የኢትዮጵያ ቡና በጥራት፣ በተወዳዳሪነትና በዋጋ አስደናቂ ውጤት እየተመዘገበበት መሆኑን በኢትዮጵያ የካፕ ኦፍ ኤክሰለንሲ አስተባባሪ ገለጹ። በመጀመሪያውና ሁለተኛው የባለ ልዩ ጣዕም (የካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ) ውድድር የኢትዮጵያ ቡና አስደናቂ ውጤት የተገኘበት መሆኑ ይታወቃል። የካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ ሶስተኛው ውድድር የቡና እና ሻይ ባለስልጣን ከአሊያንስ ኮፊ ኤክሰለንስና የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (ዩኤስኤይድ) ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ሲሆን የኢትዮጵያ ቡና አሸናፊ ሆኗል። በኦንላይን ጨረታ በተከናወነው መርሃ ግብር አንድ ኪሎ ቡና 884 ዶላር ከ10 ሳንቲም ወይም 47 ሺህ 236 ብር ከ23 ሳንቲም ተሽጧል። በዚህም የባለ ልዩ ጣዕም ቡና ቅምሻ ውድድር ጥራቱ የተጠበቀ ቡና ለዓለም አቀፍ ገበያ ለማቅረብ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረገ መጥቷል። ባለፈው አመት በተካሄደው ውድድር ከ22 አገራት 170 ገዥዎች ተመዝግበው የኢትዮጵያን ቡና ለ11 ሰአታት በመጫረት አንድ ኪሎ ግራም ቡና 47 ሺህ 236 ብር ከ23 ሳንቲም ተሽጧል። የኢትዮጵያ ቡና በውድድሩ በሁሉም መልኩ የዓለምን ቀልብ እየገዛ መሆኑን የገለጹት በኢትዮጵያ የካፕ ኦፍ ኤክሰለንሲ አስተባባሪ ቅድስት ሙሉጌታ፤ የኢትዮጵያ ቡና በጥራት፣ በተወዳዳሪነትና በዋጋ አስደናቂ ውጤት እየተመዘገበበት መሆኑን ተናግረዋል። በካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ መሳተፍ የቡና ገዥዎች የውድድሩ አሸናፊ የሆነው አምራች አርሶ አደር ወደ ሚገኝበት አካባቢ ሄደው እንዲያበረታቱና ሌሎችም ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዕድል ይፈጥራል ብለዋል። በሦስተኛውን ዙር ውድድድር አሸናፊ የሆኑት አርሶ አደር ለገሠ በጦሳ፤ 1 ኪሎ ግራም ቡና 47 ሺህ 236 ብር በመሸጥ በድምሩ 479 ኪሎ ግራም 22 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር መሸጥ ችለዋል። ከ23 አገራት የተወጣጡ 170 ገዢዎች ተሳታፊ በ
It's about Sidaama!