Skip to main content

በሲዳማ ክልል፤ የዘንድሮዉ የመምህራን የስራ ምደባ አሰጣጥ ለትምህርት ጥራት መሻሻል የጎላ ሚና እንደሚኖረዉ፤ የክልሉ መንግስት ገለጸ

 ሲዳማ፤ ሀዋሳ፤ መጋቢት 26/2013 ዓ.ም፤ በሲዳማ ክልል የተካሔደዉ የዘንድሮዉ የመምህራን የስራ ምደባ አሰጣጥ ለትምህርት ጥራት መሻሻል የጎላ ሚና እንደሚኖረዉ፤ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታዉቋል፡፡

ይህንን አስመልክተዉ መግለጫ የሰጡት የቢሮዉ ም/ኃላፊና የመም/ትም/አመ/ል/ሙያ ፍቃድ አስ/ዕድሳት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተክሉ አዱላ እንደገለጹት፤ መምህራን ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ አንበሳዉን ድርሻ የሚወስዱ በመሆናቸዉ፤ በክልሉ ለመምህራን ልማት ስራ ልዩ ትኩረት በመስጠት እየተሰራ እንደሚገኝ በማንሳት፤ የዘንድሮዉ ምደባም አንዱ ማሰያ መሆኑን ገጸዋል፡፡
አያይዘዉም፤ የዲፕሎማም ሆነ የዲግሪ ምሩቅ መምህራን ምደባ ከዚህ ቀደም በታችኞቹ መዋቅሮች በየከተማ አስተዳደሮቹና ወረዳዎቹ እንደሚካሄድ አንስተዉ፤
ይህም በፍትሃዊነት፤ በግልጽ ዉድድር በብቃት ላይ ብቻ ትኩረት በማድረግ አወዳድሮ ከመቅጠር አኳያ ክፍተት ሲስተዋልበት የቆዬ ከመሆኑም በላይ በአንዳንድ አከባቢዎች የመምህራን እጥረት እንዲገጥም በተቃራኒዉ ሌላጋ እንዲበዛ እንዲሁም አልፎ አልፎ በማህበራዊ ህይወቶች በመጠመድ በመማር ማስተማሩ ስራ ላይ ከፍተኛ ክፍተት እንዲታይ ማድረጉን በዳሰሳ ጥናቱ ወቅት መለየት መቻሉንም ገልፀዋል።
በሌላ ጎኑ፤ በሁሉም አከባቢዎች ተዘዋዉሮ መስራቱ ለአንድ ሀገር፤ ለአንድ ማህበረሰብ የሚሰሩ ዜጎችን በሁለንተናዊ ልምድ፤ ባህል፤ ወግና ዕዉቀት ከማስተሳሰር ረገድ የሚኖረው ሚና የጎላ መሆኑንም አንስተዋል፡፡
በዚህም መነሻ፤ ከተመዘገቡቱ መምህራን መካከል 6452 ያህሉ የተዘጋጀዉን ፈተና የወሰዱ ሲሆኑ፤ ከነዚህ መካከል 914 የምሆኑቱ መረጃቸዉ ዳግም መጠራት የሚያስፈልገዉ በመሆኑ፤ ተቀጥረዉ ሲሰሩ የነበሩ ቀርበዉ በመመዘገባቸዉ፤ ማስታወቂያ በወጣበት ወቅት ቀርበዉ ያልተመዘገቡ በመሆናቸዉ የታገዱ ሲሆን፤
የተቀሩቱን 5538 እጅግ በከፍተኛ ጥንቃቄ፤ ፍጹምነቱን በጠበቀ መልኩ በማወዳደር የወረዳዎችና የከተማ አስተዳደሮች ፍላጎት መነሻ በማድረግ 3636 መምህራንን አወዳድሮ በመለየት ለምደባ ዝግጅት መደረጉን ገልጸዉ፤
ምደባዉም ፍጹም ግልጸኝነት በተሞላው መልኩ ያለፉትን በዕጣ ብቻ በመለየት እየተካሄደ ያለ ሲሆን፤ በተቀመጠዉም አቅጣጫ መሰረት እስከ ነገ መጋቢት 27/2013 ድረስ በየዕለቱ 600 የሚሆኑ ቀርበዉ የዕጣ እያነሱ እየተተገበረ ነው ብሏል።
በሂደቱም ወደ 405 የሚሆኑቱ ቅሬታ ያቀረቡ ሲሆን፣ ኮሚቴውም የቅሬታውን ተገቢነት በማየት 136ቱ ተገቢ ቅረታ ማቅረባቸውን በማየት እንዲያልፉ መወሰኑንና የተቀሩቱ ያቀረቡት ተገቢ ሆኖ ባለመገኘቱ መታለፉን ም/ኃላፊው ገልፆል።
በመጨረሻም፣ ምደባውን በክልሉ መንግስት አቅጣጫ መነሻ፣ ቢሮው ከፓብልክ ሠርቨስና ሠው ሀብት ልማት ቢሮ ጋር በመሆን እያስፈፀመ ያለ ሲሆን፣ በቀጣይነት የትምህርት ጥራት ለማረጋገጥና ለማህበረሰቡ ተገቢውን አገልግሎት በመስጠት ረገድ የሚኖረው ሚና የጎላ በመሆኑ፣ ፍፁም ጥንቃቄ በተሞላበት ደረጃ የተሠራና እየተሠራ የሚገኝ መሆኑን ገልፀው፣ ውድ መምህራንም በዕጣቸው መሠረት በተመደቡበት በመሄድ ማህበረሰባቸውን እንዲያገለግሉ ጥሪ አቅርበዋል።

Comments

Popular posts from this blog

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

የለበሰው ያደፈ ቁምጣና ሹራብ ከቅዝቃዜው አላዳነውም፡፡ ካፊያው ልብሱን አርሶታል፡፡ ሽው እያለ ከሐይቁ የሚነሳው ነፋስ የሚፈጥረው ቅዝቃዜ ያንቀጠቅጠዋል፡፡ የተጫማው ያረጀ ሲሊፐር እግሩን ከምንም አላዳነውም፡፡ በባዶ እግሩ የሚራመድ ያህል ጨቅይቷል፡፡ ተደባዳቢ ይመስል ፊቱ የተሞነጫጨረ ነው፡፡ ገና 12 ዓመቱ ቢሆንም፣ ቁመናው እንደ ትልቅ ሰው ግዙፍ ነው፡፡ የሚለብሰውን እንደ ልቡ ባያገኝም፣ የሚያስፈልገውን ነገር ለማሟላት ቤሳቢስቲን የሌላቸው ወላጆቹን አያስቸግርም፡፡ ከቤተሰቦቹ ጋር ከሚኖሩበት ታቦር ተራራ ጀርባ ወዳለው ሐዋሳ ሐይቅ ከወረደ እንኳንስ የራሱን የቤተሰቦቹንም የዕለት ጉርስ የሚሸፍንበት ገንዘብ አያጣም፡፡ የአስጎብኚነት ዕውቀት፣ ከሐይቁም ውስጥ ዓሳ የሚያጠምድበት መረብም ሆነ ፈቃድ የለውም፡፡ ሙሉቀን (ስሙ ተቀይሯል) እና ጓደኞቹ ሐይቁን ለመጎብኘት የሚሄዱ ጎብኚዎች በካሜራቸው ጥሩ ፎቶ እንዲያስቀሩ ድባቡን የማሳመር ሥራ ይሠራሉ፡፡ ካሜራውን ይዞ ቁጭ ብድግ እያለ ጥሩ ፎቶ ለማንሳት ጥረት የሚያደርግ ሲያዩ፣ ቆርጠው የያዙትን የዓሳ ሥጋ ይዘው ጠጋ ጠጋ ይላሉ፡፡ ቁርጥራጩን የዓሳ ሥጋ ምግብ ለሚቀሙት አባኮዳዎች ሻሞ ይላሉ፡፡ የተወረወረላቸውን ቀድመው ለመቅለብ አባኮዳዎቹ ክንፋቸውን እየመቱ ወደ ላይ ብድግ ይላሉ፡፡ የናሽናል ጆግሪፊ የፎቶግራፍ ባለሙያዎች ያነሱት ዓይነት ፎቶዎች ሳያስቡት ያነሳሉ፡፡ በሁኔታው ተደስተው ደጋግመው ድንቅ ፎቶዎችን ለመውሰድ ሲዘጋጁ እነ ሙሉቀንም አጀንዳቸውን ይፋ ማድረግ ይጀምራሉ፡፡ አቶ ዳዊት አብርሃም ‹‹አንዱን ዓሳ በአሥር ብር ገዝቼ ነው እንዲህ የማዘጋጀው፤›› በማለት በቅድሚያ  መረጃ ይሰጣሉ፡፡ ለቀጣዩ ዜና በዚህ መልኩ እንዲዘጋጁ ካደረጉ በኋላ፣ ሌሎች ሰዎች መቶም ሁለት መቶም ብር እንደሚሰጧቸው ቀለል

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የመንግሥት ስልጠና የምርጫ ቅስቀሳ አካል ነው ብሏል  የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ለምን ወጣ መባሉ ተገቢ አይደለም - ምርጫ ቦርድ ምርጫ ቦርድ ከኢህአዴግ ተፅዕኖ ሙሉ ለሙሉ ነፃ መሆኑ ሳይረጋገጥና የምርጫ አፈፃፀም ችግሮች ሳይወገዱ የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ለማወጅ መዘጋጀቱ ተገቢ አይደለም ሲል ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ የሚመሩት ኢማዴ-ደህአፓ ተቃወመ፡፡ መንግስት፤ የዩኒቨርሲቲ መምህራንና ተማሪዎችን ጨምሮ ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየሰጠ ያለው ስልጠና የምርጫ ቅስቀሳ አካል ነው ሲልም ፓርቲው ኮንኗል፡፡  የኢትዮጵያ ማህበረ ዴሞክራሲ ደቡብ ህዝቦች አንድነት ፓርቲ ሰሞኑን ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ባስገባው ግልፅ ደብዳቤ፤ ያለፉት አገር አቀፍና የአካባቢ ምርጫዎች ከመካሄዳቸው በፊት በምርጫ ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው ዙሪያ ኢህአዴግ ከተቃዋሚዎች ጋር የሚወያይበት መድረክ እንዲዘጋጅ በተደጋጋሚ ብንጠይቅም እስካሁን ከቦርዱ የተሰጠ ተግባራዊ ምላሽ የለም ብሏል፡፡  ሃገሪቱ “በአንድ አውራ ፓርቲ” ብቸኛ ቁጥጥር ስር መውደቋ አደገኛና አሳሳቢ ነው ያለው ፓርቲው፤ የመድብለ ፓርቲ ስርአት የመገንባት ተስፋችን ጨርሶ እንዳይከስም ቦርዱ ሃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት አሳስቧል፡፡ ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ የሚካሄድበትን ሁኔታ ለመፍጠር ገዥው ፓርቲና ሃቀኛ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚወያዩበት መድረክ እንዲያመቻች በህግ ስልጣን የተሰጠው ምርጫ ቦርድ የገባውን ቃል በማጠፍ መድረኩን ሳያመቻች የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማዘጋጀቱ ፋይዳ የለውም ብሏል - ፓርቲው፡፡  ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ በተሻሻለው የምርጫ ህግ፣ ለቦርዱ የተሰጠውን የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ መድረክ የማስተባበር ስልጣን ለመቀማት ታማኝ ፓርቲዎችን በተቃዋሚ ስም አሰባስቦ “የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ መድረክ” በመፍጠር የምርጫ ውድድር አሯሯጭ አሰልፏል ሲ

የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል ማለፊያ ነጥብ ውጤት ነገ ይፋ ይሆናል

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 23 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) የ10ኛ ክፍል ማጠቃለያና የ12ኛ ክፍል መሰናዶ ማለፊያ ነጥብ ውጤትን ነገ ይፋ እንደሚያደርግ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። የዩኒቨርስቲ መግቢያና ወደ መሰናዶ ማለፊያ ነጥብን ለመወሰን  ፥ የዩኒቨርስቲዎችን ቀጣይ የመቀበል አቅም ከግምት ውስጥ በማስገባት መወሰኑንም ነው ሚኒስቴሩ የገለጸው። በአጠቃላይ 548 ሺህ 138 ተማሪዎች የ10 ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተናውን ወስደው 70 በመቶዎቹ 2 ነጥብ እና ካዛ በላይ ውጤት ሲያስመዘግቡ ፥ በተመሳሳይም የ12ኛ ክፍልን የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተናን ከወሰዱት መካከል 70 በመቶ የሚሆኑት ተፈታኞች ከ350 ነጥብ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውን ቀደም ሲል  የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና የፈተናዎች ኤጀንሲ አስታውሷል ። በነገው እለትም የሁለቱም ፈተናዎች የመቁረጫ ውጤት ይፋ ይደረጋል ተብሏል።