በ13 ቢሊዮን ብር በመካሄድ ላይ ያለው የሞጆ ሐዋሳ የፍጥነት መንገድ ለምን ለአመታት ተጓተተ በ13 ቢሊዮን ብር በመካሄድ ላይ ያለው የሞጆ ሐዋሳ የፍጥነት መንገድ ላለፉት በርካታ አመታት ግንባታው ከምገባው በላይ በመጓተት ላይ በመሆኑ፤ ጉዳዩ የሚመለከተው የሲዳማ እና የኦሮሚያ ክልል መንግስታት፤ መንገዱ ለአገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እድገት ካለው ፋይዳ አንጻር አንድ ሊሉ ይገባል። ግንባታው ከተጀመረ በርካታ አመታትን ያስቆጠረው የሞጆ ሐዋሳ የፍጥነት መንገድ፤ ግንባታው በአራት ምእራፍ ተከፍሎ በመካሄድ ላይ ያለ ሲሆን፤ ባለፉት በርካታ አመታት ከአራቱ ምእራፎች አንዱ የሆነው ከሞጆ መቂ ድረስ ያለው የመንገድ ግንባታ ብቻ ከ80 ከመቶ በላይ የደረሰ ሲሆን፤ የተቀሩት የግንባታ ምእራፎች ግን በተለያዩ ችግሮች የተነሳ እስከአሁን ድረስ ግንባታቸው መድረስ ከምገባው የግንባታ ደረጃ ላይ መድረስ አልቻሉም። የመንገድ ግንባታው ከአራት የተለያዩ ባንኮች በተገኘ የገንዘብ ወደ 13 ቢሊዮን ብር ብድር እና ድጋፍ የሚሰራ ሲሆን፤ የመንገዱ ግንባታ በዚህ መልኩ መጓተቱ፤ በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ካለው አሉታዊ ፋይዳ አንጻር፤ የሁለቱ ክልል መንግስታት ከፌዴራል መንግስት ጋር በመቀናጄት፤ የፍጥነት መንገድ ግንባታው ያጋጠመውን የወሰን አከላለል እና መሰል ችግሮች በመፍታት፤ የሁለቱን ክልሎች ህዝቦች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን የማረጋገጥ ስራ ልሰሩ ይገባል። በተለይ የሲዳማ ክልል መንግስት፤ በክልሉ ካሉ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ለአለም ገበያ የሚቀርቡትን የተለያዩ የኢንዱስትሪ እና የግብርና ምርቶችን በከፍተኛ ፍጥነት ለገበያ ለማድረስ ይቻል ዘንድ የዚህ መንገድ መጠናቀቅ ካለው ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ አንጻር፤ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥተው መስራት አለባቸው። ከዚህም በተጨማሪ ከአዲስ አበባ ወደ ሐዋሳ ያለው
It's about Sidaama!