Skip to main content

Posts

Showing posts from June, 2022

የሲዳማ ክልል ቤቶች አስተዳደርን የተመለከተ ወቅታዊ መረጃ

አቤት የሲዳማ ክልል ወሬዎች

የእነ ደስታ ኩታ ገጠም እርሻ በተዛባ አረዳድና መንገድ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን በተደጋጋሚ ተናግረን ነበር

  ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሰፊው በሥራ ላይ እየዋለ የሚገኘው የኩታ ገጠም የእርሻ ልማት በተዛባ አረዳድና አተገባበር እየሄደ መሆኑ ተነገረ፡፡ የኢትዮጵያ ግብርና ባለሙያዎች ማኅበር ዓመታዊ ጉባዔ ላይ የኩታ ገጠም እርሻ ልማት በሰፊው የሚገመግም ጥናት ቀርቧል፡፡ በዚህ ጥናት እንደተመለከተውም፣ የእርሻ ልማቱ የገበሬውን ፍላጎት በሚጋፋ መንገድ መተግበሩ ለዘርፉ አደጋ ነው ተብሏል፡፡ አርሶ አደሩ የራሴ የሚለው የግል መሬት ሳይኖረውና ማምረት የሚፈልገውን የምርት ዓይነትና መጠን በራሱ ሳይወስን ይዞታውን ለኩታ ገጠም እርሻ ካላዋለ መባሉ፣ የፖሊሲውን ዓላማ የሚያስት መሆኑ በጥናቱ ተመልክቷል፡፡ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር ኩታ ገጠም እርሻን አስገዳጅ አሠራር ማድረጉ፣ ከ1972 ዓ.ም. የኮሙኒስታዊው ደርግ አሠራር ጋር ሊያመሳስለው የሚችል ነው በሚልም ፖሊሲው ተተችቷል፡፡ ባለፈው ሳምንት ተካሂዶ በነበረው የግብርና ባለሙያዎች ማኅበር ዓመታዊ ጉባዔ ላይ የአነስተኛ ባለይዞታ አርሶ አደሮች ለገበያ ተኮርና ዘመናዊ ግብርና ያላቸውን ሚና የተመለከተ ጥናት፣ የግብርና ኢኮኖሚክስ ባለሙያው ደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) አቅርበው ነበር፡፡ በዚህ ጥናታቸው የችብቻቦ እርሻ ስለሚሉት ኩታ ገጠም (Cluster Farming) ምንነት በሰፊው ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ የመስኖ (በጋ) ስንዴ ስለሚባለው የእርሻ ልማትና በኩታ ገጠም እርሻ ይሳተፋሉ ስለሚባሉ የሙያ ማኅበራት ተናግረዋል፡፡ በዚህ ጥናታቸውም የኩታ ገጠም እርሻ (ክላስተር እርሻ) ምንነት የተዛባ አረዳድ እንዳለ ማረጋገጣቸውን ገልጸዋል፡፡ በአሥር ዓመቱ የአገር በቀል ኢኮኖሚ ልማት ዕቅድ ላይ ግብርና አንዱ ዋና ዘርፍ ተብሎ መቀመጡን ያመለከቱት ደምስ (ዶ/ር)፣ ግብርናን ለማዘመን የሚረዳ በማለትም የመስኖና ኩታ ገጠም

ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተውጣጡ አመራር አካላት በሐዋሳ ከተማ በመገኘት የልምድ ልውውጥ አደረጉ

    ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተውጣጡ አመራር አካላት በሐዋሳ ከተማ በመገኘት የልምድ ልውውጥ አደረጉ   ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ኮምሽን አመራሮች፣ ዳይሬክቶሬቶችና ቡድን መሪዎች በሐዋሳ ከተማ በመገኘት ነው የአረንጓዴ ልማት ስራዎችን እና ሌሎች የተከናወኑ ተግባራትን የጎበኙት።   ለእንግዶቹ አቀባበል ያደረጉት የሐዋሳ ከተማ ብልጽግና ፖርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ካሱ አሩሳ በሐዋሳ ከተማ አስተዳደር የተከናወኑ ተግባራትን አስመልክቶ ለልምድ ልውውጡ ለመጡ እንግዶች የጉብኝት መረሀ ግብርን መርተዋል።   በዚህ ወቅት አቶ ካሱ እንደገለጹት ለኑሮ ተስማሚ፣ ለንግድ ለኢንቨስትመንት እና ለቱሪዝም ምቹ የሆነችው የሐዋሳ ከተማ ካሏት ዘርፈ ብዙ ትሩፋቶቿ መካከል እንደሚጠቀስላት ተናግረዋል።   በገለፃቸው አቶ ካሱ የሐዋሳ ከተማ በፈጣን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ የዕድገት ግስጋሴ ላይ መገኘቷንም ነው ለእንግዶቹ ያስረዱት። የሐዋሳ ከተማ ፕላን ተግባራዊ እየተደረገ በመሠራቱ ለከተማዋ መሻሻል ከፍተኛ ለውጥ እያስመዘገበ እንደሚገኝም የገለፁት አቶ ካሱ በአረንጓዴ ልማት ተግባርም ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን በንግግራቸው አመላክተዋል።    ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ም/ኮምሽን አቶ ጌታቸው ኃይሌ በበኩላቸው የፍቅር ከተማ የሆነችው ሐዋሳ በየጊዜው እያስመዘገበችው ባለው ፈጣን እድገት እንዲሁም በልማት፣ በመልካም አስተዳደርና በሰላም እሴት ግንባታ ስራዎች ያላት እምቅ አቅም የተሻለ የልምድ መቀመሪያ እና የተሞክሮ መቅሰሚያ ልዩ ከተማ እንደሚያደርጋት ገልፀዋል።    ኮምሽነሩ አክለውም እንደ ሐዋሳ ከተማ በአረንጓዴ ልማት በህብረተሰብ ተሳትፎ የተከናወኑ ተግባራት በከተማቸው ተሞክሮውን በመውሰድ ለማስፋት የተለየ አጋጣሚ እንደሚፈጥርላቸውም ነው

የከተማው አነጋጋሪ ሆቴል ተመረቀ ኬና ሆቴል፤

በ8.7 በመቶ ዕድገት ይመዘገብበታል ተብሎ የነበረው የ2014 ዓ.ም. ኢኮኖሚ ከሰባት በመቶ እንደሚወርድ ተገለጸ

የ2015 ዓ.ም. የበጀት ጉድለት 224 ቢሊዮን ብር ወይም 3.4 በመቶ የአገራዊ ምርትን ይይዛል የ2014 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የ8.7 በመቶ ዕድገት እንደሚያስመዘግብ በዓመቱ መጀመሪያ በመንግሥት በኩል ተገልጾ የነበረ ቢሆንም፣ ይጠበቅ የነበረው አገራዊ ዕድገት ከሰባት በመቶ ሊበልጥ እንደማይችል የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ አስታወቁ፡፡ አቶ አህመድ ባለፈው ዓመት ሰኔ 2013 ዓ.ም. የ2014 ዓ.ም. አጠቃላይ በጀት ሲያቀርቡ፣ ኢኮኖሚው በመንግሥት እየተወሰዱ ያሉ ማሻሻያዎችን በተጠናከረ ሁኔታ ተግባራዊ በማድረግና የግሉን ዘርፍ ዕምቅ አቅም በመጠቀም በ2014 ዓ.ም. የተሻለ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እንደሚኖር ገልጸው ነበር፡፡ ይሁን እንጂ አቶ አህመድ ግንቦት 30 ቀን 2014 ዓ.ም. ከ786 ቢሊዮን ብር በላይ ሆኖ የቀረበውን የ2015 ዓ.ም. አገራዊ በጀት ሲያቀርቡ በተያዘው ዓመት በነበረው ጦርነት ምክንያት የመንግሥት ገቢ መቀነሱንና ከልማት አጋሮች የሚገኘው የበጀትና የልማት ድጋፍ በከፍተኛ ሁኔታ ማሽቆልቆሉን ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም በዓመቱ የነበሩ በርካታ መፈናቀሎች፣ የመሠረተ ልማትና የአገልግሎት መስጫ ተቋማት ውድመቶች የመንግሥት ሀብት ለጦርነት በመዋሉ፣ ድርቅ በመከሰቱ የአገሪቱ ምጣኔ ሀብት ዕድገት ከታቀደው የ8.7 በመቶ ወርዶ በ6 እና 7 በመቶ መካከል ሊሆን እንደሚችል አስረድተዋል፡፡ እንደ ሚኒስትሩ ገለጻ የቀጣዩ የ2015 በጀት ዓመት ኢኮኖሚው አሁን ካለበት ችግር በማገገም በአሥር ዓመቱ የልማት ዕቅድ በተቀመጠው መሠረት የ9.2 በመቶ ዕድገት ያስመዘግባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በሌላ በኩል በሚያዚያ 2014 ዓ.ም. መጨረሻ የታየውን የሸቀጦች ዋጋ 36 በመቶ ማሻቀብ በማስታወስ በ2015 ዓ.ም. መንግሥት አስፈላጊ የፖሊሲና መዋቅራዊ ዕርምጃዎችን ተግባ

“Xeena calla agadhite dirunni Mitte higge latisidhanno daga soorro diabbitanno”

“Xeena calla agadhite dirunni Mitte higge latisidhanno daga soorro diabbitanno” -Kalaa Yooseef Belayneh Sidaamu Qoqqowi Gorsu Latishshi Ejense Qara Loosu Harisaancho *********** (I P U/Bakkalcho Gaazeexa) Hawaasa:-Xeena calla agadhite dirunni Mitte higge latisidhanno daga soorro abbitannokki daafira,Qoqqowi giddo Gorsu latishshira noo injo garunni horonsi’ra hasiissannota Sidaamu Qoqqowi Gorsu Ejense Qaru Loosu Harisaanchi Kalaa Yooseef Belaynehu huwachishi. Kalaa Yooseefi Itophiyu Pireesete Uurrinsha ledo noosi keeshshonni xawisino garinni, Sidaamu Qoqqowira hala’lado Gorsunni lattara dandiitanno baattonna waay noo gede xiinxallotenni badate dandiinoonni. Konni kaiminnino qoqqowu deerrinni jajjabba Gorsu latishshi pirojektubba loonsanni afammannita coyi’rinohu qaru loosu harisaanchi; kuri mereerinnino Lemiina Honse /29/ pirojekte gumulante dagate owaante uytanni afantannoha ikkanna, Lemiina Mitte/28/ ijaarshu aananna Settayna Sette/88/ qole xiinxallotenna dizaynete loosi goofeenna a

በአጎራባች ክልሎች መካከል ዘላቂ ሰላም ማስፈንን አላማ ያደረገ ምክክር በሀዋሳ እየተካሄደ ነው

  በአጎራባች ክልሎች መካከል ዘላቂ ሰላም ማስፈንን አላማ ያደረገ ምክክር በሀዋሳ እየተካሄደ ነው ሰኔ 2 ቀን 2014(ኢዜአ) የኦሮሚያ፣ሲዳማ፣የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦችና የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልሎች የአጎራባች የመንግስታት ግንኙነት መድረክ ዛሬ በሀዋሳ እየተካሄደ ነው። በክልሎቹ መካከል ዘላቂ ሰላም ለማስፈን፣ችግሮች ሲያጋጥሙ በጋራ ለመፍታት፣ዋስትና ያለው ዴሞክራሲን በጋራ ማረጋገጥ የመድረኩ ዓላማ ሲሆን በመድረኩ ፈጣን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማትን ለማስቀጠል የሚያስችል ውይይት ይደረግበታል። በመድረኩ አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማህበረሰብን ለመገንባት ይቻል ዘንድ ከተናጠል ጥረቶች የጋራ አቅሞች በተገቢው መንገድ አቀናጅቶና አዋህዶ ዘርፈ ብዙ የልማት ተግባራትን ለማከናወን የሚያስችል ፎረም ይመሰረታል ተብሎም ይጠበቃል። የፌዴሬሽን ምክር ቤት ባዘጋጀው በዚሁ የምክክር መድረክ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ፣የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ዘሃራ ሁመድ፣የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተስፋዬ ይገዙና የየክልሎቹ ምክር ቤቶች አፈ ጉባኤዎችና ተወካዮች ተገኝተዋል።

የሀገር ወስጥ አምራች ኢንተርፕራይዞች በመንግስት የግዥ ስርዓት ውስጥ ተሳታፊ እንዲሆኑ እየሰራን ነው

   የሀገር ወስጥ አምራች ኢንተርፕራይዞች በመንግስት የግዥ ስርዓት ውስጥ ተሳታፊ እንዲሆኑ እየሰራን ነው //አቶ ብሩ ወልዴ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር// EED ግንቦት 27/2014 ዓ.ም (ሐዋሳ) *********** የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት በአነስተኛና መካከለኛ ፋይናንስ ፕሮጀክት አማካኝነት ከሲዳማ፣ ከደቡብ ምዕራብ፣ ከደቡብ፣ ከኦሮሚያ ክልሎችና ከአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር የመጡ 206 አምራች ኢንተርፕራይዞች በጨርቃጨርቅ፣ በወተትና ወተት ተዋዕጾ ማቀነባበርና በማርኬቲን /ፖኬጅንግ፣ ብራንዲንግ፣ ጥራትና በኤሌክትሮኒክስ ግብይት/ ዙሪያ በሐዋሳ ከተማ ሲሰጥ የነበረው ሰልጠና ተጠናቀቀ። በሰልጠናው ማጠቃለያ መድረክ የተገኙት የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር አቶ ብሩ ወልዴ የተሰጠው ሰልጠና አምራች ኢንተርፕራይዞች የተሻለና አለም አቀፋ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የሚያግዝ ስልጠና እንደሆነ ጠቁመው ኢንተርፕራይዞች በተግባር ሊታይ የሚችል የተሻለ ምርት በማምረት ራሳቸውንና ሀገራቸውን በኢኮኖሚ ማሳደግ እንዳለባቸው ተናግረዋል። የሀገር ወስጥ አምራች ኢንተርፕራይዞች በመንግስት የግዥ ስርዓት ውስጥ እንዲሳተፉ እየሰራን ነው ያሉት አቶ ብሩ ወልዴ አምራች ኢንተርፕራይዞች የሚያመርቷቸውን ምርቶች በስፋትና በጥራት ማምረት እንዳለባቸውና የተደራሽነት ወሰኑን በማስፋት የምስራቅ አፍሪካን ገበያ በማጥናት ተደራሽ መሆን እንደሚችሉ ጠቁመዋል። የሀገር ወሰጥ፣ የምስራቅ አፍሪካ፣ የአፍሪካንና የአለምን ገበያን መቆጣጠር የሚችሉ አምራች ኢንተርፕራይዞችን ለመፍጠር ከአጋር ተቋማት ጋር ተቀናጅተን እየሰራን ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ አምራች ኢንተርፕራይዞች በሚስተዋሉ ችግሮች ላይ የበኩላቸውን ጥረት ማድረግ እንዳለባቸው አብራርተዋል። ተወዳዳሪ የሆ

Hamaraancho Culture Of Sidama

የሴቶች ተጠቃሚነት ለከተማ ልማትና ለሀገር ገጽታ ግንባታ ወሳኝ ነው!

  የሴቶች ተጠቃሚነት ለከተማ ልማትና ለሀገር ገጽታ ግንባታ ወሳኝ ነው ! በሚል መሪ ቃል በሴቶች ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ዙሪያ የውይይት መድረክ ተካሄደ። በሀይሌ ሪዞርት የተካሄደው መድረክ የሲዳማ ብሄራዊ ክ / መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ጽ / ቤት፣ ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ( ስርዓተ ፆታ ) ዘርፍ ከሚኒስተር ቢሮ ጋር በመቀናጀት የተዘጋጀ ነው። በመድረኩ ከፌዴራል፣ ከሲዳማ ክልል፣ የሐዋሳ ከተማ አመራሮች፣ የሐይማኖት አባቶች ፣ የሐገር ሽማግሌዎች፣ ነጋዴዎች እና ነዎሪዎች ተገኝተዋል። የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ብልጽግና ፓርቲ ጽ / ቤት ሀላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ ሴቶች እንደ ሀገር በተገኘው ፈጣን እድገትና ድል የጎላ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ገልጸዋል ። የህብረተሰቡ ግማሽ አካል ለሆኑ ሴቶች ልዩ ትኩረት በመስጠት ዘላቂ ልማትን ማረጋገጥ እንዲቻል ምቹ ሁኔታ መፍጠርና ማብቃት የሚ ጠበቅ መሆኑን አቶ አብረሃም አክለዋል። የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ረ / ኘ ፀጋዬ ቱኬ ሴቶች አይችሉም የሚለውን አስተሳሰብ በመስበር እንደ ሀገር ኢትዮጵያን ማሻገር የቻሉ ሴቶችን ማስተዋል እንደተቻለ ተናግዋል። እንደ ሐዋሳ ከተማ ለከተማዋ ውበትና ጽዱ መሆን ሴቶች ግንባር ቀደም መሆናቸውን ከንቲባ ፀጋዬ አክለዋል። በከተማዋ ባሉ ጠንካራ የሴቶች አደረጃጀት ግንባር ቀደም መሆን እንደተቻለ የገለጹት ከንቲባው ሴቶችን በሁሉም ዘርፍ በማሳተፍ የሀገርን ብልጽገና ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።