩ በርካቶች ናቸው፡፡ የ

የሲዳማ ባንክ ከየት ወዴት፤ ከባንኩ ፕሬዝዳንት ታደሰ ሐጢያ ጋር የተደረገ ውይይት

ለሰላም እሴት ግንባታ ጉልህ ድርሻ ያላቸውን ሀገር በቀል እውቀት ማበልፀግ እንደሚገባ ተመላከተ

ኢምፓክት ቱር በሐዋሳ || IMPACT TOUR 2022/15 - HAWASSA -- ክፍል 1

በሲዳማ ክልል ዝግ ግምገማ እንደሚካሄድ አፊኒ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘግቦ አይተናል

  በዛሬው ዕለት በሲዳማ ክልል ዝግ ግምገማ ይካሄዳል ፤ ====================================== አፊኒ ጥር 12 2015 ዓ.ም ሐዋሳ ባሳለፍነው ሳምንት በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የክልሉ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች በሃገራዊ፣ ወቅታዊና ክልላዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለሁለት ቀን መምከሩ ይታወሳል። በዚህ መድረክ መጀመሪያ ቀን በርካታ የክልሉ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፓለቲካዊ ጉዳዮችን የሚዳስስ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል። በውይይቱ በተለይ ህዝቡን ያስቆጡ ንግግሮችና ዘለፋዎች የክልሉ መንግስት በሚመራቸው ሚዲያዎች ጭምር ተሰራጭቷል። ከውይይቱ ተሳታፊዎች በዋናነት የህዝብን የስልጣን ሉዓላዊነት ላይ ያነጣጠሩና የህዝቡን የነፃነት ትግል ያላማከሉ ንግግሮች ተደምጠዋል። ከዚህ በተጨማሪ በክልሉ በተጨባጭ ካለው ችግር በተቃራኒ ግለሰቦችን ያነጣጠረ ስድብና ዘለፋ ብቻ ሳይሆን ዛቻ ጭምር ከመድረኩ መሪዎች እስከ ውይይቱ ተሳታፊዎች ተሰንዝረዋል። የክልሉ ፕረዚዳንት ከስልጣን እንደተነሳ ስለተነሳው ጉዳይ፣ እሳቸው ከስልጣን እንዳልተነሱና ከስልጣን ቢነሱ እንኳ የተሻለ ስልጣን እንደሚጠብቃቸው ገልፀው፣ ሀሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስበዋል። በውይይቱ ስራአጥነት አንዱ የመወያያ ነጥብ የነበረ ቢሆንም፣ አመራሩ ስራአጥነትን በውሸት ሪፖርት አድበስብሰው ለማለፍ ያደረጉት ነገር ብዙዎችን ያሳዘነ ነበር። በክልሉ ተመርቀው ከ4 ዓመት በላይ ስራአጥ ሆነው እየተንከራተቱ ያሉ ብዙ ወጣቶች ባሉበት፣ ብዙ የስራ ዕድል ተፈጥሯል ተብለው በተለይ በወረዳ አስተዳዳሪዎች የተነሳው ጉዳይ፣ መንግስት ለችግሩ መፍትሔ እንዳይሰጥ እስከማስተጓጎል የሚደርስ ነው። በሌላ በኩል የሐዋሳ ከተማ ከንቲባን በተመለከተ፣ የስልጣን ሽኩቻ ውስጥ እንደተገባና፣ የክልሉ ፕረዚዳንት

የመካነ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ሲዳማን ጨምሮ በተለያዩ ክልሎች ከ118 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የሚተገበር የልማት ስራ ይፋ አደረገች

ቤተ ክርስቲያኗ ከ118 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የሚተገበር የልማት ስራ ይፋ አደረገች አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ልማትና ማህበራዊ አገልግሎት ኮሚሽን በተለያዩ ክልሎች ላይ ተግባራዊ የሚሆንና በ118 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የልማት ስራ ይፋ አደረገች፡፡ በደቡብ ክልል አራት ወረዳዎችና በሲዳማ ሦስት ወረዳዎችን እንዲሁም በኦሮሚያ ተልተሌን መዓከል ያደረገ ፕሮጀክት በይፋ ስራ የማስጀመር ስምምነት ተደርጓል ። ተግባራዊ በሚደረጉት ፕሮጀክቶች ሦስት አብይ ተግባራት የሚከወን መሆኑን የተናገሩት በኮሚሽኑ የፕሮጀክቶች ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢቂላ አበያ ፥ በሰላም ግንባታ ፣በሴቶች አቅም ማጎልበትና የምግብ ዋስት ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራ መሆኑን አንስተዋል፡፡ ኮሚሽነር ዶክተር አበያ ዋቅወያ በበኩላቸው÷ ተቋሙ በሁሉም ክልሎች እየሰራ የሚገኝና በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ270 ፕሮጀክቶች በላይ በተግባር ላይ እንደሚገኙም ነው የገለጹት ። የ270 ፕሮጀክቶች አካል የሆኑ የተወሰኑ ፕሮጀክቶችን በሲዳማና ደቡብ ክልሎች ውስጥ ለመተግበር መፈራረማቸውን በመግለፅ በቀጣይም በሌሎችም ክልሎች ተግባራዊ የሚደረጉ ፕሮጀክቶች መኖራቸውን ጠቁመዋል፡፡ ፕሮጀክቱ ለሦስት አመታት የሚቆይ ሲሆን ÷ በርካታ ዜጎችን ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ምንጭ

በሲዳማ ክልል የትምህርት ጥራት ለማሻሻል የክልሉ ባለሃብቶች የገቡትን ቃል በመፈጸም ላይ ናቸው፤ የክልሉ መንግስትስ?

  በሲዳማ ክልል ለዘመንናት በነበርው የትኩረት ማነስ የተነሳ፣ በክልሉ ባሉ ትምህርት ቤቶች ትምህርታቸውን ተከታትሎ በአገር አቀፍ ደረጃ በሚሰጡት ፈተናዎች ላይ የሚቀመጡ ተማሪዎች ዝቅተኛ ውጤን በማስመዝገብ የክልሉን የትምህርት ጥራት ችግር በአደባባይ ማስጣታቸውን ተከትሎ፤ የክልሉ መንግስት በጀመረው የትምህርትን ጥራት ከመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ጀምሮ ለማስተካከል፣ በመማሪ ማስተማሪያ ህደቶችን ለማቀላጠፍ የሚያስችሉ ጥራት ያላቸው የመማሪያ ትምህርት ቤቶችን የመገንባት እና ለዚሁም ስራ ከመንግስት ብቻ ሳይሆን የክልሉ ባለሃብቶችን ተሳታፍ መድረጉን ተከትሎ፣ በርካታ የክልሉ ባለሃብቶች በራሳቸው ተነሳሽነት ትምህርት ቤቶችን በመገንባት ለህዝብ ለመስረከብ ቃል በመግባት ወደ ስራ መግባታቸው ይታወቃል። በክልሉ የትምህርት ጥራት ላይ የራሳቸውን አሻራ ለማሳረፍ ተነሳሽነትን ወስደው ወደ ስራ ከገቡት ባለሃብቶች መካከል፣ ባለሃብት ዱካሌ ዋቃዮ በሸበዲዮ ወረዳ በቦሮያ ምሪዴ ቀበሌ ሙሉ በሙሉ የግንባታ ወጭውን በመሸፈን ያሰሩትን የKindergarden (ለጀማሪ) ተማሪዎች የሚሆን ት/ቤት ፣ ጥራቱን በጠበቀ መልኩ ገንብተው ለአገልግሎት ዝግጁ ማድረጋቸውን ሰምተናል። ባለሃብት ካላ ዱካሌ በገቡት ቃል መስረት ትምህርት ቤቱን መስራታቸው ብቻ ሳይሆን፤ እንደ አንድ የክልሉ ተወላጆ በክልሉ ትምህርት ጥራት ላይ ይህን የመሰለ አሻራ ማሳረፋቸውን ከፍተኛ አድናቆት እና ክብር ይገባቸዋል። በሌላ መልኩ የክልሉ መንግስት ከባለሃብቶች በተጨማሪ የክልሉን የትምህርት ጥራትን በዘላቂነት ለማሻሻል የተለያዩ ተግባትን እና እርምጃዎችን ለመወሰድ ቃል የገባ ቢሆንም እስከ አሁን ድረስ ከንግግር ባለፈ የተሰራ ስራ አለመኖሩ ይታወቃል። ሰለዚህም የክልሉ ባለሃብቶች ቃላቸውን አክብረው ወደ ስራ ከመግባታቸው

Coffee Tour Sidaama

Cuuammate ayyaana Hawaasa

Sidaamu Televizhiine Qarra Odoo

በተያዘው የበጀት ዓመት የተጀመሩ ስራዎችን የማጠናቀቅና በሃዋሳ ሃይቅ ዙሪያ ጨለለቃ ተፋሰስ ላይ የአረንጓዴ ልማት ስራ በትኩረት ይከናወናል መባሉን ሰምተናል

  ተፋሰሶችን ከደለል ለመከላከል ከ1 ነጥብ 2 ሚሊየን ሄክታር በላይ መሬት ላይ የማልማትና የእንክብካቤ ስራ መከናወኑን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ በሚኒስቴሩ የስምጥ ሸለቆ ቤዚን አስተዳደር ጽህፈት ቤት ስር ባሉ ተፋሰሶች በተከናወኑ ስራዎች ላይ በሻሸመኔ ከተማ ውይይት ተካሂዷል፡፡ በመድረኩ የተገኙት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር የውሃ ሃብት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አብርሃ አዱኛ፤ ከተከናወኑት ስራዎች መካከል በስምጥ ሸለቆ ቤዚን ስር ባሉ አባያና ጫሞ፣ሃዋሳና ዝዋይ ሻላ ንኡስ ተፋሰሶች እንደሚገኙበት ጠቅሰዋል። ስራዎቹ የተከናወኑት ባለፉት አምስት ዓመታት እንደሆነ ገልጸው፤ በዚህም ውጤት እየመጣ መሆኑን በየአካባቢው ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች በተሰራው ጥናት ማረጋገጥ መቻሉን አስረድተዋል፡፡ በስራውም ወደ ሃይቆቹ የሚገባውን የደለል ክምችትና የጎርፍ አደጋ መቀነሱን እንዲሁም የተፋሰሱን ዙሪያ በማልማትም ህብረተሰቡ በተለያየ ስራ ተሰማርቶ ተጠቃሚ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በተፋሰሱ አካባቢ ባሉ ወረዳዎች የተከናወኑ ስራዎችን ማህበረሰቡ እንዲያስቀጥለው በማድረግ ተሞክሮውን ወደ ሌሎች አካባቢዎች የማስፋት ስራ በቀጣይ እንደሚከናወንም ገልጸዋል፡፡ እንደ ሃገር ሃይቆቹ በደለል እንዳይሞሉ ከመከላከል በተጨማሪ የሃይቆቹን ደህንነት በመጠበቅ የተለያዩ የልማት ስራዎች ማከናወን፣ ኢንደስትሪዎች ያሉባቸውን ተፋሰሶች ከብክለት ነጻ የማድረግና ጥራቱን የመጠበቅ ስራም እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡ በሚኒስቴሩ የስምጥ ሸለቆ ቤዚን አስተዳደር ጽህፈት ቤት ሃላፊ ዴቢሶ ዴዴ፤ በአባያና ጫሞ፣ሃዋሳና ዝዋይ ሻላ ንኡስ ተፋሰሶች ስር ባሉ 24 በሚደርሱ ወረዳዎች የልማትና እንክብካቤ ስራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል፡፡ በዚህም የአፈርና ውሃ ጥበቃ፣ሃይቆቹን ከደለል የመከላከል፣የአረንጓ

በሲዳማ ክልል ለጉዳት የተጋለጠ 116 ሺህ ሄክታር መሬት በአፈርና ውሃ እቀባ ልማት ይለማል

በሲዳማ ክልል በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ችግር ለጉዳት የተጋለጠ 116 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የአፈርና ውሃ እቀባ ልማት ስራ እንደሚካሄድ የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ አስታወቀ። በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች የተሳተፉበት የ2015 ዓ.ም ክልላዊ የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ንቅናቄ መድረክ ዛሬ በሀዋሳ ከተማ ተካሂዷል። በመድረኩ ላይ የቢሮው ኃላፊ አቶ መስፍን ቃሬ ፤ በክልሉ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ንቅናቄ “በቴክኖሎጂ የዘመነ ተፋሰስ ልማት ለብልጽግናችን” በሚል መሪ ቃል እንደሚካሄድ ገልጸዋል። በንቅናቄው በክልሉ የተራቆቱና የተጎዱ አካበቢዎችን ጥቅም ሊሰጡ ወደ ሚችሉበት ደረጃ ለማምጣት ትኩረት መሰጠቱን ተናግረዋል። በዚህ ረገድ በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ለጉዳት የተጋለጠ 116 ሺህ ሄክታር መሬት ከሰውና እንስሳት ንኪኪ በመከለል የአፈርና ውሃ እቀባ ልማት ስራ ለማካሄድ መታቀዱን አስታውቀዋል። እንዲሁም የስነ አካላዊ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ በነባርና አዳዲስ 646 ንዑስ ተፋሰሶች ላይ ለመስራት ግብ መያዙን ጠቅሰው፤ ለስኬታማነቱ የሰው ጉልበትና የስራ ጥራት ሳይጓደል በተቀናጀ መልኩ ርብርብ እንደሚደረግ አስረድተዋል። የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ንቅናቄው ለክልሉ ግብርና ምርት እድገት፣ለእንስሳት መኖ ልማት ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ለላቀ የህብረተሰብ ተጠቃሚነት የጎላ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ገልጸዋለ። ለ30 ተከታታይ ቀናት በሚከናወነው በዘንድሮው የተፋሰስ ልማት ንቅናቄ ላይ ከ1 ነጥብ 6 ሚሊዮን በላይ ህብረተሰብ እንደሚሳተፍ የሚጠበቅ መሆኑን ተናግረዋል። በንቅናቄው መድረክ ላይ የተገኙት የብልፅግና ፓርቲ የሲዳማ ክልል ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ፤ የዘንድሮው የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራን ለየት የሚያደርገው ሃገራዊ ሰላም በተረጋገጠ ማግስት መሆኑን ነው ብለዋል። የ

በሀዋሳ ከተማ የጥምቀት በዓል እየተከበረ ነው

  ሀዋሳ ጥር 11/2015 (ኢዜአ) በሀዋሳ የጥምቀት በዓል እየተከበረ ይገኛል ። በደብረ ምጥማቅ መድኃኔዓለም ቤተክስትያን እየተካሄደ ባለው የጥምቀት ክብረ በዓል ላይ የሲዳማ ፣የጌዴኦ ፣አማሮና ቡርጂ እንዲሁም የምዕራብ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ ተገኝተዋል ። እንዲሁም የሲዳማ ሀገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ መጋቤ ጥበባት ቀሲስ ሞላልኝ መርጊያ ሌሊት በማህሌትና ቅዳሴ ሥርዓት ሲያመሰግኑ ያደሩት የቤተክርስቲያኒቱ ሊቃውንትና በርካታ ምዕመናን ተገኝተዋል ። ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ ቃለ ምዕዳን እና ቡራኬ በሰጡበት ወቅት ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በባህረ ዮርዳኖስ የተጠመቀው የሰው ልጆችን የዕዳ ደብዳቤ በመደምሰስ ከባርነት ቀንበር ነፃ ለማውጣት ነው ብለዋል ። በክርስቶስ ያገኘነውን ነፃነታችንን ጠብቀን ለመኖር ራሳችንን መግዛትና ከክፋት ማራቅ ይጠበቅብናል ነው ያሉት ። ሠላምና ለሰው ልጆች ሁሉ ፍቅርን መስጠትን ዋንኛ የሕይወት መርህ ማድረግ እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል ። ሥልጣን፣ ዝናና ሀብትን በመጠቀም ሌሎችን ከመበደል መራቅ በተለይ ለተቸገሩ ዜጎች የሚራራ ልብ ያስፈልገናል ብለዋል ። በአቋራጭ ለመክበር ከሚደረግ ጥረት ከሌብነት ፣ ከሀሰት ፣ ከመለያየትና እርስበርስ ከመጨካከን ራስን ማቀብ ያሻል ነው ያሉት ። ኢትዮጵያ የቀደመ የአብሮነትና አንድነት እሴቶቿ ተጠብቀው ፅኑ ሀገር ሆና እንድትቀጥል እርስ በርስ ከመገፋፋትና ከመጠላላት ይልቅ መከባበርና መዋደድ እንደሚገባም አስገንዝበዋል ። የሲዳማ ሀገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ መጋቤ ጥበባት ቀሲስ ሞላልኝ መርጊያ የጥምቀት በዓል ከሐይማኖታዊ አስተምህሮቱ ባሻገር የኢትዮጵያን አንድነትና ትሥሥር የሚያጠናክሩ ማህበራዊ ኩነቶች በውስጡ መያዙንጠቅሰዋል ። የሀገርን ገፅታ በበጎ መልኩ በማጉላት

የረዳት ፕሮፌሰር ሀርቃ ሀሮዬ ስርዓተ ቀብር ተፈፀመ

ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር እና የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የህግ መምህር የነበሩት ረዳት ፕሮፌሰር ሀርቃ ሀሮዬ ኦዳ ቀብር ነው ዛሬ በቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የተፈፀመው። ረዳት ፕሮፌሰር ሀርቃ ሀሮዬ ስርዓተ ቀብር ላይ የፌዴራል እና የሲዳማ ክልል ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችን ጨምሮ የተለያዩ ወዳጅ እና ዘመዶቻቸው ተገኝተዋል። ረዳት ፕሮፌሰር ሀርቃ ሀሮዬ ለሲዳማ ነፃነት ሲታገሉ የኖሩ በዚህም ለበርካታ አመታት ለዚህ ትግል አስተዋፆኦ ሲያበረክቱ የኖሩ እና ይህን በመወጣታቸውም እስራት እና እንግልት የደረሰባቸው ምሁር ነበሩ። ረዳት ፕሮፌሰር ሀርቃ በቆይታቸው እና በትምህርት ዘመናቸው በህግ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪያቸውን የሰሩም ሰው ነበሩ። በትምህርት ቆይታቸውም የረዳት ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ያገኙት ሀርቃ ሀሮዬ በደረሰባቸው አፈናን የመንግስትን አቋም በመቃወም እምቢ በማለት ከኬኒያ እስከ ታንዛኒያ የእግር ጉዞ ማድረጋቸውን የህይወት ታሪካቸው ያስረዳል። በተለይ በደርግ ዘመን ለ3 ተከታታይ አመታት እና በአጠቃላይ ከ10 ጊዜ በላይ እስራትን የቀመሱ ሰውም ነበሩ። በዚህም በቅጽል ስማቸው "ማስተር እስር" ይባሉ እንደነበረ ይነገርላቸዋል። የረዳት ፕሮፌሰር ሀርቃ ሀሮዬ የትግል ህይወት እንደሚያመለክተው ከሆነ በሲዳማ ጠቅላይ ግዛት የነበረውን የንፁሀንን መረሸንን ለማስቆም ትልቅ ተጋድሎ ያደረጉ ጀግና እንደነበሩም ነው የህይወት ታሪካቸውን የሚያስረዳው ቃል የሚገልፀው። ረዳት ፕሮፌሰር ሀርቃ ሀሮዬ ዕድሜ ልካቸውን ለሲዳማ እንዲሁም ለኢትዮጵያ የታገሉ ሰው ናቸው በማለትም ነው ዛሬ በቀብር ስርዓታቸው ላይ የተገለፀው። ረዳት ፕሮፌሰር ሀርቃ ሀሮዬ የሦስት ወንድና የሁለት ልጆች አባትም ነበሩ። ረዳት

ፓርላማው በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚቀርቡለትን ሹመቶች በነገው ስብሰባው ሊያጸድቅ ነው 

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የሚያቀርቧቸውን የአስፈጻሚ አካላትን ሹመት ለማጽደቅ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ ማክሰኞ ስብሰባ ሊያደርግ ነው። ሁለት የፓርላማ አባላት የነገው አጀንዳ “ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚያቀርቧቸውን ተሿሚዎች ሹመት ማጽደቅ” መሆኑን የሚገልጽ መልዕክት እንደደረሳቸው ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። የተወካዮች ምክር ቤት ለመገናኛ ብዙሃን ዛሬ ባሰራጨው መረጃም ነገ ከቀኑ 7:30 ጀምሮ በሚካሄድ ስብሰባ ፓርላማው በጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረቡ ሹመቶችን መርምሮ እንደሚያጸድቅ አስታውቋል። አንድ ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ የፓርላማ አባል፤ በምክር ቤቱ ጽህፈት ቤት በኩል የተላለፈው መልዕክት “ማንም የምክር ቤት አባል እንዳይቀር” የሚል ማሳሰቢያ መያዙን አክለዋል። አራት የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ካቢኔ አባላት ከትላንት በስቲያ ቅዳሜ ከኃላፊነት መነሳታቸው ይታወሳል። ከኃላፊነት ተነስተው “በክብር ሽኝት” እንደተደረገላቸው የተገለጹት ሚኒስትሮች፤ የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስተሯ ዳግማዊት ሞገስ፣ የማዕድን ሚኒስትሩ ታከለ ኡማ እና የግብርና ሚኒስትሩ ኡመር ሁሴን ናቸው። ከዚህ በተጨማሪ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ኃላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትሩ አቶ ተፈሪ ፍቅሬም እንደዚሁ ከኃላፊነታቸው መሰናበታቸው መገለጹ ይታወሳል። ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ከሶስት ሳምንት በፊት ሹመት ከሰጧቸው አስራ አራት አምባሳደሮች መካከል አቶ ኡመር ሁሴን እና አቶ ተፈሪ ፍቅሬ ይገኙበታል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በሚኒስትር ደረጃ ለመጨረሻ ጊዜ ሹመት የሰጡት ከአምስት ወራት በፊት ባለፈው ዓመት ነሐሴ ላይ ነበር። በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሹመት የተሰጣቸው፤ አቶ ላቀ አያሌውን ተክተው የገቢዎች ሚኒስትር የሆኑት ወይዘሮ አይናለም ንጉሴ ናቸው። አቶ ላ

የኢንዱስትሪ እምርታ በሲዳማ ክልል

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለሀዋሳ ሜሪ ጆይ አረጋውያን ማዕከል የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በሀዋሳ ሜሪ ጆይ አረጋውያን ማዕከል ለተጠለሉ አረጋውያን ማዕድ በማጋራት የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ። የቁሳቁስ ድጋፉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሽፈራው ተሊላ ለሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ መስራችና ሥራ አስኪያጅ ሲስተር ዘቢደር ዘውዴ አስረክበዋል። አገልግሎቱ ያደረገው ድጋፍ 150 ጥንድ አንሶላና የሌሊት ልብስ፣ 75 ሊትር የምግብ ዘይትና የንጽህና መጠበቂያ ቁሶች መሆናቸውን በርክክቡ ወቅት ተገልጿል። በተጨማሪም አገልግሎቱ በማዕከሉ ለጠለሉ 120 አረጋውያን ማዕድ አጋርቷል። የአገልግሎቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሽፈራው ተሊላ በወቅቱ እንደገለጹት፤ አገልግሎቱ ከአረጋውያን ጎን መሆኑን ለማሳየት የተደረገ ድጋፍ መሆኑን ጠቁመው በተለይ በማዕከሉ ያለውን የኤሌክትሪክና ትራንስፎርመር ችግር ለመፍታት ቃል ገብተዋል። እኛ ኢትዮጵያውያን እርስ በእርስ መደጋገፍ እንደምንችል ማዕከሉን በጎበኘንበት ወቅት ተረድተናል ያሉት አቶ ሽፈራው፤ ይህ ተግባር እንዲስፋፋ የሁሉንም ተሳትፎ እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል። ሲስተር ዘቢደር በአገልግሎቱ ለተደረገው ድጋፍ በአረጋውያን ስም አመስግነዋል። በተለይ ማዕከሉ በኤሌክትሪክ ችግር ምክንያት በተለያዩ ለጋሽ አካላት የተገኙ የህክምናና ሌሎችም ማሽኖች ካለ አገልግሎት መቀመጣቸውን አስታውቀዋል። በዚህ ረገድ ያለው ችግርን ለማቃለል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አጋርነታቸውን በማሳየታቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል። አሁን ላይ ማዕከሉን ለማጠናከር የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር፣ በከተማዋ የሚገኙ የመንግሥትና የግል ሴክተሩ የጤና ባለሙያዎች እንዲሁም ከሲዳማ ክልላዊ መንግስት ጋር በቅርበት እየሰሩ መሆናቸውንም አብራርተዋል። ኢዜአ  

የኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ አራት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣ ምርት ለወጪ ንግድ ገቢ ለማበርከት አቅዷል፣ ሲዳማስ?

የኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ አራት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ምርት ለወጪ ንግድ ገቢ ለማበርከት አቅዶ እየሠራ መሆኑን አስታወቀ። ወጪ ንግዱን በአግባቡ መምራት የአገርን ሉዓላዊነትን ማስከበር እንደሆነም ተገልጿል፡፡ የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ክልሉ በወጪ ንግድ ዙሪያ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት ከባለሀብቶች እና ባንኮች ጋር ትናንት ውይይት ሲያደርጉ እንደገለጹት፤ የወጪ ንግዱን በአግባቡ በመምራት በያዝነው ዓመት እንደ አገር አራት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ዶላር ከወጪ ንግድ ለማግኘት ታቀዶ እየተሠራ ነው፡፡ የአገር ውስጥን ምርት በከፍተኛ ዋጋ ገዝተው በመሰብሰብ ለውጭ ገበያ አቅርበው በአነስተኛ ዋጋ በመሸጥ የሚያገኙትን ዶላር የውጭ ምርቶችን ወደ አገር ውስጥ በማስገባት በከፍተኛ ዋጋ የሚሸጡ ባለሀብቶች የውጭ ንግዱ ፈተና መሆናቸውን ገልጸው፤ ይህ ህገ ወጥ ድርጊት ሊቆም እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ በቁም እንስሳት ምርት ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ቀዳሚ ብትሆንም ጎረቤት አገራት በዘርፉ ከፍተኛ ላኪና ትርፋማ መሆናቸው ሲታይ የወጪ ንግዱ በአግባቡ ላለመመራቱ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡ እንደ አገር ለውጪ ንግድ ከሚቀርቡ ምርቶች ብዛት አንጻር የሚገኘው ገቢ ተመጣጣኝ አይደለም ያሉት ፕሬዚዳንት ሽመልስ፤ አገር ከወጪ ንግዱ ማግኘት የሚገባትን ጥቅም እንድታገኝ መንግሥት እና ባለሀብቱ ተባብረው መሥራትና ችግሮችን መፍታት አለባቸው ብለዋል፡፡ የክልሉ መንግሥት በዘርፉ የሚታዩ ተግዳሮቶችን ለመፍታት በአቅርቦት ዙሪያ ምርቶቹ በፍጥነትና በጥራት ለማምረት በመስኖና በሜካናይዜሽን ላይ ትኩረት አድርጎ እየሠራ መሆኑን ገልጸው፤ ባለሀብቱም አገሩን ለመቀየር ከመንግሥት ጋር ተቀራርቦ ያለውን ችግር በመፍታት ወጪ ንግዱን ገቢ ለማሳደግ በባለቤትነት ስሜት እንዲሠራ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ መንግሥ

በሲዳማ ክልል የተቋቋመው የፀሬ-ሙስና ኮሚቴ ከህብረተሰቡ መረጃ በመስጠት እንድተባበረው መጠየቁን ሰምተናል

በሲዳማ ክልል የተቋቋመው የፀሬ-ሙስና ኮሚቴ ከህብረተሰቡ መረጃ መቀበያ መንገዶችን ይፋ አደረገ። ሲዳማ ብ/ክ/መ/ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጥር 05/2015 ዓ.ም ሀዋሳ። የኮሚቴ ሰብሳቢ እና የሲዳማ ክልል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ቢሮ ኃላፊ አቶ ማቶ ማሩ ሙስና ልማትና መልካም አስተዳደር በሀገርቱ እንዳይኖር ከማድረግ ባሻገር ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ቀውስ የሚያስከትል በመሆኑ ሁላችንም በጋራ ልንከላከል ያስፈልጋል ብለዋል። ህብረተሰቡ ተሳትፎ ከለለ ሙስናን መከላከል የማይታሰብ ነው ያሉት አቶ ማቶ ማሩ የትኛውም የሙስና ድርግት የተፈፀመውን ለመጠቆም እንድመች ቢሮዎችን ከማደራጀት ጀምሮ የስልክ ቁጥሮችን ይፋ መደረጉን ተናግሯል። አምስት ዋና ኮሚተና ከሥራቸው ንዑስ ከሚቴ የተደራጀ ሲሆን በአካል ቀርበው ጥቋማ ለሚሰጡት በጠቅላይ አቃቤ ሕግ ቢሮ ፣ በፀሬ-ሙስና ኮሚሽን ቢሮ ፣ በክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ቢሮ እና በበንሳ ዳዬ በሚገኘው በንሳ አከባቢ ከፍተኛ አቃቤ ህግ ጽ/ቤት በአካል ቀርበው ወይም በስልክ ቁጥር 0462125106/0462125107 በመጠቀሙ ጥቆማ መስጠት እንደሚቻል ገልጸዋል። ጥቆማ የሰጡ ግለሰቦች ምስጥራዊነቱ የተጠበቀ ነው ያሉት የኮሚቴ ሰብሳቢ በቅርቡ በሌሎች ዞን ከተሞች የጥቆማ ቢሮዎች እንደሚዘጋጅ ተናግረዋል።

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የጤናው ዘርፍ መዋቅርና የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ የሜሪጆይ የአረጋዊያን ማዕከልን ለማገዝ ቃል ገቡ

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የጤናው ዘርፍ መዋቅርና የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ የሜሪጆይ የአረጋዊያን ማዕከልን ለማገዝ የተለያዩ ድጋፎችን ለማድረግ ቃል የገቡ ሲሆን፤ በዚሁም መሰረት በዚህ አመት ወደ 4 መቶ ሺ ብር የሚያወጣ መድሃኒት ለመስጠት፤ እንድሁም በቋምነት ባለሙያ ለመመደብ ቃል መግባታቸውን ሰምተናል።   

በሲዳማ ክልል የህዝብ ሀብት በእቅድ እንደምመዘበር ተገለፀ

የሲዳማ ክልል በሁለት አመት ውስጥ 576 በሙሲና የተዘፈቁ ግለሰቦችን ተጠያቂ ማድረግ መቻሉን እና ከ22 ሚሊዮን ብር በላይ የተመዘበረ ሃብት ማስመለስ መቻሉን ካላ ማቶ ማሩ ተናገሩ። ከዚህ ባሻገር፣ በሲዳማ ክልል የህዝብ ሀብት በእቅድ እንደምመዘበር ተገለጻል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ በክልሉ ልመዘበር የታቀደ ከ18 ሚሊዮን በላይ ብር ተመላሽ ማድረጉን የክልሉ ጸረ ሙስና ኪሚቴ ሰብሳቢ መናገራቸውን ሰምተናል። ለዝርዝሩ የደቡብ ክልል ቲቪ ዘገባን ይመልከቱ።

የሱማሊ ላንድ የሐርጌሳ ከተማ ልዑካን ቡድን አባላት በሐዋሳ ልምድ ልውውጥ አደረጉ

ልዑካን ቡድን አባላቱ በሐዋሳ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም ደማቅ አቀባበል ከተደረገላቸው በኋላ በሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ በቢሮአቸው ልዩ ገለፃም ተደርጎላቸዋል። በዚህም ከንቲባ ፀጋዬ ቱኬ እንግዶቹን በቢሮአቸው ተቀብለው ስለ ከተማዋ ያለውን የልማት ስራ ያስረዱት የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ የሐዋሳ ከተማን ተመራጭነት እና ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሳየች ያለችውን ተመራጭነት የሚያመላክት እንደሆነ አብራርተውላቸዋል። ከእንግዶቹ ጋር ከንቲባ ፀጋዬ ቱኬ በነበራቸው ቆይታ የሐዋሳ ከተማ በበርካቶች የጉብኝት መዳረሻ እንደሆነች የገለፁት ከንቲባው ለዚህም አስተዳደሩ በየ በጀት አመቱ እያከናወናቸው የልማት ስራዎች ውጤት እንደሆነም ገልፀዋል። ይህ አይነቱ የልማት ስራ በቀጣይ የሐዋሳን ተመራጭነት ለአለም ለማሳየት በይበልጥ ይሰራል ያሉት ከንቲባ ፀጋዬ ቱኬ በተለይም በከተማ ውበት፣ ፅዳትና አረንጓዴነት ላይ የተከናወኑ የልማት ስራዎች ከተማዋን ተጠቃሽ ያደርጋታል በማለትም ነው ለሐርጌሳ ከተማ ከንቲባ እና የልዑካን ቡድኑ የገለፁት። ከሶማሊ ላንድ የመጡ እንግዶችም በቆይታቸው የተለየ ልምድ ሊቀስሙ እንዲችሉ ተዟዙረው የከተማዋን የልማት ስራዎች ከከንቲባ ፀጋዬ ቱኬ ጋር መጎብኘትም ችለዋል። ልዑካን ቡድኑን በሐዋሳ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ድረስ በመገኘት አቀባበል ያደረጉት የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባና የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ሚልክያስ ብትሬ ናቸው። የሶማሊ ላንድ የሐርጌሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አብዱልከሪም አህመድ በበኩላቸው የሐዋሳ ከተማ ውበት እና ፅዳት ከሀገራቸው ከተማ ከሆነችው የሐርጊሳ ከተማ ጋር የሚያመሳስላቸው በርካታ ነገሮች እንዳሉም ገልፀዋል። በዚህም አሉ ከንቲባው በንግግራቸው በሐ

የሴንተራል ሐዋሳ ሆቴል ባለቤተ ወ/ሮ አማረች ዘለቀ የቀብር ስነ ሥርዓት በሐዋሳ ቅዱስ ገብረኤል ቤተክርስቲያን ተፈጸመ

የተለያዩ ክልሎች ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ ጉዳይ ላይ እየመከሩ ነው

(ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ እና የሲዳማ ክልሎች ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ እየተወያዩ ነው፡፡ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ፖለቲካዊ ሁኔታዎች እንዲሁም በሠላምና ፀጥታ አዝማሚያዎች ላይ በሀዋሳ ከተማ እየመከሩ ነው። ክልላዊ ወቅታዊ ፖለቲካዊ አዝማሚያዎችን እና የሠላምና የፀጥታ ሁኔታዎችን አመላከች መነሻ ሀሳብ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳ ቀርቧል። የአማራር መድረኩ በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ፖለቲካዊ አዝማሚያዎች ላይ የጋራ አረዳድ በመፍጠር የተጀመረው የሠላም፣ የልማትና የዲሞክራሲ ግንባታ ሂደቱ እንዲጠናከር ፋይዳዉ የጎላ መሆኑ ተገልጿል ። በተመሳሳይ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ እና የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ የውይይት መነሻ ሃሳቦችን አቅርበዋል፡፡ በውይይት መድረኩ በሀገራዊ፣ ወቅታዊና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ አመራሮች ዝርዝር ውይይት እንደሚያካሂዱና የጋራ መግባባትላይ እንደሚደርሱ ይጠበቃል፡፡ በዚህም የህዝብ ተጠቃሚነት፣ ሀገራዊ አንድነትና ወንድማማችነትን በጋራ አጠናክሮ ለማስቀጠል የሚያስችል አቅጣጠጫ ይቀመጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ የርዕሰ መስተዳድሩ ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡ የውይይቱ ተሳታፊ አመራሮች ሀገራዊ ለውጡና የሰላም ስምምነቱ ዘላቂ እንዲሆን የበኩላቸውን ኃላፊነት እንደሚወጡ አረጋግጠዋል፡፡ በተመሳሳይ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ፈተናዎችን በመሻገር ድሎቻችንን እናፀናለን” በሚል መሪ ቃል በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ውይይት በመካሄድ ላይ ነው። በውይይቱ የክልል ፣የዞን የወረዳ እና የከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች የተገኙ ሲሆን በወቅታዊ ፖለቲካዊና የጸጥታ ጉዳ

Hawassa Industrial Park Secures USD 32 Million From Exports

Hawassa Industrial Park secured USD 32 million from goods exported to the international market within the past three months. The park which is located 275 kilometers south of Addis Ababa was inaugurated in 2016 as the first industrial park of the country. It started operation the same year with 52 factory sheds which were rented out mostly to foreign companies. Industrial park companies generated USD 357 million from the sale of goods and created jobs for 57,000 citizens during the 2021/2022 fiscal year. They were able to export goods worth USD 196 million while supplying goods to the local market substituting import products which amounted to USD 161 million. Source: Fana BC, Ethiopian News Agency, Industrial Parks Development Corporation (IPDC) Image source: IPDC

Hong Kong manufacturer leaves Bahir Dar Industry Park over AGOA market loss

-It is looking for buyers to sell machineries – It laid off over 700 workers after paying compensation Hop Lun, a Hong Kong-based company, has departed Bahir Dar Industry Park after incurring significant losses and losing market as a result of Ethiopia’s suspension from the Africa Growth Opportunity Act (AGOA). It is a major blow for officials, who were already under pressure as a result of the departure of factories from Hawassa Industrial Park for the same reason. Founded in 1992, Hop Lun, which has a presence in Bangladesh, China and Indonesia, joined the Ethiopian market three years ago. Its intention was to make Bahir Dar Industrial Park an exemplary and a leading industrial park like Hawassa Industrial Park. In 2019, the firm leased all eight industrial sheds that the government had erected in the Park after signing a Memorandum of Understanding (MoU) with the Ethiopian Investment Commission (EIC). Four of the eight sheds were converted into production facilities, and Hop immedia

የቀድሞ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልና የፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ሀርቃ ሀሮዬ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

  የቀድሞ የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የነበሩት አቶ ሀርቃ ሀሮዬ ኦዳ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። አቶ ሀርቃ ከ1992 እስከ 1997 እንዲሁም ከ1998 እስከ 2002 ዓ.ም ለሁለት የምክር ቤት ዘመናት የኢትዮጵያ ፓርላማ አባል በመሆን አገልግለዋል። በፍትህ ሚኒስቴር በሚኒስትርነት እንዲሁም በሲቪል ሰርቪስ፣ በአዲስ አበባ እና በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲዎች ደግሞ በመምህርነት አገልግለዋል። አቶ ሀርቃ ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ጥር 7 ቀን 2015 ዓ.ም በ74 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። የአቶ ሀርቃ ሥርዓተ ቀብር ከነገ በስቲያ ጥር 9 ቀን 2015 ዓ.ም በሐዋሳ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ቤተሰቦቻቸውና ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 6:00 ሰዓት ላይ የሚፈፀም መሆኑን ከኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአቶ ሀርቃ ሀሮዬ ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ሀዘን ገልፆ፤ ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን ተመኝቷል። የወራንቻ ድረ ገጽ አዘጋጅም ለካላ ሀርቃ ሀሮዬ ቤተሰቦቻቸው እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ይመኛል።

«ኢትዮጵያ በአካባቢ ጥበቃ ለዓለም ተሞክሮ የሚሆኑ ተግባራት አከናውናለች»ዶክተር ፍጹም አሰፋ የፕላንና ልማት ሚኒስትር

ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን በመከላከል ረገድ ለዓለም ተሞክሮ የሚሆኑ ተግባራትን እያከናወነች መሆኑን የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አሰፋ ገለጹ። ሚኒስትሯ «እድገትን ከአካባቢ ጋር ተስማሚ ማድረግና ከአኗኗር ዘይቤዎች ጋር ማመጣጠን» በሚል መሪ ቃል በሕንድ በተዘጋጀ የትብብር ጉባኤ ላይ በበይነመረብ ሲሳተፉ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ተፅእኖዎች ምላሽ ለመስጠት ፖሊሲዎችን በማውጣት፣ ተቋማትን በማጠናከር፣ የልማት ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት እና ፕሮጀክቶችን በመተግበር ላይ ነች። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2019 በተጀመረው የኢትዮጵያ አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በአራት ዓመታት 25 ቢሊዮን ችግኞች የተተከሉበት መሆኑን የገለጹት ዶክተር ፍጹም፤ አረንጓዴ እና አየር ንብረትን የሚቋቋም ማኅበረሰብ እየፈጠረ ያለ መሆኑን አንስተዋል። ከ20 ሚሊዮን በላይ ዜጎች እና የኢትዮጵያ ወዳጆች የተሳተፉበት 25 ቢሊዮን ችግኞችን የመትከሉ ተግባርም ከ700 ሺህ በላይ ለሆኑ ዜጎች በተለይም ለሴቶችና ለወጣቶች አረንጓዴ የሥራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን ወደ 25 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አስገኝቷል ብለዋል። ዓለም በየጊዜው በሚቀያየረው የአየር ንብረት ለውጥና የአካባቢ መራቆት ብዙ እየተፈተነች መሆኑን ያነሱት ዶክተር ፍጹም፤ በተለይ በማደግ ላይ ያሉ አገራት እና አፍሪካ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰባቸው መሆኑን አንስተዋል። ለታዳሽ ኢነርጂ ዘርፍ ልማት ኢትዮጵያ ከፍተኛ ትኩረት መስጠቷን ያነሱት ዶ/ር ፍጹም የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ምንጮች በዋናነት ከታዳሽ ኃይል ቢሆንም የኃይል ተደራሽነት ከ50 በመቶ በታች መሆኑን አብራርተዋል። ኢትዮጵያ በጣም ተጋላጭ ከሆኑ አገራት አንዷ መሆኗን ያነሱት ሚኒስትሯ የማህበረሰቡን የመላመድና የመቋቋም አቅም ለማሻሻል ተግባራዊ እርምጃዎች እየ