ሚኒስተር መስሪያ ቤቱ የመስክ ቡድን በዛሬ እለት በሀዋሳ ከተማ በሃይሌ ሪዞርት ከሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክትል ርዕስ መስተዳደርና ትምህረት ቢሮ ኃላፊ አቶ በቀለ ቱንሲሳ መድረክ መሪነት ከክልሉ ንግድ ቢሮ እና ስራ ፈጠራና ኢንዱስትሪ ቢሮ፣ ከክልል እስከ ዞንና ወረዳ ድረስ ያሉ ኃላፊዎች ጋር ተወያይቷል፡፡
በውይይቱ የኢፌዴሪ ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በ2013 በመጀመሪያው በጀት ዓመት በተከናወኑ ተግባራት እና በሁለተኛው ግማሽ ዓመት በትኩረት ሊሰሩ በሚገቡ ጉዳዮች ላይ የመስክ ጉብኝት ባደረጉበት እና በክልሉ የሚገኙ የግል ዘርፍ የወጪ ንግድ ፣የመሠረታዊ ሸቀጦች ፣ በኢንዱስትሪ ላይ ያሉ የግብይት ተዋንያዎች ጋር በተደረጉ ውይይቶች መነሻ በክልልና ዞን የሚፈቱትን ለመፍታት እንዲሁም መፍታት በመይቻሉ ጉዳዮች ላይ በኢፌዴሪ ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ለበላይ አመራር በሚቀርቡ ቀጣይ መፍትሔ በሚሰጥባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡
ከዚህም ባሻገር በሲዳማ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ያለፉት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ውይይት መደረጉን የሚኒስተር መስሪያ ቤቱን ጠቅሶ ወራንቻ ዘግቧል፡፡
Comments
Post a Comment