በስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ በሲዳማ ክልል ለፓርላማ የተወዳደሩ ሁለት ተመራጮች፤ በመጪው ሳምንት መጀመሪያ ወደሚከፈተው የተወካዮች ምክር ቤት ላይገቡ እንደሚችሉ አስጠነቀቁ። የሲዳማ አርነት ንቅናቄ (ሲአን) አመራሮች የሆኑት ሁለቱ ግለሰቦች፤ በፓርቲያቸው እና በሲዳማ ብልጽግና መካከል ያለው የቅንጅት ሂደት እልባት ካላገኘ ወደ ፓርላማ ላለመግባት መወሰናቸውን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን ከመቀላቀላቸው በፊት ያስቀመጡት ቅድመ ሁኔታ እንዲሟላ የጠየቁት የፓርላማ ተመራጮች፤ አቶ ሰላሙ ቡላዶ እና አቶ ደሳለኝ ሜሳ ናቸው። የሲአን ኢኮኖሚ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሰላሙ በሲዳማ ክልል በቡርሳ ምርጫ ክልል ተወዳድረው ያሸንፉ ሲሆን፤ የፓርቲው ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ ደሳለኝ ደግሞ በቱላ ምርጫ ክልል ለፓርላማ የተመረጡ ናቸው። ሁለቱ ተመራጮች ባለፈው ሰኔ ወር በተካሄደው ምርጫ ለውድድር የቀረቡት ገዢው ብልጽግና ፓርቲን ወክለው እንደነበር ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተገኘው መረጃ ያሳያል። የሲዳማ ክልል በተወካዮች ምክር ቤት ያሉትን 19 መቀመጫዎች ሙሉ ለሙሉ ያሸነፈውም ገዢው ፓርቲ ነው። ሁለቱ የሲአን ከፍተኛ አመራሮች በብልጽግና ስም ለምርጫ የቀረቡት፤ ፓርቲያቸው ከሲዳማ ብልጽግና ፓርቲ ጋር የፈጠረው ቅንጅት “በፍጥነት ዕውቅና ያገኛል” ብለው በማሰባቸው እንደነበር ያስረዳሉ። የፓርቲያቸው አመራሮች “የዕጩ ማስመዝገቢያ ጊዜ እንዳያልፍ” በሚል እንደ ብልጽግና ፓርቲ ዕጩዎች እንዲመዘገቡ እንደነገሯቸው አቶ ደሳለኝ ይናገራሉ። “የቅንጅቱ ጉዳይ ከዚያ በኋላ ያልቃል” የሚል ቃል እንደተገባላቸውም መልስ ብለው ያስታውሳሉ። የሲአን እና ብልጽግና ቅንጅት ጉዳይ መነሳት የጀመረው ከሲዳማ ክልል ምስረታ ማግስት ጀምሮ ነው። ሲአን ለገዢው
It's about Sidaama!