በሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ዘንድ አንቱታን ያተረፉት አቶ ተፈራ ዊላ፤ በብዙዎች ዘንድ የሚታወቁት “ለተቸገረ ሁሉ ደራሽ” በመሆናቸው ነው። ይህ የበጎ አድራጎት ተግባራቸው በሀዋሳ ብቻ ሳይሆን በብዙ የሀገሪቱ ክፍሎች በርካታ ወዳጅ እንዳፈራላቸው የቅርብ ሰዎቻቸው ይናገራሉ። ተጨዋች እና በቀላሉ ተግባቢ መሆናቸውም ለዕውቅናቸው እንዲናኝ ምክንያት ሆኗል። “የሆስፒታልን ደጃፍ እምብዛም ረግጠው አያውቁም” የሚባልላቸው አቶ ተፈራ፤ ከሰሞኑ ወደ ህክምና ተቋም ጎራ እንዲሉ ያደረጋቸው የህመም ስሜት ገጥሟቸው ነበር። የህመሙ ስሜት በመጀመሪያ “ጉንፋን ነው” በሚል ችላ ብለውት የነበረ ቢሆንም፤ ከቀናትም በኋላ አለመጥፋቱ ግን በቅርብ ሰዎቻቸው ጥርጣሬ ማስከተሉ ለነገሩ ትኩረት እንዲሰጡ አስገድዷቸዋል። የአቶ ተፈራ ወዳጆች ከህመማቸው ምልክት ተነስተው የተጠራጠሩት “ምናልባትም በሽታው ኮሮና ሳይሆን አይቀርም” የሚል ነበር። ቅዳሜ መጋቢት 18፤ 2013 ወደ ሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል የሄዱት አቶ ተፈራ፤ ኮሮና ይኖርባቸው እንደው ለማወቅ ናሙና ከሰጡ በኋላ ውጤታቸው እስኪታወቅ በህክምና ተቋም እንዲቆዩ ይደረጋሉ። ከሁለት ቀናት በኋላ የመጣው የምርመራ ውጤት ታዲያ የቅርብ ሰዎቻቸውን ጥርጣሬ ያረጋገጠ ሆነ። ውጤቱ ከጠበቁት በተቃራኒ የሆነባቸው አቶ ተፈራ፤ የጤና ባለሙያዎች የነገሯቸውን ለማመንም ሆነ ለመቀበል ተችግረው እንደነበር የሚያውቋቸው ይናገራሉ። በኮሮና ቫይረስ እንደተጠቁ ማወቃቸው የፈጠረባቸው ጭንቀት የጤንነታቸው ሁኔታ በከፍተኛ ሁኔታ እንዲያሽቆለቆል ሰበብ መሆኑንም ይገልጻሉ። የአቶ ተፈራ ሁኔታ ያሳሰባቸው የህክምና ባለሙያዎች፤ የአተነፋፈስ ስርዓት እንዲስተካከል የሚያግዘውን ኦክስጅን ሊያጠልቁላቸው ሙከራ ቢያደርጉም፤ ኸህመምተኛው የገጠማቸው ብርቱ እምቢተኝነት ግን ያሰቡትን ማ
የለበሰው ያደፈ ቁምጣና ሹራብ ከቅዝቃዜው አላዳነውም፡፡ ካፊያው ልብሱን አርሶታል፡፡ ሽው እያለ ከሐይቁ የሚነሳው ነፋስ የሚፈጥረው ቅዝቃዜ ያንቀጠቅጠዋል፡፡ የተጫማው ያረጀ ሲሊፐር እግሩን ከምንም አላዳነውም፡፡ በባዶ እግሩ የሚራመድ ያህል ጨቅይቷል፡፡ ተደባዳቢ ይመስል ፊቱ የተሞነጫጨረ ነው፡፡ ገና 12 ዓመቱ ቢሆንም፣ ቁመናው እንደ ትልቅ ሰው ግዙፍ ነው፡፡ የሚለብሰውን እንደ ልቡ ባያገኝም፣ የሚያስፈልገውን ነገር ለማሟላት ቤሳቢስቲን የሌላቸው ወላጆቹን አያስቸግርም፡፡ ከቤተሰቦቹ ጋር ከሚኖሩበት ታቦር ተራራ ጀርባ ወዳለው ሐዋሳ ሐይቅ ከወረደ እንኳንስ የራሱን የቤተሰቦቹንም የዕለት ጉርስ የሚሸፍንበት ገንዘብ አያጣም፡፡ የአስጎብኚነት ዕውቀት፣ ከሐይቁም ውስጥ ዓሳ የሚያጠምድበት መረብም ሆነ ፈቃድ የለውም፡፡ ሙሉቀን (ስሙ ተቀይሯል) እና ጓደኞቹ ሐይቁን ለመጎብኘት የሚሄዱ ጎብኚዎች በካሜራቸው ጥሩ ፎቶ እንዲያስቀሩ ድባቡን የማሳመር ሥራ ይሠራሉ፡፡ ካሜራውን ይዞ ቁጭ ብድግ እያለ ጥሩ ፎቶ ለማንሳት ጥረት የሚያደርግ ሲያዩ፣ ቆርጠው የያዙትን የዓሳ ሥጋ ይዘው ጠጋ ጠጋ ይላሉ፡፡ ቁርጥራጩን የዓሳ ሥጋ ምግብ ለሚቀሙት አባኮዳዎች ሻሞ ይላሉ፡፡ የተወረወረላቸውን ቀድመው ለመቅለብ አባኮዳዎቹ ክንፋቸውን እየመቱ ወደ ላይ ብድግ ይላሉ፡፡ የናሽናል ጆግሪፊ የፎቶግራፍ ባለሙያዎች ያነሱት ዓይነት ፎቶዎች ሳያስቡት ያነሳሉ፡፡ በሁኔታው ተደስተው ደጋግመው ድንቅ ፎቶዎችን ለመውሰድ ሲዘጋጁ እነ ሙሉቀንም አጀንዳቸውን ይፋ ማድረግ ይጀምራሉ፡፡ አቶ ዳዊት አብርሃም ‹‹አንዱን ዓሳ በአሥር ብር ገዝቼ ነው እንዲህ የማዘጋጀው፤›› በማለት በቅድሚያ መረጃ ይሰጣሉ፡፡ ለቀጣዩ ዜና በዚህ መልኩ እንዲዘጋጁ ካደረጉ በኋላ፣ ሌሎች ሰዎች መቶም ሁለት መቶም ብር እንደሚሰጧቸው ቀለል