የፕሮቴስታንት እምነት በሲዳማ

የፕሮቴስታን እምነት በከፍተኛ ፍጥነት ከተስፋፋባቸው የኢትዮጵያ ክልሎች ሲዳማ አንዱ ሲሆን፤ ከሲዳማ ክልል ነዋሪዎች መካከል ወደ 80 ከመቶ የሚሆኑት የክርስቲና ሃይማኖት በተለይ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች መሆናቸውን አንዳንድ ምንጮች ይጠቁማሉ። ጥያቄው እንግዲህ፤ ለመሆኑ የፕሮቴስታንት እምነት ወደ ሲዳማ እንዴት እና ለምን ገባ? እንዴትስ በአጭር ጊዜ ውስጥ የእምነቱ ተከታዮች ልበዙ ቻሉ?

ይህ ጥያቄ፤ እናንተም ጥያቄ ከሆነ በ John H. Hamer የተጻፌ፤ The Religious Conversion Process among the Sidāma of North-East Africa የሚባል እና በ Africa: Journal of the International African Instituteታተመ መጽሐፍን ጨምሮ፤ ከሌሎች ምንጮች ያሰባሰብኳቸውን መረጃዎች ከእናንተ ጋር እጋራለሁኝ አብራችሁኝ ዝለቁ። 

በ1880ዎቹ ላይ ሲዳማን የወረረው የአጸ ምኒልክ መንግስት፤ በነፍጥ አንጋቢዎቹ የፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ የበላይነት የተቆናጠጠ ቢሆንም፤ በባህል ላይ የነበረው ተጽኖ የጎላ አልነበረም፣ ነገር ግን ከአጸ ሚኒልክ ቀጥሎ የነበሩ ነገስታት ጠብመንዣ ያዥ ወታደሮቻቸውን ወደ ሲዳማ በብዛት የመላኩ ህዴት በ19ኛ ክፍለ ዘመን የመጀመሪያዎቹ ሁለት አስርት አመታት ከመቀጠሉ ጋር ተያይዞ፤ ወደ ሲዳማ የዘለቁት አብዘኛዎቹ ወታደሮች ለንጉሶቻቸው ለዋሉላቸው ውለታ፤ የሲዳማን መሬት እና ከመሬቱ ላይ የነበሩትን አርሶ አደር ሲዳማዎችን በጭስኝነት ይሰጧቸው ነበር። እነዚህ በሲዳማ የመሬት ባለቤት የሆኑት ወታደሮች፤ በአብዘኛው ትናንሽ የገበያ ማእከላት በነበሩት እንደ በንሳ ቃዋዶ፣ ሁላ፣ዳሌ፣ ተፌሪ ኬላ፣ ሌኩ ወዘተ እና ወደ በሓላ ላይ ወደ ከተማነት በተቀየሩት ሰፈራዎች እየኖሩ፤ በገጠር የሚኖረውን የሲዳማ ህዝብ ያስተዳድሩ ነበር። ታዲያ በዚህ ጊዜ በገዥና በተገዥ መካከል ያለውን ልዩነት ለማስጠበቅ ስሉ፤ ይዘውት የመጡትን ሃይማኖት የሲዳማ ህዝብ እንድቀበል አላስገደዱም ነበር። 

በነገራችን ላይ ለአምስት አመታት ሲዳማ ውስጥ የቆየው የኢጣሊያ ወራር መንግስት፤ ሲዳማዎችን ሃይማኖታቸውን ወደ ካቶሊክ እምነት ተካታይነት እንድቀይሩ ስለማስገደዱ ምንም መረጃ አላገኘሁም። ነገር ግን ከሁለተኛው የአለም ጦርነት ማብቂያ ላይ ወደ አገራቸው በእንግሊዝ መንግስት ድጋፍ የተመለሱት አጸ ሃይለስላሴ፤ ወደ ስልጣን ከተመለሱበት ጊዜ አንስተው፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን ተጠቅመው፤ ማእከላዊነትን በማጠናከር ስልጣናቸውን ለማስፋት እንዲሁም ስልጣነን እና ኢኮኖሚያዊ እድገት ለማምጣት በሚል፤ በአትዮጵያ ግዛቶች ስር የሚኖረውን ህዝብ ወደ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታይነት የመቀየር ፖሊሲ መከተላቸውን ተከትሎ፤ የሲዳማ አርብቶ አደሮች በግድ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት እንድቀበሉ እና እንድጠመቁ ይገደዱ ነበር። ሃይማኖቱን እንዲቀበሉ ከመገደዳቸው በላይ፤ ሃይማኖቱን የተቀበሉ ደግሞ እንዲጾሙ፤ አርብቶ አደሮች እና ቅይጥ የግብርና ዘይቤ ተከታዮች መሆናቸው እየታወቀ፤ የከብት ምርቶችን በጾም ቀናት እንዳይመገቡ መደረጋቸው፤ እና ሌሎች ምክኒያቶች ተጨምርውበት፤ የሲዳማ ህዝብ ወደ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታይነት በተፈለገው ፍጥነት እንዳይቀየር አድርገዋል። 

አጸ ሃይለስላሌ የተከተሉት በገፍ ሲዳማን በማጥመቂ ኦርቶዶክስ የማድረጉ ተግባር፤ ንጉሱ ያለሙትን ዘመናዊነት እና የኢንዱስትሪ ምርታማነትን ሊያመጣ አልቻለም። በተለይ ንጉሱ የመንግስት ስልጣንን ጠቅልሎ ከያዙ በኋላ፣ የኢኮኖሚ እድገት ለማምጣት የሲዳማን ክልል ሰፋፊ የእርሻ መሬቶችን በመያዝ፤ የአከባቢውን ህዝብ ጉልበት ተጠቅመው፤ ከፍተኛ የሆነ የእርሻ በተለይ የቡናን ምርት በማሳደግ እና የኢንዱስትሪ ግብአት በማምረት አለማቀፍ ንግድ ለመመስረት ወጠኑ። ይህንን ውጥን ለማሳካት የየአከባቢውን ህዝብ ማሰልጠን ለዚሁም በየገጠሩ ትምህርት ቤቶችን መክፈት አማራጭ የሌለው መሆኑን ቢገነዘቡም፤ የሰው ሃይል እና የገንዘብ አቅሙ ስላልነበራቸው ፊታቸውን በስዴት አውሮፓ እያሉ ካፈሯቸው ወዳጅ አገሮች ወደሚመጡ ሚሽኔሪዎች አደረጉ። 

በተለይ በ1940ዎቹ መጨረሻ ላይ ኢቫንጄልካል ፕሮቴስታንት ሚሽኔሪዎችን/ Evengelical Protestant missions በአዲስ አበባ ሆስፒታሎችን እና ትምህርት ቤቶችን እንድገነቡ በጋበዟቸው ጊዜ የሰጧቸውን ፈጣን ምላሽ እና የሰሯቸውን ስራዎች በማየታቸው፤ በ1950 ላይ የስዊዲን ኢንትሬር ሚሽኔሪን/ Sewden Interior Mission ወደ ሲዳማ እንዲገቡ ብሎም ትምህርት ቤቶችን እና የጤና ማእከላትን እንድገነቡ ጋብዘዋቸዋል። ግብዥውን የተቀበሉት ሲዊድኖች ሐዋሳን ማእከል አድርገው፤ በወንዶ ገነት እና ወራንቻ በመሳሰሉ አከባቢዎች የትምህርት ቤቶችን እና ኪሊኒኮችን ክፍተዋል። የሲዊድኖቹን ወደ ሲዳማ መግባታቸውን ተከትሎ የኖርዊጂያን ሉቴራን/ Norwegian Lutherans እና ሰቨን ዴይ አዲቨንቲስት/ Seven Day Adventist ሚሽኔሪዎች እንዲሁ ሐዋሳን ማእከል አድርገው ወደ ሲዳማ ገብተዋል። ለአብነት ያህል፤ የኖርዊጂያን ሉቴራን/ Norwegian Lutherans ከበንሳ ዳዬ አስራ ምናምን ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከሚገኘው ሃቼ ከተባለው ቦታ ላይ ማእከላቸውን በማድረግ ትምህርት ቤት መስርተዋል። 

እንግዲህ ሚሽኔሪዎቹ የአውሮፓውያንን አኗኗር ስልት የሚከተሉት እና ነጻ የሆነ አመለካከት ያላቸው፤ እንዲሁም የአከባቢው ህዝብ የሚከተሉትን ሃይማኖት እንዲከተል የማያስገድዱ ነገር ግን ህዝቡን በትምህርት ወደፊት እንደሄድ የሚጥሩ መሆናቸው፤ ብሎም ለበርካታ አቅም የሌላቸው ህዝብ ነጻ የጤና አጠባበቅ እና የህክምና እርዳት መስጠታቸው፤ በየሚሽኔሪው አከባቢ በሚኖሩ የሲዳማ ተወላጆች ዘንድ ተወዳጅነትን ብቻ ሳይሆን ህዝቡ በፍቃዳቸው ወደ ፕሮቴስታትን እምነት እንድቀበል ምክኒያት ሆነዋል። 

በእነዚህ ሚሽኔሪዎች ሰበብ የተጀመረው የፕሮቴስታንቲዥም አብዮት ከታች በፎቶ ላይ እንደሚታዩት፤ ጊዜያቸውን እና ገንዘባቸውን ለእምነቱ መስፋፋት ለተሰጡ የሲዳማ ተወላጆች መፈጠር ምክንያት በመሆኑ ለዛሬ በርካታ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ የሲዳማ ተወላጆች መፈጠር ምክኒያት ሆነዋል። 

ይህ ከታች የሚታዩት ፎቶ በ1965 አም የተነሳ ሲሆን፤ የየኖርዊጂያን ሉቴራን ሶሳይቲ/ Norwegian Lutherans  EECMYEthiopian Evg. Church Mekane Yesus. From an evangelism session at Sidamo, South Ethiopia. ለወንገል ስራ ከሲዳማዎች የገንዘብ ምጽዋት ስሰበስቡ ያሳያል። Collection of the offerings. (Photo from the Norwegian Lutheran Mission Society, 1965).

 


መልካም ቀን 

ኖሞናኖቶ ነኝ 

No comments