Skip to main content

በሐዋሳ የኮቪድ 19ኝ ወረርሽኝን ለመከላከል ተገቢውን ጥንቃቄ በማያደርጉ ግለሰቦች፣ ተቋማትና አገልግሎት ሰጪዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ የመውሰዱ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለፀ

በሐዋሳ የኮቪድ 19ኝ ወረርሽኝን ለመከላከል ተገቢውን ጥንቃቄ በማያደርጉ ግለሰቦች፣ ተቋማትና አገልግሎት ሰጪዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ የመውሰዱ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለፀ።

ወረርሽኙን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ተገቢውን ጥንቃቄ በማያደርጉ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ የመውሰዱ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙንጠሻ ብርሀኑ እና ኮማንደር ደረሰ ቡሳሮ የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ገልፀዋል።

በከተማ ደረጃ የኮቪድ 19ኝ ወረርሽኝ ስርጭት አሳሳቢ ደረጃ መድረሱን የገለፁት የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙንጣሻ ብርሀኑ በተለያየ ጊዜ የተሰራው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ ብቻውን የሚፈለገውን ውጤት አለማምጣቱን ገልፀዋል።

በከተማ ደረጃ የበሽታውን ስርጭት ለመከላከል በሚደረገው ጥረት የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ ቢሆንም በህብረተሰቡ ዘንድ የሚስተዋለው መዘናጋት ትልቅ ዋጋ እያስከፈለ መሆኑንም ኃላፊዎቹ ጠቁመዋል።

በዚህም ከጊዜ ወደ ጊዜ የቫይረሱ የስርጭትና በበሽታው ምክንያት ህይወታቸው የሚያልፍ ሰዎች ቁጥርም እየጨመረ መምጣቱን አቶ ሙንጠሻ አመላክተዋል።

ከዚህ ባለፈም ባለፉት ተከታታይ 5 ቀናት የተደረገ ምርመራ ከተመረመሩት 100 ሰዎች በአማካይ 59 ሰዎች ቫይረሱ እንዳለባቸው የሚያሳይ መሆኑንም የጤና መምሪያው ኃላፊ ገልፀዋል።

የሐዋዳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ደረሰ ቡሳሮ በበኩላቸው ግንዛቤ ከማስጨበጥ ባለፈ ህጋዊ እርምጃ በመውሰድ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግና የቫይረሱን ስርጭት መከላከል እንዲችል የወጡ መመሪያዎችን ተግባራዊ በማያደርጉ ግለሰቦች,ተቋማትና ሌሎች አገልግሎት ሰጪዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን ጠቁመዋል።

የመንግስትና የግል ተቋማት፣ሆቴሎችና መዝናኛ ስፍራዎች፣ የሀይማኖት ተቋማት፣የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች እንዲሁም ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት ኮቪድ 19ኝን ለመከላከል የወጡ መመሪያዎችን በተገቢው ተግባራዊ የማድረግ ግዴታ የተጣለባቸው ሲሆን ይህን የማያደረግ የትኛውም አካል በህግ ተጠያቂ እንደሚሆንም ኮማንደር ደረሰ አመላክተዋል።

ዜጎች የጥንቃቄ እርምጃዎችን በመውሰድ እራሳቸውንና ህብረተሰቡን ከበሽታው እንዲጠብቁ ስፋት ያለው የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ የተሰራ ቢሆንም ግለሰቦች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ ሳያደርጉ፣ርቀታችውን ሳይጠብቁና ሌሎች የጥንቃቄ እርምጃዎች ሳይወስዱ በየትኛውም አካባቢ መንቀሳቀስ እንደማይችሉና ይህን ተላልፈው የሚገኙ አካላት በገንዘብና በእስር ጭምር ቅጣት የሚጣልባቸው እንደሆነም ተገልጿል።

የመንግስትም ይሁን የግል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ሳያደርጉ አገልግሎት መስጠት እንደማይችሉ እንዲሁም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ላላደረገ አካል አገልግሎት መስጠት እንደሌለባቸውም በመግለጫው ተመላክቷል።

ሆቴሎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ላላድረገ አካል አገልግሎት መስጠት እንደማይችሉ እንዲሁም በአንድ ጠረጴዛ ከ3 ሰዎች በላይ ማስተናገድ የተከለከለ መሆኑም እንዲሁ።

የሆቴል አስተናጋጆች ማስክ ሳያደርጉ አገልግሎት እንዳይሰጡ እንዲሁም የእጅ ንፅህና መጠበቂያ ውሀና ሳሙና ወይንም ሳኒታይዘር የማቅረብ ግዴታ የተጣለባቸው መሆኑ።

በሁሉም የሀይማኖት ተቋማት ምዕመናን ተገቢውን የጥንቃቄ እርምጃ የማድረግ ግዴታ እንዳለባቸው አቶ ሙንጠሻ የገለፁ ሲሆን ማስክ የመጠቀም ርቀትን የመጠበቅና ንፅህና መጠበቂያ ውሀና ሳሙና ወይንም ሳኒታይዘር ተቋማቱ የማዘጋጀት ግዴታቸውን በተገቢው ሊወጡ እንደሚገባም ተመላክቷል።

ትራንስፖርትን በተመለከተ ከወንበር በላይ ትርፍ ሰው መጫን በግለሰብ 1000 ብር የሚያስቀጣ ሲሆን ባለሁለት እግር ሞተር ተሽከርካሪን ጨምሮ ለማንኛውም አሽከርካሪ, ተሳፋሪና ረዳት ያለማስክ መንቀሳቀስ የተከለከለ ሲሆን ይህን አለማድረግ በግለሰብ ደረጃ በገንዘብ 150 ብር የሚያስቀጣ መሆኑን ኮማንደር ደረሰ ገልፀዋል።

በዚህም ማስክ ያላደረገ ተሳፋሪ የጫነ አሽከርካሪ እንዲሁም ማስክ ያላደረገው ተሳፋሪ ላይ ቅጣቱ የሚጣልም መሆኑንም የፖሊስ መምሪያ ኃላፊው ገልፀዋል።

ስፖርታዊ እንቅስቃሴን በሚመለከት ማንኛውም በስፖርት ቤት ውስጥ የሚደረግ ስፖርታዊ እንቅስቃሴም ተከልክሏል ያሉት አቶ ሙንጠሻ ከቤት ውጭ የሚደረግ ስፖርትን በሚመለከትም ኮቪድ 19ኝን ለመከላከል የሚያስችሉ ጥንቃቄዎችን በተገቢው በመተግበር ሊፈፀም እንደሚገባም አሳስበዋል።

በከተማው ማንኛውንም ድግስ ማካሄድ የተከለከለ መሆኑን የገለፁት ኃላፊው ሰርግና መሰል ብዙ ሰው የሚታደምባቸው ድግሶች የተከለከሉ መሆኑንም አመላክተዋል።

የለቅሶ ስነስርዓትን በሚመለከት ድንኳን መጣል የተከለከለ ሲሆን ቀብር ከ50 ሰው በታች በተገኘበት የጥንቃቄ እርምጃዎችን በተገቢው በመተግበር የሚከናወን መሆኑም አመላክተዋል።

ይህን ተግባራዊ በማያደርግ ማንኛውም ግለሰብ, ተቋማትና ሌሎች አገልግሎት ሰጪዎች ላይ በህግ እርምጃ እንደሚወሰድም በመግለጫው ተመላክቷል።

የሐ/ከ/አስ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ
መጋቢት/24/2013ዓም
ሐዋሳ

Comments

Popular posts from this blog

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

የለበሰው ያደፈ ቁምጣና ሹራብ ከቅዝቃዜው አላዳነውም፡፡ ካፊያው ልብሱን አርሶታል፡፡ ሽው እያለ ከሐይቁ የሚነሳው ነፋስ የሚፈጥረው ቅዝቃዜ ያንቀጠቅጠዋል፡፡ የተጫማው ያረጀ ሲሊፐር እግሩን ከምንም አላዳነውም፡፡ በባዶ እግሩ የሚራመድ ያህል ጨቅይቷል፡፡ ተደባዳቢ ይመስል ፊቱ የተሞነጫጨረ ነው፡፡ ገና 12 ዓመቱ ቢሆንም፣ ቁመናው እንደ ትልቅ ሰው ግዙፍ ነው፡፡ የሚለብሰውን እንደ ልቡ ባያገኝም፣ የሚያስፈልገውን ነገር ለማሟላት ቤሳቢስቲን የሌላቸው ወላጆቹን አያስቸግርም፡፡ ከቤተሰቦቹ ጋር ከሚኖሩበት ታቦር ተራራ ጀርባ ወዳለው ሐዋሳ ሐይቅ ከወረደ እንኳንስ የራሱን የቤተሰቦቹንም የዕለት ጉርስ የሚሸፍንበት ገንዘብ አያጣም፡፡ የአስጎብኚነት ዕውቀት፣ ከሐይቁም ውስጥ ዓሳ የሚያጠምድበት መረብም ሆነ ፈቃድ የለውም፡፡ ሙሉቀን (ስሙ ተቀይሯል) እና ጓደኞቹ ሐይቁን ለመጎብኘት የሚሄዱ ጎብኚዎች በካሜራቸው ጥሩ ፎቶ እንዲያስቀሩ ድባቡን የማሳመር ሥራ ይሠራሉ፡፡ ካሜራውን ይዞ ቁጭ ብድግ እያለ ጥሩ ፎቶ ለማንሳት ጥረት የሚያደርግ ሲያዩ፣ ቆርጠው የያዙትን የዓሳ ሥጋ ይዘው ጠጋ ጠጋ ይላሉ፡፡ ቁርጥራጩን የዓሳ ሥጋ ምግብ ለሚቀሙት አባኮዳዎች ሻሞ ይላሉ፡፡ የተወረወረላቸውን ቀድመው ለመቅለብ አባኮዳዎቹ ክንፋቸውን እየመቱ ወደ ላይ ብድግ ይላሉ፡፡ የናሽናል ጆግሪፊ የፎቶግራፍ ባለሙያዎች ያነሱት ዓይነት ፎቶዎች ሳያስቡት ያነሳሉ፡፡ በሁኔታው ተደስተው ደጋግመው ድንቅ ፎቶዎችን ለመውሰድ ሲዘጋጁ እነ ሙሉቀንም አጀንዳቸውን ይፋ ማድረግ ይጀምራሉ፡፡ አቶ ዳዊት አብርሃም ‹‹አንዱን ዓሳ በአሥር ብር ገዝቼ ነው እንዲህ የማዘጋጀው፤›› በማለት በቅድሚያ  መረጃ ይሰጣሉ፡፡ ለቀጣዩ ዜና በዚህ መልኩ እንዲዘጋጁ ካደረጉ በኋላ፣ ሌሎች ሰዎች መቶም ሁለት መቶም ብር እንደሚሰጧቸው ቀለል

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የመንግሥት ስልጠና የምርጫ ቅስቀሳ አካል ነው ብሏል  የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ለምን ወጣ መባሉ ተገቢ አይደለም - ምርጫ ቦርድ ምርጫ ቦርድ ከኢህአዴግ ተፅዕኖ ሙሉ ለሙሉ ነፃ መሆኑ ሳይረጋገጥና የምርጫ አፈፃፀም ችግሮች ሳይወገዱ የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ለማወጅ መዘጋጀቱ ተገቢ አይደለም ሲል ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ የሚመሩት ኢማዴ-ደህአፓ ተቃወመ፡፡ መንግስት፤ የዩኒቨርሲቲ መምህራንና ተማሪዎችን ጨምሮ ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየሰጠ ያለው ስልጠና የምርጫ ቅስቀሳ አካል ነው ሲልም ፓርቲው ኮንኗል፡፡  የኢትዮጵያ ማህበረ ዴሞክራሲ ደቡብ ህዝቦች አንድነት ፓርቲ ሰሞኑን ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ባስገባው ግልፅ ደብዳቤ፤ ያለፉት አገር አቀፍና የአካባቢ ምርጫዎች ከመካሄዳቸው በፊት በምርጫ ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው ዙሪያ ኢህአዴግ ከተቃዋሚዎች ጋር የሚወያይበት መድረክ እንዲዘጋጅ በተደጋጋሚ ብንጠይቅም እስካሁን ከቦርዱ የተሰጠ ተግባራዊ ምላሽ የለም ብሏል፡፡  ሃገሪቱ “በአንድ አውራ ፓርቲ” ብቸኛ ቁጥጥር ስር መውደቋ አደገኛና አሳሳቢ ነው ያለው ፓርቲው፤ የመድብለ ፓርቲ ስርአት የመገንባት ተስፋችን ጨርሶ እንዳይከስም ቦርዱ ሃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት አሳስቧል፡፡ ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ የሚካሄድበትን ሁኔታ ለመፍጠር ገዥው ፓርቲና ሃቀኛ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚወያዩበት መድረክ እንዲያመቻች በህግ ስልጣን የተሰጠው ምርጫ ቦርድ የገባውን ቃል በማጠፍ መድረኩን ሳያመቻች የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማዘጋጀቱ ፋይዳ የለውም ብሏል - ፓርቲው፡፡  ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ በተሻሻለው የምርጫ ህግ፣ ለቦርዱ የተሰጠውን የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ መድረክ የማስተባበር ስልጣን ለመቀማት ታማኝ ፓርቲዎችን በተቃዋሚ ስም አሰባስቦ “የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ መድረክ” በመፍጠር የምርጫ ውድድር አሯሯጭ አሰልፏል ሲ

የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል ማለፊያ ነጥብ ውጤት ነገ ይፋ ይሆናል

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 23 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) የ10ኛ ክፍል ማጠቃለያና የ12ኛ ክፍል መሰናዶ ማለፊያ ነጥብ ውጤትን ነገ ይፋ እንደሚያደርግ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። የዩኒቨርስቲ መግቢያና ወደ መሰናዶ ማለፊያ ነጥብን ለመወሰን  ፥ የዩኒቨርስቲዎችን ቀጣይ የመቀበል አቅም ከግምት ውስጥ በማስገባት መወሰኑንም ነው ሚኒስቴሩ የገለጸው። በአጠቃላይ 548 ሺህ 138 ተማሪዎች የ10 ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተናውን ወስደው 70 በመቶዎቹ 2 ነጥብ እና ካዛ በላይ ውጤት ሲያስመዘግቡ ፥ በተመሳሳይም የ12ኛ ክፍልን የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተናን ከወሰዱት መካከል 70 በመቶ የሚሆኑት ተፈታኞች ከ350 ነጥብ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውን ቀደም ሲል  የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና የፈተናዎች ኤጀንሲ አስታውሷል ። በነገው እለትም የሁለቱም ፈተናዎች የመቁረጫ ውጤት ይፋ ይደረጋል ተብሏል።