በሲዳማ እና ኦሮሚያ ክልሎች አጎራባች አከባቢዎች የሚከሰቱትን ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ያስችላል የተባለለት የሰላም ኮንፌራንስ በሐዋሳ ከተማ እንደሚካሄድ ሰምተናል
ሰሞኑን በሲዳማ እና ኦሮሚያ ክልሎች አጎራባች አንዳንድ ቀበሌያት ተከስተው በነበረው ግጭቶች በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ የሚታወሰ ሲሆን፤ ባለፉት ጥቅት ቀናት ይህንን በተመለከተ በአከባቢው ሰላለው አጠቃላይ የጸጥታ ሁኔታ እና በቀጣይነት ተመሳሳይ ችግሮች እንዳይፈጠሩ በመደረግ ላይ ባሉት ተግባራት ላይ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት አንዳንድ መረጃዎችን ለአንዳንድ የክልሉ የሚዲያ አውታሮች ስሰጡ ተመልክተናል።
ባለፈው ሳምንት የተከሰተው እና በሰው ነፍስ እና በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሰው ግጭት በተለየ ሁኔታ እንደሚባለው በህዝቦች መካከል የተነሳ ሳይሆን፤ በኦሮሚያ ክልል የሚቀሳቀሱ የታጠቁ ሃይሎች በግልጽ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሲዳማ ልዩ ሃይል በኦሮሚያ መሰማራቱን በመቃዎም እና ለዚሁ የበቀል እርምጃ በሲዳማ ህዝብ ላይ እንደሚወስዱ በአደባባይ ካዛቱ በሃላ የፈጸሙት ነው።
ይህንን የአሽባሪ ቡድን ተግባር በመጀመሪያ ደረጃ የሁለቱም ክልል መንግስታት በአደባባይ ማውገዝ እና ዳግም እንዳይከሰት ለማድረግ ቃል መግባት ሲገባቸው፤ ምንም ሳይሉ ማለፋቸው ብሎም በአጠቃላይ፤ ከመንግስትም ሆነ ከተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች በግዳዩ ላይ የተባለ ነገር አለመኖሩ በርካታ፣ በተለይ የሲዳማን ምሁራንን ማስቆጣቱ ይታወሳል።
ያህም ሆነ ይህ ከቆይታ በሃላም ቢሆን ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ሰሞኑን በዳዬ ከተማ ውይይት ማድረጋቸው የተሰማ ሲሆን፤ በወይይቱም ላይ በአጎራባች አከባቢዎች በተደጋጋሚ የሚከሰቱትን ግጭቶችን በዘላቂነት ለመፋታታ ያስችላል የተባለለት ሰነድ ላይ ውይይት መደረጉ እና ከስምምነት ላይ መደረሱ ታውቋል።
ለወራንቻ ድረገጽ የደረሱ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከሆነ፤ በኦሮሚያ ክልል ምእራብ አርሲ ዞን እና በሲዳማ ክልል የድንበር ሰላምን ለማስፈን የተዘጋጀ የጋራ ስምምነት ስነድ በድንበር አከባቢ በተደጋጋሚ ግጭቶች በሚከሰቱባቸው አከባቢዎች የሚኖሩ የሁለቱም ክልል ህዝቦች የሰላም እና የእርቅ ኮንፌራንሳችን እንዲያካህዱ የሚያደርግ ነው።
ከዚህም ባሻገር ግጭት በሚቀሰቅሱ እና በግጭት ላይ በሚሳተፉ አካላት ላይ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የሁለቱም ክልል አከላት እርምጃ ለመውስድ መስማማታቸው የተነገረ ሲሆን፤ ለዚህም እንድረዳ ከሁለቱም ክልሎች የተወጣጣ አንድ የምርመራ ቡድን መቁቋሙን፤ የየአከባቢዎቹ የፖለቲካ አመራሮች ዘላቂ ሰላም ማምጣት በሚያስችሉ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት እንዲያደርጉ መወሰኑ እና በዚህ ሳምንት መጨረሻ ላይ ከአጎራባች ቀበሌያት የተወጣጡ ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት መሪዎችን ያካተተ የሰላም ኮንፌራንስ በሐዋሳ ከተማ እንዲደረግ ከስምምነት ላይ መደረሱ ተሰምቷል።
በቀጣይነትም የሰላም እና የእርቅ ኮንፌራንሶች በየቀበሌያቱ የሚካሄዱ ሲሆን፤ በወንጀል ላይ ተሳትፎል ተብሎ የተጠረጠሩት በህግ ስር ሆነው የማጣራት ስራ እንደሚሰራባቸው እና ወንጀለኞችን ከአንዱ ክልል ወደ ለሌላኛው ክልል አሳልፎ ለመስጠት ከስምምነት ላይ መደረሱ ታውቋል።
ግጭቱን ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል በኩል አንዳንድ እርምጃዎች መወሰዳቸው የተሰማ ሲሆን፤ ግጭቱ እንዳከሰት መስራት ያቻሉ እና ቸልተኝነትን አሳይቷል የተባሉ አመራሮች ከሃላፍነታቸው ላይ መነሳታቸው ተነግሯል። ነገር ግን ከሲዳማ ክልል በኩል ተመሳሳይ እርምጃዎችን አለመወሰዳቸው ተገልጿል።
በሲዳማ እና ኦሮሚያ አጎራባች አንዳንድ አከባቢዎች አልፎ አልፎ ግጭቶች መከሰታቸው አዲስ ነገር ባይሆንም፣ ባልፉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ በተደጋጋሚ መከሰታችው እና በተለይ ባለፈው ሳምንት በግጭቱ ላይ የተሰተፉት ሃይሎች የታጠቁ እና በሚሊቴር ሳይንስ የተደራጁ መሆናቸው ልዩ ያደርገዋል ተብሏል።
ከዚህም ባሻገር እነዚህ የተጠቁ ሃይሎች ከአጎራባች አከባቢዎች አለመሆናቸው እና ምንም አይነት ግጭት ሳይኖር በቀጥታ በሲዳማ አርሶ አደሮች እና በነዋሪዎች ላይ በዘፈቀደ ጥቃት የተፈጸመ መሆኑ አሳሳቢነቱን ከፍ አድርጎታል።
የሁለት ክልል መንግስታት በአመራሮች ደረጃ የሚያደርጉትን እከከኝ ልከክህ ግኙኝነትን ብቻ በህዝቦች መካከል ሰላምን ማምጣት ስለማይችል ዘላቂ መፍትሄ ማምጣት በሚያስችሉ አቅጣጫዎች ላይ ትኩረት ስጥተው መሰራት ይጠበቅባቸዋል።
Comments
Post a Comment