የሲዳማ ክልል የመንግስት የኮሙኒኬሽን ቢሮ ዛሬ በሀይሌ ሪዞርት የዘጠኝ ወር እቅድ አፈጻጸም ግምገማና የሚዲያ ፎረም ማቋቋሚያ መድረክ አካሂዷል።
የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ አቶ ፊሊጶስ ናሆም ሴክተሩ ከቢሮ ጀምሮ እስከታችኛው መዋቅር ድረስ ዘርፉ የተመራበን አግባብ የተሻለ የሚባል ነው ሲሉ ገልጸዋል። አቶ ፊሊጶስ አክለውም ክልሉ አዲስ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በሰው ሀይል፣ በክህሎት ውስንነትና በቁሳቁስ እጥረት የሚፈለገውን ያክል እንዳልተሰራም ተናግረዋል።
ክልሉ ያለበትን የሚዲያ ደረጃ በመገምገም የሚዲያ ፎረም የሚቋቋም መሆኑን የገለጹት አቶ ፊሊጶስ በቀጣይ በክልሉ ተአማኒነት ያለው መንግስትንና ህዝብን የሚያቀራርብ፣ ለሀሰተኛ መረጃዎች አጸፋ የሚሰጥ የተጠናከረ የሚዲያ ተቋም የማቋቋም ዓላማ መኖሩን ገልጸዋል።
የሐ/ከ/መ/ኮ/ጉ/መምሪያ
Comments
Post a Comment