Skip to main content

Posts

Showing posts from January, 2021

Yirgalem Integrated Agricultural Products Processing Industrial Park is expected to contribute significantly to foreign exchange earnings

Yirgalem Integrated Agricultural Products Processing Industrial Park is expected to contribute significantly to foreign exchange earnings. According to the Ministry of Trade and Industry, the Integrated Agricultural Products Processing Industrial Park uses more than 90 percent of its inputs from domestic production. The park is being developed on 300 hectares of land in the first phase and the rural centers are being developed on 10 hectares each. The infrastructure and construction stages that the park needs to meet the food industry industry are being fully developed. By http://www.motin.gov.et/ 

11ኛው ሀገር አቀፍ የአብሮነት ቀን በሀዋሳ ከተማ ሰሞኑን ተከብሯል

የአብሮነት ባህላችን ለዘላቂ ሰላማችን በሚል ሀሳብ ዛሬ በሀዋሳ የተከበረው የአብሮነት ቀን በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴርና በሲዳማ ብሔራዊ  ክልላዊ መንግስት  ትብብር  የተዘጋጀ ነው። በመድረኩ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የሁሉም ክልሎች ተወካዮች፣ አባገዳዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የኃይማኖት አባቶች፣ የወጣቶችና ሴቶች  አደረጃጀቶችና የህዝብ ተወካዮች ታድመዋል። በበዓሉ መክፈቻ ላይ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ቡዝነሽ መሠረት እንዳሉት የአብሮነት ቀን የመከበሩ ዋንኛ ምክንያት የዓለም ህዝቦች በመልከዐ ምድር አቀማመጥ፣ በቀለም፣ በኃይማኖት፣ በጎሳና በቋንቋ ልዩነቶች ምክንያት  በየጊዜው በሚፈጠሩ  ግጭቶችና አለመግባባቶች የሚያስከትሉትን መጠነ ሰፊ ጉዳት አጉልቶ በማሳየት ለማስገንዘብ ነው። በተለይ አንዱ የሌላውን ሰብዓዊ መብት በማክበርና ከሌሎች ጋር በመቻቻል መኖር ለህዝቦች እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ግንዛቤ ለማስረፅ ጭምር እንደሆነ ገልፀዋል። “በሀገራችን የመቻቻል ቀን ስናከብር በአብሮነት መኖር መርሆዎችን በማስተማር ቅድመ አያቶቻችን ያቆዩልንን ተከባብሮና ተፈቃቅዶ የመኖር ባህላችንን ግንዛቤ በማስጨበጥ  ነው” ብለዋል። “በተለይ አንዱ የሌላውን ማንነት የማክበር ባህል ሳይሸራረፍ እንዲቀጥል የማድረጉ ኃላፊነት የሁሉም ዜጋ መሆኑን በማሳወቅ ልዩነቶችን በመግባባትና በሠላማዊ መንገድ ብቻ እንዲፈቱ ለማስቻል መድረኩ መማማሪያ ይሆናል” ያሉት። የሲዳማ ክልል ባህል፣ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃጎ አገኘው በበኩላቸው የሲዳማ ህዝብ በሰው ልጅ ማህበራዊ ህይወት ውስጥ አይቀሬ የሆነውን ግጭት የሚፈታበት  “ አፊኒ ”  የተሰኘ ብርቅዬ የእርቅ ሥርዓት ባለቤት መሆኑን ገልጸዋል። አፊኒ እስከ ነፍስ ግድያ ያሉ ጥፋቶች እውነታውን በጥሞና በመመርመር እርቅ ማውረ

ሲዳማ - ኦሮሚያ እርቀ ሰላም ||NahooTv

በሲዳማ ክልል በተለያዩ ወረዳዎች የግብርና መካናይዘሽን እርሻ ስራ መጀመሩ ተሰማ

በሲዳማ ክልል በተለያዩ ወረዳዎች የግብርና መካናይዘሽን እርሻ  ስራ መጀመሩ ተሰማ   የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ በተያዘው በ2013 በጀት ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ በሎካ አባያ ወረዳ የግብርና መካናይዘሽን እርሻ ስራ ያስጀመረ ሲሆን፤ ስራው በቀጣይነት በተለያዩ ወረዳዎች ተግባራዊ እንደሚሆን በክልሉ ግብርና ቢሮ የቢሮ ምክትልና የእርሻ ዘርፊ ኃላፊ ካላ ክፍሌ ሻሾ ገልፀዋል።  የግብርና መካናይዘሽን እርሻ ማጠናከር የግብርናን ምርትና ምርታማነትን ከማሳደግ አልፎ ጊዜና ወጪ ቆጣቢ ዘመናዊ የእርሻ ስራ ተግባራዊ ለማድረግ ያስችላል ተብሏል።  እንደ ካላ ክፍሌ ከሆነ፤ በግብርና መካናይዘሽን በትራክተር እርሻ የሚለማ 63,188 ሄክታር መሬት በበቆሎ ዘር በመሸፈን 3,035,873 ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ በእቅድ የተያዘ ሲሆን፤ በዚህም 229,632 አ/አደሮች ተጠቃሚና ተሳታፊ ይሆናሉ።  የተጀመረው ይኸው ስራ ወደ 30 የእርሻ ትራክተሮችን ትስስር በመፍጠር በኪራይ እንዲሳተፉ የተደረገ መሆኑ የተነገረ ሲሆን፤ ወደፊትም አርሶ አደሮች በቡድን እየተደራጁ በግላችን የእርሻ ትራክተር በመግዛት የግብርና መካናይዘሽንን ስራ የሚያስፋፉበት እድል እንደሚኖር ተሰፋ እንዳላቸው በመካናይዘሽንበ ስራ ላይ የተሳተፉ አርሶ አደሮች መናገራቸው ተሰምቷል።

Ethiopia: ጥብቅ መረጃ - እውን ዶ/ር አብይ አህመድ ሞቶ ቢሆንስ ኖሮ? | Dr Abiy Ahmed

የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር 2 የተለያዩ ፕሮጀክቶች ግንባታ ስራን አስጀመረ

የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ ረዳት ፕ/ር ፀጋዬ ቱኬ የአረጋውያን መዋያ ማዕከላት የግንባታ ፕሮጀክት እንዲሁም በ600 ካ.ሜ ቦታ ላይ የሚያርፍ የአርሶ አደሮች ምርት መሸጫ የገበያ ማዕከል የግንባታ ስራ በዛሬው ዕለት የተለያዩ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በይፋ አስጀምረዋል።  የአረጋውያን መዋያ ማዕከላቱ በ8ቱም ክፍለከተማ ተደራሽ በሆኑ አካባቢዎች በአጠረ ግዜ ውስጥ ደረጃ በደረጃ ተገንብተው አረጋውያን በዝቅተኛ ወጪ እየተዝናኑ የሚውሉባቸው መሆናቸውን ክቡር ከንቲባው አመላክተዋል።  ይህችን ሀገር ጠብቀው ለአሁኑ ትውልድ ከማሸጋገር ረገድ አረጋውያን ላበረከቱት አስተዋጽኦ የሚመጥን እንክብካቤ ያስፈልጋቸዋል ያሉት ክቡር ከንቲባው ከተማ አስተዳደሩ ይህን ሁለንተናዊ ጠቀሜታ ያለው የአረጋውያን ማቆያ ማዕከል በአጭር ጊዜ ውስጥ አስገንብቶ ጥቅም ላይ የሚያውል መሆኑንም አመላክተዋል።   በ600 ካ.ሜ መሬት ላይ የሚያርፍ  የአርሶ አደሮች መርት መሸጫ የገበያ ማዕከል ግንባታ ፕሮጀክት ክቡር ከንቲባው በዛሬው ዕለት በይፋ ያስጀመሩት ሌላኛው ፕሮጀክት ሲሆን ይህም ፕሮጀክት የዲዛይን ስራው ተጠናቆ የግንባታ ስራው በዛሬው ዕለት በይፋ ተጀምሯል።  ከቦታ መረጣ ጀምሮ በቅርበት  አርሶአደሩን ታሳቢ በማድረግና የትራንስፖርት አገልግሎት በበቂ ሁኔታ የሚገኝበት አካባቢ የገበያ ማዕከሉ የሚገነባ መሆኑ ሸማቹንና አርሶአደሩን በቀጥታ የሚያገናኝ መሆኑንም ክቡር ከንቲባው ጠቁመዋል።  አርሶ አደሮች በምቹ የመሸጫ ቦታ እጦት ምርታቸውን ተገቢነት በሌለው ዋጋ ከመሸጥ ያነሳ ለተለያዩ ችግሮች ሲጋለጡ መቆየታቸውን የገለፁት ረዳት ፕ/ር ፀጋዬ ቱኬ አዲሱ የገበያ ማዕከል ግንባታ ሲጠናቀቅ ምቹ የገበያ ትስስር የሚፈጥር ከመሆኑ በተጨማሪ የግብይት ሰንሰለቱን በማሳጠር የአርሶ አደሩንና የሸማቹን ቀጥተ

በሲዳማና በወንድም ኦሮሞ ህዝብ መካከል የተከሰተውን ግጭት ለማስቀረት በሐዋሳ ዙሪያና ሥራሮ ወረዳዎች ነዋሪዎች መካከል የእርቅና የሠላም ኮንፎራንስ ተካሄደ

በህዝቦች መካከል ሠላምን እና ወንድማማችነትን መፍጠር ለሀገር ሠላምና ለዴሞኪራሲ ግንባታ ያለው ፋይዳ የጎላ መሆኑን የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሠላምና ፀጥታ ቢሮ እና ኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምዕራብ አርሲ ዞን ሠላምና ፀጥታ መምሪያ ገለፁ። በሲዳማና በወንድም ኦሮሞ ህዝብ መካከል የተከሰተውን ግጭት ለማስቀረት በሐዋሳ ዙሪያና ሥራሮ ወረዳዎች ነዋሪዎች መካከል የእርቅና የሠላም ኮንፎራንስ ተካህደዋል። የእርቅና ሠላም ኮንፎራንስ ሥነሥርዓት የተጀመረው በሁለቱም ብሔር ሀገር ሽማግሌዎችና በአባ ገዳዎች ምርቃት ሲሆን ሽማግሌዎችና አባገዳዎች ባስተላለፉት መልዕክት ሁለቱም ወገን እርስ በእርስ በጋብቻ ፤ በማህበራዊ ኑሮ የተሳሰራችሁ በመሆናችሁ ከእርስ በእርስ ጥል እና መገፋፋት ወጥታችው ከጥንት አባቶቻችሁ የወረሳችሁትን ወንድማማችነት ባህላችሁን በማዳበር ለሀገራችሁ ሠላም ዘብ ልትቆሙይገባልብለዋል። የሐዋሳ ዙሪያ ወረዳ ዋና አስተዳደር አቶ ብርሃኑ ኦንዳሞ እና የሥራሮ ወረዳ ዋና አስተዳደር አቶ ማህመድ ማቲ በጋራ በሰጡት አስተያየት የሲዳማና የኦሮሞ ህዝብ ከረጅም ጊዜ ጀምሮ እርስ በእርስ በመከባበር፣ በመቻቻልና በመረዳዳት የኖሩ፤ በደም የተዋሄዱ ህዝቦች መሆናቸውን ጠቅሰው ለጥልና ብጥብጥ እንዲሁም ለደም መፋፈስ የሚያበቃቸው መነሻ ለህብረተሰቡ ኖረዋቸው ሳይሆን የግል ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ የሚሯሯጡ ኃላ ቀር ፖለቲከኞች በመሆኑ ሁለቱም ወንድም ህዝብ ይህንን ተረድተው ሠላሙን በእራሱ እንዲጠብቅ አስተውቀዋል። የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቴዎስ በኮንፈረንሱ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ሀገራችን ኢትዮጵያ ከአደጉት ሀገራት ተርታ በእድገት ማማ ለማሰለፍ እየተረባረበ እንደሚገኝ አስታውሰው ባለፉት አመታት የአንድ ብሔር በ

የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ም/ርዕሠ መስተዳደርና የት/ት ቢሮ ኃላፊ፣ ከኃላፊነት መነሳታቸው ተገለፀ

የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ም/ርዕሠ መስተዳደርና የት/ት ቢሮ ኃላፊ፣ ከኃላፊነት መነሳታቸው ተገለፀ። ሀዋሳ፣ ሲዳማ ጥር 18/2013 የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ም/ርዕሠ መስተዳደርና የት/ት ቢሮ ኃላፊ ካላ በቀለ ቱንሲሳ ከኃላፊነት መነሳታቸው ተገልፆል። ካላ በቀለ ተንሲሳ ክልሉ ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምረው፣ ክልሉን በም/ርዕሰ መስተዳደርነትና በት/ት ቢሮ ኃላፊነት ሲመሩ የቆዩ ሲሆን፣ የክልሉ የበላይ አመራሮች ለተከታታይ ሁለት ቀናት ሲያካሄዱ በነበረው የአፈፃፀም ክንውን ግምገማና የአመራር እንዲሁም የአባላት ግምገማ ውጤት ግምገማ መድረክ መነሳታቸው ተነግሯል። ኃላፊው ላለፉት ጊዜያቶች ከወረዳ እስከ ክልል በተለያዩ በመንግስትና በድርጅት ኃላፊነት ቦታዎች ህዝቡን ሲያገለግሉ የቆዩ ከመሆናቸውም በላይ ከክልል ምስረታው ጀምረው እስከአሁን ድረስ በተመደቡበት የመንግስት ኃላፊነት የበኩላቸውን ሚና የተወጡ ነባር አመራር መሆናቸውም ተገልፆል። ሆኖም ተቋሙን በቀጣይነት ለማሻገር ሲባል ይህ የእርምት እርምጃ መወሰዱም ታክሎበታል። የወሬው ምንጭ ትምህርት ቢሮው ነው

Dire Dawa Hammers Adama, Hadiya and Hawassa in Stalemate

Dire Dawa Ketema emerged victorious over Adama Ketema in round 9 of the BetKing Ethiopian Premier League as Hadiya Hossana and Hawassa Ketema settled for a barren draw in the last fixture of the week. The Easterners put three past Adama Ketema to end their successive winless streak. It was a good day for head coach Fisseha Tumelsan and his charges as they achieved their biggest win of the season so far in the game played out at the Jimma University Stadium. Dire Dawa Ketema were wasteful but they still managed to win the encounter 3-0. Muhdein Musa opened the scoring in the 15th minute after Namibian striker Junias Nandjebe failed to convert the easiest chances of the tie. Musa, who happens to be a Dire Dawa native, was on a beast mode as he extended the lead 9 minutes later. Asechalew Girma struck the third goal minutes following the resumption of the second half. Adama Ketema looked very shaky at the back as well as rusty in front. The win took Dire Dawa Ketema to 8th with 10 points.

የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ኮሮናን በመከላከል ምርት እንዳይስተጓጎል ያደረገው ጥረት ለሌሎች ምሳሌ የሚሆን ነው – የንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ኮሮናን በመከላከል የምርት ሂደቱ እንዳይስተጓጎል እያደረገ ያለው ጥረት ለሌሎችም ተቋማት ምሳሌ እንደሚሆን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አስታወቀ። የኮሚቴው አባላት በፓርኩ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን የቡድን መሪው አቶ ዘውዱ ከበደ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ ፈሶባቸው የተቋቋሙት የሥራ ዕድል ፈጠራን፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርን እንዲሁም የውጭ ምንዛሪን ለማሳደግ መሆኑን አስረድተዋል። በዚህ ረገድ የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከመንግስት የተሰጠውን ተልዕኮ እየተወጣ መሆኑን ባደረጉት ቅኝት ማረጋገጣቸውን ጠቅሰዋል። በተለይ ኮሮናን መከላከል መሠረት ባደረገ መልኩ በውስጡ ያሉ ኩባንያዎች ሳይዘጉ ሥራቸውን እንዲቀጥሉ በማድረግ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴው የከፋ ጫና ውስጥ እንዳይገባ ያደረገው ጥረት ውጠታማ መሆኑን አስረድተዋል። በኩባንያዎች ውስጥ የተቀጠሩ ሠራተኞች የሚከፈላቸው ደመወዝ አነስተኛ እንደሆነ መረዳታቸው የገለጹት አቶ ዘውዱ በጊዜ ሂደት ማሻሻያዎች በማድረግ የሚስተካከል እንደሆነም ተናግረዋል። አሁን ላይ የሠራተኛው ደመወዝ ከፍ በማድረግ መደገፍ ባይቻልም በተለይ የመኖሪያ ቤት

Bacterial Profile, Antibiotic Susceptibility Pattern and Associated Factors Among Patients Attending Adult OPD at Hawassa University Comprehensive Specialized Hospital, Hawassa, Ethiopia.

Background: Urinary tract infection (UTI) is a common health problem occurring when infectious agents colonize, invade, and propagate the urinary tract including the urethra, bladder, renal pelvis, or renal parenchyma. The study aimed to determine the prevalence of symptomatic UTI, drug resistance pattern, and its associated factors among patients attending adult outpatient department (OPD) at Hawassa University Comprehensive Specialized Hospital (HUCSH). Methods: A cross-sectional study was conducted from October 2018 to February 2019 among adults ≥18 years old with symptoms of UTI. Processing of specimens for culture and identification was done. Antimicrobial susceptibility was done for positive urine cultures. Data entry and analysis were performed using SPSS version 23.0 software. Bivariate and multivariate logistic regression analysis test results were used. Results: The overall prevalence of symptomatic urinary tract infection was 32.8% (95% CI: 28.3-37.6). The predominant isolat

Excessive intake of iodine and low prevalence of goiter in school age children five years after implementation of national salt iodization in Shebedino woreda, southern Ethiopia.

Background : Iodine is a trace element required for the synthesis of thyroid hormones. The multiple effects of iodine deficiency on human health are called iodine deficiency disorders (IDDs). IDDs have been common nutritional problems in Ethiopia. In 2012, Ethiopia launched a national salt iodization program to address IDDs. The objective of this study was to assess the effects of this program after 5 years by measuring urinary iodine concentration (UIC) and prevalence of go

A historical moment: the first UiB – Hawassa University joint PhD degree defended

Hawassa University in Ethiopia and the Centre for International Health (CIH) at the University of Bergen (UiB) have had a long-lasting, productive scientific co-operation in Global Health. In 2015, the two universities developed a joint PhD degree programme. The first PhD candidate from this joint degree programme, Moges Tadesse Borde, defended his dissertation 20 January 2021. In these pandemic times, the Defence was held digitally. It led by professor Thorkild Tylleskär from CIH. Borde’s thesis was entitled, ‘Maternal and neonatal health in southern Ethiopia: A cohort study on the incidence of illnesses and utilisation of healthcare service’. The research involved almost 900 women and their newborn babies from South Ethiopia. The women and babies were followed over time and information about their health situation was recorded. While several of the pregnant mothers developed anaemia and hypertension, only few were given any treatment, due to the lack of both health centres and qualif

Ethnic conflict could unravel Ethiopia’s valuable garment industry

Ethiopia has long been considered one of Africa’s economic wunderkinds . Until recently, it had relative political stability in comparison to other countries on the continent. And, with an average GDP growth rate of 10% in the past decade and a government that instituted policies friendly to foreign investors , the country was able to attract South and East Asian clothing manufacturers . These sell to international brands, such as Decathlon and H&M. But, for the past two months, violent conflict in Ethiopia’s northern Tigray region fuelled by ethnic power politics has threatened the country’s stability. According to the International Crisis Group , the violence has likely kille

“የበፊቱን ሐዋሳ ከተማን ለመገንባት ጠንክረን እየሰራን ነው”ብሩክ በየነ

ሐዋሳ ከተማን የአጥቂ ስፍራ በጥሩ ብቃቱ እየመራ ያለው ወጣቱ ተጨዋች ብሩክ በየነ ሲዳማ ቡናን ድል ካደረጉ በኋላ ስለ ቡድናቸው የቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊግ ተሳትፎ ዙሪያ እና ሌሎችንም ጥያቄዎች የሀትሪክ ስፖርቱ ድረ-ገፅ ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ አንስቶለት ምላሽን ሰጥቶበታል። ከሲዳማ ቡና ጋር የነበራቸውን ጨዋታ ስለ ማሸነፋቸው “ጨዋታው ለእኛ በጣም አስፈላጊያችን እና ካሸነፍን ደግሞ ወደ መሪዎቹ ልንጠጋበት የምንችልበት ነበር። በፈጣሪ እርዳታም ግጥሚያውን ድል አድርገን አሸናፊነታችንን ወደ ማጠናከሩ መጥተናል”። ስለ ሲዳማ ቡና “ሲዳማ ቡና ጠንካራ ቡድን ነው። የባለፈው ጨዋታ ላይ ብናሸንፋቸውም ግጥሚያው የወንድማማቾች ደርቢ ከመሆኑ አንፃር ፈትነውን ነበር። በእዛን ዕለቱ ጨዋታ እነሱን በማሸነፋችን ግን በጣም ደስ ብሎኛል”። ስለ ጠንካራ እና ክፍተት ጎናቸው “እንደ ጥንካሬ የማነሳው ቡድናችን የሚያደርጋቸውን እያንዳንዱን ጨዋታዎቹን በህብረት ለማሸነፍ መጫወቱንና እንደ በፊቱ ጎሎችን እምብዛም የማናስተናግድ መሆናችን ነው። ሌላው በክፍተት ደረጃ የማነሳው ደግሞ ብዙ ኳሶችን እናገኝና እነዛን አንጠቀምም”። የሊጉ አጀማመራቸው ላይ ስኬታማ ካለመሆናቸው ጋር ተያይዞ ወራጅ ሊሆኑ ይችላሉ ስለመባላቸው “በትክክል ውድድሩን ስንጀምር እንደ አሁኑ በተሳካ ሁኔታ አልነበረም። ያ ሊሆን የቻለውም የአዲስ አበባ አየር ከብዶን ስለነበር ነው። ያኔም ሐዋሳ ዘንድሮ ይወርዳል የሚል ነገርን እንሰማም ነበር። አሁን ግን ጅማ ላይ ያ ስጋት እኛ ቡድን ጋር እንደሌለ በምናስመዘግባቸው ውጤቶች እያሳየን ይገኛልና ከዚህ በኋላም በሚኖሩን ጨዋታዎች አሸናፊነታችንን በማስቀጠል የበፊቱን ጠንካራውን ሐዋሳ ከተማን የምንገነባ ይሆናል”። ስለ ስብስባቸው “በአብዛኛው በወጣቶች የተገነባ ቡድን ነው ያለን። ጥቂት ሲ

እግር ኳስ በአዲሲቷ ክልል ሲዳማ

አዲሱ የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ከወራት በፊት ራሱን ችሎ በክልል ደረጃ መቋቋሙ ይታወቃል:: በዚህ ሂደትም እንደ አዲስ በመዋቀር ላይ ካሉ ዘርፎች መካከል አንዱ ስፖርት ነው:: ክልሉ በተለይ በእግር ኳስ የተሻለ አቅም ያለው እንደመሆኑ የክልሉን የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ምስረታና እስካሁን የተጓዘባቸውን በተመለከተ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ከሲዳማ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ብሩ ወልዴ ጋር ቆይታ አድርጓል:: አዲስ   ዘመን፡ –  ክልሉ   አዲስ   ክልል   እንደመሆኑ   ፌዴሬሽኑን   ከማደራጀት   አኳያ   ያላችሁበት   ሂደት   ምን   ይመስላል ? አቶ   ብሩ፡ –  የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ወደ ስራ ከገባ ስድስት ወራትን አስቆጥሯል፤ ፌዴሬሽኑም ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እውቅና አግኝቶ ወደ ስራ ገብቷል:: በመሰረታዊነትም የ2013 ዓ.ም እቅድን በማዘጋጀት ስራው የተጀመረ ሲሆን፤ በቅድሚያ የሚከናወኑ ተግባራትም ተለይተዋል:: በዚህ መነሻነትም የቢሮና ሌሎች የአደረጃጀት፣ የሰው ኋይልን ማሟላትን የመሳሰሉ ስራዎች እየተከናወኑ ነው:: በተጨማሪም በክልሉ እየተካሄደ ያለውን የሴቶች ፕሪምየር ሊግ በመደገፍና ከብሄራዊው ፌዴሬሽን ጋር በቅንጅት በመስራት ላይ ይገኛል:: አዲስ   ዘመን፡ –  በዓመቱ   የተቀመጡት   እቅዶች   በዋናነት   ምን   ላይ   ያተኮሩ   ናቸው ? አቶ   ብሩ፡ –  በዚህ ዓመት ለመስራት ከታቀዱ ስራዎች መካከል ዋነኛው ታዳጊ ወጣቶችን በፕሮጀክት በመያዝና ልዩ ትኩረት በመስ

በሲዳማ ክልል ውስጥ ባሉ የኢንቨስትመንት እድሎች እና ከዚሁ ጋር ተያይዞ ተግዳሮች ዙሪያ የተደረገ ውይይት እና የይርጋለም የግብርና ኢንዱስትሪ ግብኝት

በሲዳማ ክልል ውስጥ ባሉ የኢንቨስትመንት እድሎች እና ከዚሁ ጋር ተያይዞ ተግዳሮች ዙሪያ የተደረገ ውይይት እና የይርጋለም የግብርና ኢንዱስትሪ ግብኝት 

ሀገር አቀፍ የአብሮነት ቀን በሀዋሳ በመከበር ላይ ይገኛል

"የአብሮነት ባህላችን ለሰላማችን" በሚል የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከሲዳማ ክልል ጋር በመተባበር አዘጋጅተውታል:: ቀኑ በአለም አቀፍ ደረጃ ለ25ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ11ኛ ጊዜ ነው አየተከበረ ይገኛል:: የፌደራል እና የክልል የመንግስት የስራ ሃላፊዎችን ጨምሮ የሀገር ሽማግሌዎች ፤የጎሳ መሪዎች እና ወጣቶች በስነ ሰርዓቱ ላይ ተገኝተዋል:: በዝግጅቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ብዙነሽ መሠረት ቀኑ የአለም ህዝቦች በቀለም፤ በዘር፤ በሀይማኖት እና በመልካም ምድር አቀማመጥ ልዩነቶች ምክንየት በየጊዜው በሚፈጠሩ ግጭቶች እና አለመግባባቶች የሚያሰከትሉትን መጠነ ሰፊ ጉዳት አጉልቶ በማሳየት አንዱ የሌላውን ሰብዓዊ መብት በማክበር ከሌሎች ጋር በመቻቻል መኖር ለህዝቦች አሰፈላጊ በመሆኑ ግንዛቤ ለማሰረፅ ታሰቦ መሆኑን ገልፀዋል:: ኢትዮጵያ የበርካታ ማንነቶች ሀገር ናት ያሉት ሚኒስትር ዲኤታዋ በየማህበረሰቡ ያሉ አብሮነትን የሚያጎለብቱ ሀገር በቀል እውቀቶችን ማጎልበት እና በየእለት ተእለት መስተጋብራችን ልንጠቀማቸው ይገባል ብለዋል:: በአሁኑ ሰዓት በአብሮነት ላይ ያተኮረ የውይይት መነሻ ፅሁፍ ቀርቦ ውይይት አየተካሄደ ይገኛል፡፡

The Ethiopia’s Dictator PM’s Bribe of his Sidama Cadres is Unionists’ Futile Ploy to Prove the Failure of Federalism in Ethiopia!

January 17, 2021 (By Denboba Natie) I. A Defining Moment that Shattered Unionists' Ambition in Ethiopia The Ethiopia’s then hopeful PM who suddenly became inhumane dictator before completing his 10th month in office has called for a meeting of the then southern nations and nationalities SNNRS’s cadres to inject them with his delusional unionist venom. The PM planned to summon them to Finfinnee (Addis Ababa) on July 19, 2018. The Sidama nation has made a defining history before joining the meeting by making decisive decision. Cognizant of the maliciousness of his intents during the upcoming meeting, the Sidama Zone council motivated by Sidama national popular urge to reignite the Sidama’s quest for national regional State has made urgent call for an extra-ordinary meeting of its council. The Sidama zone’s urgent council meeting summoned and a unanimous decision was made for the Sidama to be a national regional state on 18 July 2018. The indicated quest of the nation was in the top p

Hawassa swept aside Bahir Dar Ketema

Hawassa Ketema came from behind to beat the very inconsistent Bahir Dar Ketema 2-1 in round 7 of the BetKing Premier League fixture played out at the Jimma University Stadium. The Lakers take home another win with Mesfin Tafesse getting in the score sheet. The homers started off the duel on a positive note and almost went ahead when Baye Gezaghen tried to lob Hawassa’s keeper Mensah Shoho. The onslaught carried on for the first 15 minutes as the Waves of Tana looked the better side from the onset. Gezagehen and Girma Desasa were the culprits for squandering some pretty simple chances. However, in the 21st minute Shoho parried away Desasa’s goalbound kick but the Togolese was unable to deny Salamelak Tegegen from scoring with the rebound. The Lakers responded in empathic fashion three minutes later with Tafesse converting from the pref

አልቶ የሙዚቃ ትምህርት ቤት በሀዋሳ

በሀዋሳ ከተማ ከሁለት ቢሊዮን 400 ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሀብቶች ወደ ስራ ገቡ

በሀዋሳ ከተማ ከሁለት ቢሊዮን 400 ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሀብቶች ወደ ስራ ገቡ ሐዋሳ፣ ጥር 07/2013 (ኢዜአ) በሐዋሳ ከተማ ባለፉት ስድስት ወራት ከሁለት ቢሊዮን 400 ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ 22 ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወስደው ወደ ሥራ መግባታቸውን የከተማዋ አስተዳደር አስታወቀ። በከተማዋ ያለውን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴና በመስኩ ያጋጠሙ ችግሮችን የሚገመግም የምክክር መድረክ በሀዋሳ ተካሂዷል። በምክክር መድረኩ የከተማዋ አስተዳደር የኢንቨስትመንት ማስፋፊያ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ በላይነህ ተሾመ እንዳሉት ባለሀብቶቹ ወደ ሥራ የገቡባቸው መስኮች ግብርና፣ ማኑፋክቸሪንግ፣ አገልግሎትና ግንባታ ላይ ነው። ከሁለት ቢሊዮን 400ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል በማስመዝገብ ወደ ስራ የገቡት ባለሀብቶቹ ከ3 ሺህ ለሚበልጡ የከተማዋ ነዋሪዎች ጊዜያዊና ቋሚ የሥራ ዕድል መፍጠራቸውን አስታውቀዋል። በከተማዋ ያለው ሠላማዊ ሁኔታ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ብልጫ ያለው ባለሀብት ወደ ስራ ለማስገባት ማስቻሉን ጠቁመዋል። በከተማዋ ያለውን የባለሀብቶች እንቅስቃሴ በመገምገም የኢንቨስትመንት ፈቃድ አውጥተው ቦታ በመረከብ ወደ ስራ ያልገቡ 120 ባለሀብቶች ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ጠቁመዋል። የተሰጣቸውን መሬት ሳያለሙ አጥረው በማስቀመጥ ለሌላ ያከራዩ መኖራቸውንም ጠቁመው በስድስት ወራት ውስጥ ወደ ስራ እንዲገቡ የጊዜ ገደብ እንደተቀመጠላቸው ገልጸዋል። የሃዋሳ ከተማ አስተዳደር ምክትል ካንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ጸጋዬ ቱኬ በበኩላቸው አስተዳደሩ በተገቢው መንገድ ወደ ስራ የገቡ ባለሀብቶችን ለመደገፍ የሚያስችል ሥርዓት መዘርጋቱን ተናግረዋል። ባለሀብቱ በተሰጠው የአንቨስትመንት ፈቃድ መሰረት የተረከበውን ቦ

የኦሮሚያ ክልል ከአፋር እና ሲዳማ ክልሎች ጋር በሚዋሰንባቸው አካባቢዎች የክልሎቹን ቋንቋዎች ለማስተማር ዝግጅት አጠናቋል፦ አቶ አዲሱ አረጋ

የኦሮሚያ ክልል ከአፋር እና ሲዳማ ክልሎች ጋር በሚዋሰንባቸው አካባቢዎች የክልሎቹን ቋንቋዎች ለማስተማር ዝግጅት አጠናቋል፦ አቶ አዲሱ አረጋ  **********************  የኦሮሚያ ክልል ከአፋር እና ሲዳማ ክልሎች ጋር በሚዋሰንባቸው አካባቢዎች የክልሎቹን ቋንቋዎች ለማስተማር ዝግጅት መጠናቃቁን በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የማኅበራዊ ክላስተር አስተባባሪ አቶ አዲሱ አረጋ ገለጹ።  አቶ አዲሱ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት፣ “ከአፋር ክልላዊ መንግሥት ጋር በሚያወስኑን የኦሮሚያ ወረዳዎች በሚገኙ ትምህርት ቤቶች አፋርኛ ቋንቋን /Qafar Afih/፣ ከሲዳማ ክልላዊ መንግሥት በሚያዋስኑን የኦሮሚያ ወረዳዎች ባሉ ትምህርት ቤቶች ደግሞ የሲዳሚኛ ቋንቋ /Sidaamu Afoo/ ትምህርት ለማስጀመር ዝግጅት አጠናቀናል” ብለዋል።  አንዱ የሌላውን ቋንቋ መማር የሕዝቦችን በወንድማማችነት፣ እኩልነት እና በመከባበር ላይ የተመሠረተ መስተጋብር ያጎለብታል፤ ጠንካራ አንድነት ያላት ሀገርን ለመገንባትም ያግዛል ሲሉም ገልጸዋል።  ከዚህ በፊት በምሥራቅ እና ምዕራብ ሐረርጌ በሚገኙ 11 ትምርት ቤቶች የሶማሊኛ ቋንቋ /Af-Soomaali/ መሰጠት መጀመሩ ይታወሳል።  EBC

የኢፌዴሪ ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የፌደራል መስክ ቡድን በሲዳማ ክልል ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ማድረጉ ተሰማ

ሚኒስተር መስሪያ ቤቱ የመስክ ቡድን በዛሬ እለት በሀዋሳ ከተማ በሃይሌ  ሪዞርት  ከሲዳማ   ብሔራዊ   ክልላዊ   መንግስት   ምክትል   ርዕስ   መስተዳደርና   ትምህረት   ቢሮ   ኃላፊ   አቶ   በቀለ   ቱንሲሳ   መድረክ   መሪነት   ከክልሉ   ንግድ   ቢሮ   እና   ስራ   ፈጠራና   ኢንዱስትሪ   ቢሮ፣   ከክልል   እስከ   ዞንና   ወረዳ   ድረስ   ያሉ   ኃላፊዎች   ጋር   ተወያይቷል ፡፡ በውይይቱ  የኢፌዴሪ   ንግድና   ኢንዱስትሪ   ሚኒስቴር   በ 2013  በመጀመሪያው   በጀት   ዓመት   በተከናወኑ   ተግባራት   እና   በሁለተኛው   ግማሽ   ዓመት   በትኩረት   ሊሰሩ   በሚገቡ   ጉዳዮች   ላይ   የመስክ   ጉብኝት   ባደረጉበት   እና   በክልሉ   የሚገኙ   የግል   ዘርፍ   የወጪ   ንግድ   ፣የመሠረታዊ   ሸቀጦች   ፣   በኢንዱስትሪ   ላይ   ያሉ   የግብይት   ተዋንያዎች   ጋር   በተደረጉ   ውይይቶች   መነሻ   በክልልና   ዞን   የሚፈቱትን   ለመፍታት   እንዲሁም   መፍታት   በመይቻሉ   ጉዳዮች   ላይ   በኢፌዴሪ   ንግድና   ኢንዱስትሪ   ሚኒስቴር   ለበላይ   አመራር   በሚቀርቡ   ቀጣይ   መፍትሔ   በሚሰጥባቸው   ጉዳዮች   ላይ   ውይይት   ተደርጓል ፡፡ ከዚህም ባሻገር  በሲዳማ   ክልል   ንግድና   ገበያ   ልማት   ቢሮ   ያለፉት   ወራት   ዕቅድ   አፈፃፀም   ላይ   ውይይት   መደረጉን የሚኒስተር መስሪያ ቤቱን ጠቅሶ ወራንቻ ዘግቧል ፡፡