Skip to main content

የተቋረጠው የሐዋሳ ስቴዲዬም ግንባታ እንዲቀጥል ኮሚቴው አሳሰበ

የተቋረጠው የሐዋሳ ስቴዲዬም ግንባታ እንዲቀጥል ኮሚቴው አሳሰበ

 (ዜና ፓርላማ)፤ መጋቢት 2013 ዓ.ም.፣ ሐዋሳ፤ የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሴቶች፣ ወጣቶች እና ማኅበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፤ የተቋረጠው የሐዋሳ ስቴዲዬም ግንባታ እንዲቀጥል አሳሰበ፡፡

ቋሚ ኮሚቴው ይህንን ማሳሰቢያ የሰጠው፤ ሰሞኑን በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሐዋሳ ከተማ የመስክ ምልከታ በአካሄደበት ወቅት ነው፡፡ የግንባታውን አሁናዊ ይዞታ የገመገመው የስቴዲዬሙ ግንባታ የቴክኒክ ኮሚቴ፤ ከዐቢይ ኮሚቴ በሚሰጠው አቅጣጫ ተመሥርቶ ወደ ግንባታ ለመግባት የሚያስችለውን ሁኔታ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እንዲያመቻችም የቋሚ ኮሚቴው ቡድን ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ ሞሚና መሐመድ አመላክተዋል፡፡  

የሐዋሳ ስቴዲዬም ግንባታ የመጀመሪያ ምዕራፍ የተጠናቀቀ ቢሆንም፤ ለአደጋ ተጋልጦ አገልግሎት ሳይሰጥ መቀመጡ ተገቢ ባለመሆኑ ለችግሩ መፍትሄ ሊበጅለት እንደሚገባ ቋሚ ኮሚቴው አሳስቧል፡፡ በተጨማሪም ከስፖርቱ ዘርፍ ጋር ተያይዞ ጤናማ እና ብቁ ዜጎችን ለማፋራት የስፖርት ማዘዉተሪያዎች ትልቅ ሚና ስላላቸዉ በቂ ትኩረት ለዘርፉ እንዲቸርም ኮሚቴው አያይዞ አስገንዝቧል፡፡

የሐዋሳ ዓለም-አቀፍ ስቴዲዬም ሳትኮን ከተሰኘ ሀገር-በቀል የግንባታ የግል ኩባኒያ ጋር በተደረገው ስምምነት መሠረት በ7 መቶ ሚሊዬን ብር የተገነባ ሲሆን፤ የመጀመሪያ የግንባታ ምዕራፉን በውሉ መሠረት ማጠናቀቁን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ እናም የሲዳማ ክልል የባሕል፣ ቱሪዝም እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃጎ አገኘሁ፤ ይህ ግልጽ ባለቤት የሌለው እና ምንም ዓይነት ርክክብ የአልተደረገለት ስቴዲዬም የፌዴራል መንግስትን ምላሽ እንደሚፈልግ ጠቁመዋል፡፡ 

የሲዳማ ክልል ዕምቅ የባህል እና የቱሪዝም ሀብት ባለቤት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ፤ በክልሉም ሆነ በባሕል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር ጥናቶች በማድረግ እና የዓቅም ግንባታ ድጋፍ በመስጠት በቅንጅት መሥራት እንደሚገባ ቋሚ ኮሚቴው አመላክቷል፡፡

የክልሉ ባሕል እና ቱሪዝም ቢሮ የክልሉን ብሔረሰብ ቋንቋ ለማሳደግ በክልሉ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት ለሚገኙ ሠራተኞች የቋንቋው ስልጠና እየሰጠ እንደሆነ ቋሚ ኮሚቴው ከተደረገለት ማብራሪያ ተረድቷል፡፡ በክልሉ የነበረው የጸጥታ ችግር ተቀርፎ ባሕል እና ቅርስ የማስተዋወቅ ሥራው በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገራት በመሠራቱ የቱሪስቶች ቁጥር እየጨመሩ መምጣቱን ኮሚቴው ከክልሉ ባሕል እና ቱሪዝም ቢሮ የማኔጅመንት ቡድን ጋር ካካሄደው ውይይት መረዳቱን ተናግሯል፡፡

የሲዳማ ክልል ቱሪዝም ዘርፍ ምክትል ኃላፊ አቶ ሳሙኤል በላይነህ እንደሚሉት፤ በ2012 የበጀት ዓመት ክልሉን ይጎበኛሉ ተብለው የተጠበቁት ቱሪስቶች 1 ነጥብ 6 ሚሊዬን ነበሩ፡፡ ይሁን እንጂ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ተጽዕኖ እና መጠነኛ የፀጥታ ችግር ባለበት ሁኔታ፤ በበጀት ዓመቱ 9 መቶ ሺህ ቱሪስቶች ክልሉን መጎብኘታቸውን ኃላፊው ገልጸዋል፡፡

በመስፍን አለሰው

Comments

Popular posts from this blog

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

የለበሰው ያደፈ ቁምጣና ሹራብ ከቅዝቃዜው አላዳነውም፡፡ ካፊያው ልብሱን አርሶታል፡፡ ሽው እያለ ከሐይቁ የሚነሳው ነፋስ የሚፈጥረው ቅዝቃዜ ያንቀጠቅጠዋል፡፡ የተጫማው ያረጀ ሲሊፐር እግሩን ከምንም አላዳነውም፡፡ በባዶ እግሩ የሚራመድ ያህል ጨቅይቷል፡፡ ተደባዳቢ ይመስል ፊቱ የተሞነጫጨረ ነው፡፡ ገና 12 ዓመቱ ቢሆንም፣ ቁመናው እንደ ትልቅ ሰው ግዙፍ ነው፡፡ የሚለብሰውን እንደ ልቡ ባያገኝም፣ የሚያስፈልገውን ነገር ለማሟላት ቤሳቢስቲን የሌላቸው ወላጆቹን አያስቸግርም፡፡ ከቤተሰቦቹ ጋር ከሚኖሩበት ታቦር ተራራ ጀርባ ወዳለው ሐዋሳ ሐይቅ ከወረደ እንኳንስ የራሱን የቤተሰቦቹንም የዕለት ጉርስ የሚሸፍንበት ገንዘብ አያጣም፡፡ የአስጎብኚነት ዕውቀት፣ ከሐይቁም ውስጥ ዓሳ የሚያጠምድበት መረብም ሆነ ፈቃድ የለውም፡፡ ሙሉቀን (ስሙ ተቀይሯል) እና ጓደኞቹ ሐይቁን ለመጎብኘት የሚሄዱ ጎብኚዎች በካሜራቸው ጥሩ ፎቶ እንዲያስቀሩ ድባቡን የማሳመር ሥራ ይሠራሉ፡፡ ካሜራውን ይዞ ቁጭ ብድግ እያለ ጥሩ ፎቶ ለማንሳት ጥረት የሚያደርግ ሲያዩ፣ ቆርጠው የያዙትን የዓሳ ሥጋ ይዘው ጠጋ ጠጋ ይላሉ፡፡ ቁርጥራጩን የዓሳ ሥጋ ምግብ ለሚቀሙት አባኮዳዎች ሻሞ ይላሉ፡፡ የተወረወረላቸውን ቀድመው ለመቅለብ አባኮዳዎቹ ክንፋቸውን እየመቱ ወደ ላይ ብድግ ይላሉ፡፡ የናሽናል ጆግሪፊ የፎቶግራፍ ባለሙያዎች ያነሱት ዓይነት ፎቶዎች ሳያስቡት ያነሳሉ፡፡ በሁኔታው ተደስተው ደጋግመው ድንቅ ፎቶዎችን ለመውሰድ ሲዘጋጁ እነ ሙሉቀንም አጀንዳቸውን ይፋ ማድረግ ይጀምራሉ፡፡ አቶ ዳዊት አብርሃም ‹‹አንዱን ዓሳ በአሥር ብር ገዝቼ ነው እንዲህ የማዘጋጀው፤›› በማለት በቅድሚያ  መረጃ ይሰጣሉ፡፡ ለቀጣዩ ዜና በዚህ መልኩ እንዲዘጋጁ ካደረጉ በኋላ፣ ሌሎች ሰዎች መቶም ሁለት መቶም ብር እንደሚሰጧቸው ቀለል

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የመንግሥት ስልጠና የምርጫ ቅስቀሳ አካል ነው ብሏል  የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ለምን ወጣ መባሉ ተገቢ አይደለም - ምርጫ ቦርድ ምርጫ ቦርድ ከኢህአዴግ ተፅዕኖ ሙሉ ለሙሉ ነፃ መሆኑ ሳይረጋገጥና የምርጫ አፈፃፀም ችግሮች ሳይወገዱ የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ለማወጅ መዘጋጀቱ ተገቢ አይደለም ሲል ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ የሚመሩት ኢማዴ-ደህአፓ ተቃወመ፡፡ መንግስት፤ የዩኒቨርሲቲ መምህራንና ተማሪዎችን ጨምሮ ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየሰጠ ያለው ስልጠና የምርጫ ቅስቀሳ አካል ነው ሲልም ፓርቲው ኮንኗል፡፡  የኢትዮጵያ ማህበረ ዴሞክራሲ ደቡብ ህዝቦች አንድነት ፓርቲ ሰሞኑን ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ባስገባው ግልፅ ደብዳቤ፤ ያለፉት አገር አቀፍና የአካባቢ ምርጫዎች ከመካሄዳቸው በፊት በምርጫ ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው ዙሪያ ኢህአዴግ ከተቃዋሚዎች ጋር የሚወያይበት መድረክ እንዲዘጋጅ በተደጋጋሚ ብንጠይቅም እስካሁን ከቦርዱ የተሰጠ ተግባራዊ ምላሽ የለም ብሏል፡፡  ሃገሪቱ “በአንድ አውራ ፓርቲ” ብቸኛ ቁጥጥር ስር መውደቋ አደገኛና አሳሳቢ ነው ያለው ፓርቲው፤ የመድብለ ፓርቲ ስርአት የመገንባት ተስፋችን ጨርሶ እንዳይከስም ቦርዱ ሃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት አሳስቧል፡፡ ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ የሚካሄድበትን ሁኔታ ለመፍጠር ገዥው ፓርቲና ሃቀኛ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚወያዩበት መድረክ እንዲያመቻች በህግ ስልጣን የተሰጠው ምርጫ ቦርድ የገባውን ቃል በማጠፍ መድረኩን ሳያመቻች የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማዘጋጀቱ ፋይዳ የለውም ብሏል - ፓርቲው፡፡  ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ በተሻሻለው የምርጫ ህግ፣ ለቦርዱ የተሰጠውን የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ መድረክ የማስተባበር ስልጣን ለመቀማት ታማኝ ፓርቲዎችን በተቃዋሚ ስም አሰባስቦ “የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ መድረክ” በመፍጠር የምርጫ ውድድር አሯሯጭ አሰልፏል ሲ

የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል ማለፊያ ነጥብ ውጤት ነገ ይፋ ይሆናል

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 23 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) የ10ኛ ክፍል ማጠቃለያና የ12ኛ ክፍል መሰናዶ ማለፊያ ነጥብ ውጤትን ነገ ይፋ እንደሚያደርግ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። የዩኒቨርስቲ መግቢያና ወደ መሰናዶ ማለፊያ ነጥብን ለመወሰን  ፥ የዩኒቨርስቲዎችን ቀጣይ የመቀበል አቅም ከግምት ውስጥ በማስገባት መወሰኑንም ነው ሚኒስቴሩ የገለጸው። በአጠቃላይ 548 ሺህ 138 ተማሪዎች የ10 ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተናውን ወስደው 70 በመቶዎቹ 2 ነጥብ እና ካዛ በላይ ውጤት ሲያስመዘግቡ ፥ በተመሳሳይም የ12ኛ ክፍልን የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተናን ከወሰዱት መካከል 70 በመቶ የሚሆኑት ተፈታኞች ከ350 ነጥብ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውን ቀደም ሲል  የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና የፈተናዎች ኤጀንሲ አስታውሷል ። በነገው እለትም የሁለቱም ፈተናዎች የመቁረጫ ውጤት ይፋ ይደረጋል ተብሏል።