የኢፌዴሪ ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በ2013 በመጀመርያው በጀት አመት በተከናወኑ ተግባራት እና በሁለተኛው ግማሽ ዓመት በትኩረት ሊሰሩ በሚገቡ ጉዳዮች ላይ የመስክ ጉብኝት እና የክትትል ስራ እያከናወነ ነው
የፌደራል መስክ ቡድን ዋና አላማ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት እና በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በተጨባጭ እየተከናወኑ ያሉ የልማትና የንግድ ስራዎችን በመመልከት በጥንካሬና በጉድለት ያሉ ጉዳዮችን ከፌደራል መስሪያ ቤቱ ጋር በተቀናጀ ሁኔታ በጎ ጎኖችን የበለጠ አሳድጎ ለሌሎች ክልሎችም ልምድ እንዲወስዱ ማድረግ ጉለቶችን ደግሞ በተናጥልም ሆነ በጋራ ከክልሎችና ከፌደራል ጋር የሚቀርፍበትን ሁኔታ ለመፍጠር መሆኑነን የፌደራል መስክ ቡድን መሪ ኦቶ ስለሺ ለማ ተናግረዋል፡፡
በመስክ ጉብኝቱ በተለይም በሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሃያ ሁለት ድርጅቶች ገብተው ምርት እያመረቱ መሆኑንና ፋብሪካዎችና ባለሃብቶቹንን ለመደገፍ የአንድ መስኮት አገልግሎት የተለያዩ መስሪያ ቤቶች በቅንጅት ድጋፍና አገልግሎት እየሰጡ መመልከታቸውን ገልፀዋል::
በዋናነት በቅንጅት መሠራቱ ብዙ ችግሮችን ለመፍታት የሚቻልበትን ተሞክሮ እንዳለ የተየበት መሆኑን አቶ ስለሺ ጠቁመው በተለይም ከግብርናው ዘርፍ ትስስር ፈጥሮ እና የኢንደስትሪውን ዕድገት በፍጥነት ለማቀላጠፍ ትልልቅ ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን አስታውሰዋል፡፡
በይርጋ አለም ግብርና ማቀነባበርያ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሁለት ፋብሪካዎች ስራ እየጀመሩ ያለበት ሁኔታ መመልከታቸውንና ዶሊ ፉድ ፕሮሰሲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የወተት አቀናባሪ ድርጅት ከአስራ ሁለት ሺህ በላያ ገበሬዎች ተለይተው ከአምስት ሺህ ገበሬዎች ጋር ትስስር የተፈጠረ ሲሆን እንዲሁም ሰንቫዶ ማኑፋክቸሪንግ የአቡካዶ ዘይቱን ከሰባ ሰባት ሺህ ገበሬዎች ጋር ትስስር መፈጠሩ አበራታች መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
የፌደራል መስክ ቡድኑ በኢትዮጵያ ምርት ገበያ መቀበያ መጋዘን ቅርንጫፍ በተለይም የቡና የምርት ቅበላና የጥራት ደረጃ አሰጣጥ ሂደትን መመልከታቸውን ኦቶ ስለሺ ለማ ገልፀው በቀጣይ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት እና በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አመራሮች ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ አቶ ስለሺ አስታውቀዋል፡፡
ምንጭ፤ ንኢሚ
Comments
Post a Comment