በዘንድሮውን የካፕ ኦፍ አክስለንሲ ኢትዮጵያ ውድድር፤ 13 የሲዳማ ቡና አብቃዮች ከ40 ምርጥ አብቃዮች መካከል መሆናቸው ታወቀ። የዘንድሮ በቡና ጥራት ውድድር አርባ ምርጥ የቡና አብቃኖች ስም ዝርዝር ይፋ የተደረገ ሲሆን፤ የሲዳማ ቡና አብቃይ የሆነው እና ከሲዳማ ክልል የቦና ዙሪያ ወረዳ በውድድሩ የተሳተፈው ቡና አብቃይ ካላ አበበ ሄዊሳ ዊቾን ጨምሮ 13 የሲዳማ ቡና አብቃዮች የዘንድሮውን የቡና ጥራት ውድድር በብሄራዊ ደረጃ በምርጥ ቡን ኣብቃይነት ተካተው አይተናል። በውድድሩ ተሳትፎ ለሆኑት የሲዳማ ክልል ቡና አብቃዮች መልካም እድል እንመኛለን።
It's about Sidaama!