የቀድሞው የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) ከፍተኛ አመራር የነበሩት ዶ/ር አለምነው መኮንን የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙ። ዶ/ር አለምነው የኢንተርፕራይዝ ልማቱ ዳይሬክተር ሆነው የተሾሙት፤ ተቋሙን ላለፉት 10 ወራት በዋና ዳይሬክተርነት ሲመሩ የነበሩት አቶ ብሩ ወልዴ ከኃላፊነታቸው በመልቀቃቸው ምክንያት ነው። የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ባለፈው ዓመት መስከረም ወር በአዲስ መልክ ከተዋቀሩ የፌደራል የመንግስት መስሪያ ቤቶች አንዱ ነው። አዲሱ ተቋም በአዋጅ የፈረሰው የፌደራል አነስተኛ እና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች ልማት ኤጀንሲ መብት እና ግዴታዎች ተላልፈውለታል። መስሪያ ቤቱ በአዲስ መልክ ከተዋቀረ ከአራት ወራት በኋላ በዋና ዳይሬክተርነት የመምራት ኃላፊነት የተረከቡት፤ የሲዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽንን ከምስረታው ጀምሮ በዋና ስራ አስኪያጅነት ሲያስተዳድሩ የቆዩት አቶ ብሩ ወልዴ ነበሩ። አቶ ብሩ እስከ ትላንት ጥቅምት 2፤ 2015 በስራ ገበታቸው ላይ እንደነበሩ የስራ ባልደረቦቻቸው ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። ከኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የዋና ዳይሬክተርነት ኃላፊነታቸው “በገዛ ፍቃዳቸው” የለቀቁት ከዛሬ ጥቅምት 3፤ 2015 ጀምሮ መሆኑን አቶ ብሩ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። አቶ ብሩ ለዚህ ውሳኔ የበቁት “በግል ምክንያት” መሆኑን ከመግለጽ ባሻገር በጉዳዩ ላይ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል። የዋና ዳይሬክተሩን ከኃላፊነት መልቀቅ የኢንተርፕራይዝ ልማት መስሪያ ቤቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልፈታህ የሱፍ አረጋግጠዋል። በተሰናባቹ ኃላፊ ምትክ ዶ/ር አለምነው መኮንን መሾማቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ለተቋሙ መድረሱንም ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጸዋል። በጠቅላይ
It's about Sidaama!