"የአብሮነት ባህላችን ለሰላማችን" በሚል የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከሲዳማ ክልል ጋር በመተባበር አዘጋጅተውታል:: ቀኑ በአለም አቀፍ ደረጃ ለ25ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ11ኛ ጊዜ ነው አየተከበረ ይገኛል:: የፌደራል እና የክልል የመንግስት የስራ ሃላፊዎችን ጨምሮ የሀገር ሽማግሌዎች ፤የጎሳ መሪዎች እና ወጣቶች በስነ ሰርዓቱ ላይ ተገኝተዋል:: በዝግጅቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ብዙነሽ መሠረት ቀኑ የአለም ህዝቦች በቀለም፤ በዘር፤ በሀይማኖት እና በመልካም ምድር አቀማመጥ ልዩነቶች ምክንየት በየጊዜው በሚፈጠሩ ግጭቶች እና አለመግባባቶች የሚያሰከትሉትን መጠነ ሰፊ ጉዳት አጉልቶ በማሳየት አንዱ የሌላውን ሰብዓዊ መብት በማክበር ከሌሎች ጋር በመቻቻል መኖር ለህዝቦች አሰፈላጊ በመሆኑ ግንዛቤ ለማሰረፅ ታሰቦ መሆኑን ገልፀዋል:: ኢትዮጵያ የበርካታ ማንነቶች ሀገር ናት ያሉት ሚኒስትር ዲኤታዋ በየማህበረሰቡ ያሉ አብሮነትን የሚያጎለብቱ ሀገር በቀል እውቀቶችን ማጎልበት እና በየእለት ተእለት መስተጋብራችን ልንጠቀማቸው ይገባል ብለዋል:: በአሁኑ ሰዓት በአብሮነት ላይ ያተኮረ የውይይት መነሻ ፅሁፍ ቀርቦ ውይይት አየተካሄደ ይገኛል፡፡