በግምገማ መድረክ ላይ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ፣ የሲዳማ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ፣ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የሀዋሳ ከተማን ጨምሮ የሁሉም ወረዳና ከተማ አስተዳደር አመራሮች ተገኝተዋል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ መድረኩን ሲያጠቃልሉ በክልሉ የ10 ዓመት መሪ የልማት እቅድ ታቅዶ ወደ ሥራ የተገባ ሲሆን በየዓመቱ በሚሠራው ሥራ መሪ እቅዳችንን ማሳካት እንችላለን ብለው ይህም የተሰሩ ሥራዎችንም እየገመገምን ያልተሰሩ ሥራዎችን እየለየን ለህዝቡ ልማት ቁርጠኛ አቋም ይዘን ለሥራ መረባረብ ይኖርብናል ብለዋል።
ለህዝባችን አፋጣኝ ምላሽ ለሚሹ ለልማት ጥያቄዎች ትክክለኛና አፋጣኝ መልስ መመለስም ያስፈልጋል ብለዋል።
በሁሉም ዘርፍ በተለይ በግብርናው፣ በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በትምህርት፣ በጤና፣በንግድ ዘርፍ፣ ወዘተ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መሥራትን እንደሚጠይቅም አንስተዋል ርዕሰ መስተዳድሩ።
የክልሉ የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ በበኩላቸው ለህዝባችን ለመሥራት የብልጽግና ፓርቲያችን ባስቀመጠው አቅጣጫና በህዝባዊ መድረክ ላይ ህዝቡ ያነሷቸውን ጥያቄዎችን መሠረት በማድረግ ሁሉም ሴክተር ሥራውን በሚገባ እየገመገመ መሄድ እንዳለበት ተናግረው በየሴክተሩ እየተሠሩ ያሉ ስራዎች የህዝባችንን ችግር ለመፍታት ጥሩ እንደሆነም በማንሳት አሁንም ያሉት ጉድለቶችን በመፈለግ ችግሮችን ለይቶ በማውጣት በእቅድ መመራትና እቅዱንም በየጊዜው እየገመገሙ መሄድ ያስፈልጋል ብለዋል።
በሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ ሁሉም ትኩረት ሰጥቶ መሥራት አለበት ያሉት ኃላፊው የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ በግብርናው ዘርፊ አሁን ካለው በላይ ፍጥነት ጨምሮ መሥራት እንዳለበትና በገቢ ማሰባሰብ ላይ ቀልጣፋ ሥራ መሥራት እንዲሁም በህብረተሰቡ ውስጥ ገብቶ ለህዝቡ የቸገረውን እየለዩ እየሰሩ መሄድ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የሲዳማ ብ/ክ/መ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት
Comments
Post a Comment