Skip to main content

በሲዳማ ክልል የመንግሥትን ወታደራዊ ርምጃ የሚደግፍ ሰልፍ ተከናወነ

በሲዳማ ክልል የመንግሥትን ወታደራዊ ርምጃ የሚደግፍ ሰልፍ ተከናወነ

የጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ መንግሥት «ስግብግብ ጁንታ» ያላችውን የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሓት) አመራሮችን ለመያዝ እየተደረገ የሚገኘውን ወታደራዊ ርምጃ የሚደግፉ ሰልፎች በሲዳማ ክልል የተለያዩ ከተሞች ተካኺደዋል።

ዛሬ ጠዋት በሀዋሳ ከተማና በዙሪያው ከሚገኙ የክልሉ ወረዳዎች የተሰባሰቡ ነዋሪዎች የተለያዩ መፈክሮችን በመያዝ በከተማው እምብርት በሚገኘው የሚሊኒየም አደባባይ በመውጣት በፌዴራሉ የመከላከያ ሠራዊት ላይ የደረሰውን ጥቃት በማውገዝ ድርጊቱን ፈጽመዋል የሏቸውን የህወሓት አመራሮች ለሕግ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል። 

ዶቼ ቨለ ( DW ) ያነጋገራቸው ከሰልፈኞቹ አንዱ አቶ አብሎ ማሴቦ ፤ «እዚህ የተገኘሁት በዓለም ላይ ሰላም በማስከበር ጥሩ ስም ያለው ሠራዊት የደረሰበትን ጥቃት ለመቃወም ነው። የአካባቢውን ገበሬ ሰብል በማጨድ ሲደግፍ በነበረ ሠራዊት ላይ የተፈጸመው ድርጊት እንደ እኔ ፈጣሪ ይቅር የማይለው ተግባር ነው። መንግሥት ይህን አስነዋሪ ድርጊት የፈጸሙትን እጃቸውን ይዞ ለሕግ እንዲያቀርባቸው እፈልጋለሁ» ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። 

ለሰልፈኞቹ ንግግር ያደረጉት የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ፦ «የህወሓት ስብስብ የአገሪቱን ሀብት ሲመዘብር የቆየ ቡድን ነው። በአሁኑ ወቅትም ተመልሶ ወደ ሥልጣን በመምጣት የለመደውን የዘረፋ ተግባር ለማከናውን አገሪቱን እያተራመሰ ይገኛል። የክልላቸው መንግሥትና ህዝብ የፌዴራሉ መንግሥት ሕግ ለማስከበር በሚያድርገው ሁሉ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋ» ብለዋል።

የፌዴራሉ መንግሥት ህወሓት በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በንጹሐን ዜጎች ላይ ከደረሱት ግድያዎችና መፈናቀሎች ጀርባ እጁ አለበት በማለት ሲወነጅል፣ ህወሓት በበኩል የፌዴራሉ መንግሥት ሕገ መንግሥታዊ ተቀባይነት የሌለው አምባገነናዊ ሥርዓት ሆኗል ሲል ይከሳል።
የፌደራል መንግሥት ወደ ጦርነት የገባው የትግራይ ክልል «ልዩ ኃይል» በሚል ያደራጃቸው ታጣቂዎች መቀሌ በሚገኘው የፌዴራሉ መከላከያ ሠራዊት ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን ባለፈው ሳምንት ካስታወቀ በኋላ ነው። 

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ቀደም ሲል በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ፦ «የሕግ ማስከበር ተልእኮዋችን አለመረጋጋት የሚፈጥሩትን ሕግ ፊት በማቅረብ ሰላም እና ደህንነትን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ማረጋገጥ ላይ ያለመ ነው» ማለታቸው ይታወሳል። 

ዘገባ፦ ሸዋንግዛው ወጋየሁ ከሀዋሳ፤ ዶይቸ ቬለ (DW)

Anti-TPLF Demonstration Underway In Sidama Region

Addis Ababa, November 11, 2020 (FBC) – Thousands of demonstrators have taken to streets of Hawassa City denouncing the treason committed by Tigray People’s Liberation Front (TPLF) against the National Defense Forces of Ethiopia.

Demonstrators dressed up with cultural clothing of Sidama People have flocked to Millennium Square of Hawassa City since 6:AM this morning echoing pro-government voices demanding continued law enforcement measures against the TPLF Junta who has put nation’s sovereignty at risk.

Waving the Flag of Ethiopia and resonating slogans heralding support to the National Defense Forces, the demonstrators expressed their firm desire to see the TPLF junta appeared before justice.

They affirmed any necessary support to the law enforcement measures being taken by the government to ensure law and order in the country.

They echoed slogans like “Ethiopia will not be dismantled by perpetration of the TPLF Junta”, “We stand with the National Defense Force,”, “and Ethiopia will prevail”

Comments

Popular posts from this blog

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

የለበሰው ያደፈ ቁምጣና ሹራብ ከቅዝቃዜው አላዳነውም፡፡ ካፊያው ልብሱን አርሶታል፡፡ ሽው እያለ ከሐይቁ የሚነሳው ነፋስ የሚፈጥረው ቅዝቃዜ ያንቀጠቅጠዋል፡፡ የተጫማው ያረጀ ሲሊፐር እግሩን ከምንም አላዳነውም፡፡ በባዶ እግሩ የሚራመድ ያህል ጨቅይቷል፡፡ ተደባዳቢ ይመስል ፊቱ የተሞነጫጨረ ነው፡፡ ገና 12 ዓመቱ ቢሆንም፣ ቁመናው እንደ ትልቅ ሰው ግዙፍ ነው፡፡ የሚለብሰውን እንደ ልቡ ባያገኝም፣ የሚያስፈልገውን ነገር ለማሟላት ቤሳቢስቲን የሌላቸው ወላጆቹን አያስቸግርም፡፡ ከቤተሰቦቹ ጋር ከሚኖሩበት ታቦር ተራራ ጀርባ ወዳለው ሐዋሳ ሐይቅ ከወረደ እንኳንስ የራሱን የቤተሰቦቹንም የዕለት ጉርስ የሚሸፍንበት ገንዘብ አያጣም፡፡ የአስጎብኚነት ዕውቀት፣ ከሐይቁም ውስጥ ዓሳ የሚያጠምድበት መረብም ሆነ ፈቃድ የለውም፡፡ ሙሉቀን (ስሙ ተቀይሯል) እና ጓደኞቹ ሐይቁን ለመጎብኘት የሚሄዱ ጎብኚዎች በካሜራቸው ጥሩ ፎቶ እንዲያስቀሩ ድባቡን የማሳመር ሥራ ይሠራሉ፡፡ ካሜራውን ይዞ ቁጭ ብድግ እያለ ጥሩ ፎቶ ለማንሳት ጥረት የሚያደርግ ሲያዩ፣ ቆርጠው የያዙትን የዓሳ ሥጋ ይዘው ጠጋ ጠጋ ይላሉ፡፡ ቁርጥራጩን የዓሳ ሥጋ ምግብ ለሚቀሙት አባኮዳዎች ሻሞ ይላሉ፡፡ የተወረወረላቸውን ቀድመው ለመቅለብ አባኮዳዎቹ ክንፋቸውን እየመቱ ወደ ላይ ብድግ ይላሉ፡፡ የናሽናል ጆግሪፊ የፎቶግራፍ ባለሙያዎች ያነሱት ዓይነት ፎቶዎች ሳያስቡት ያነሳሉ፡፡ በሁኔታው ተደስተው ደጋግመው ድንቅ ፎቶዎችን ለመውሰድ ሲዘጋጁ እነ ሙሉቀንም አጀንዳቸውን ይፋ ማድረግ ይጀምራሉ፡፡ አቶ ዳዊት አብርሃም ‹‹አንዱን ዓሳ በአሥር ብር ገዝቼ ነው እንዲህ የማዘጋጀው፤›› በማለት በቅድሚያ  መረጃ ይሰጣሉ፡፡ ለቀጣዩ ዜና በዚህ መልኩ እንዲዘጋጁ ካደረጉ በኋላ፣ ሌሎች ሰዎች መቶም ሁለት መቶም ብር እንደሚሰጧቸው ቀለል

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የመንግሥት ስልጠና የምርጫ ቅስቀሳ አካል ነው ብሏል  የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ለምን ወጣ መባሉ ተገቢ አይደለም - ምርጫ ቦርድ ምርጫ ቦርድ ከኢህአዴግ ተፅዕኖ ሙሉ ለሙሉ ነፃ መሆኑ ሳይረጋገጥና የምርጫ አፈፃፀም ችግሮች ሳይወገዱ የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ለማወጅ መዘጋጀቱ ተገቢ አይደለም ሲል ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ የሚመሩት ኢማዴ-ደህአፓ ተቃወመ፡፡ መንግስት፤ የዩኒቨርሲቲ መምህራንና ተማሪዎችን ጨምሮ ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየሰጠ ያለው ስልጠና የምርጫ ቅስቀሳ አካል ነው ሲልም ፓርቲው ኮንኗል፡፡  የኢትዮጵያ ማህበረ ዴሞክራሲ ደቡብ ህዝቦች አንድነት ፓርቲ ሰሞኑን ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ባስገባው ግልፅ ደብዳቤ፤ ያለፉት አገር አቀፍና የአካባቢ ምርጫዎች ከመካሄዳቸው በፊት በምርጫ ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው ዙሪያ ኢህአዴግ ከተቃዋሚዎች ጋር የሚወያይበት መድረክ እንዲዘጋጅ በተደጋጋሚ ብንጠይቅም እስካሁን ከቦርዱ የተሰጠ ተግባራዊ ምላሽ የለም ብሏል፡፡  ሃገሪቱ “በአንድ አውራ ፓርቲ” ብቸኛ ቁጥጥር ስር መውደቋ አደገኛና አሳሳቢ ነው ያለው ፓርቲው፤ የመድብለ ፓርቲ ስርአት የመገንባት ተስፋችን ጨርሶ እንዳይከስም ቦርዱ ሃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት አሳስቧል፡፡ ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ የሚካሄድበትን ሁኔታ ለመፍጠር ገዥው ፓርቲና ሃቀኛ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚወያዩበት መድረክ እንዲያመቻች በህግ ስልጣን የተሰጠው ምርጫ ቦርድ የገባውን ቃል በማጠፍ መድረኩን ሳያመቻች የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማዘጋጀቱ ፋይዳ የለውም ብሏል - ፓርቲው፡፡  ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ በተሻሻለው የምርጫ ህግ፣ ለቦርዱ የተሰጠውን የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ መድረክ የማስተባበር ስልጣን ለመቀማት ታማኝ ፓርቲዎችን በተቃዋሚ ስም አሰባስቦ “የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ መድረክ” በመፍጠር የምርጫ ውድድር አሯሯጭ አሰልፏል ሲ

የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል ማለፊያ ነጥብ ውጤት ነገ ይፋ ይሆናል

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 23 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) የ10ኛ ክፍል ማጠቃለያና የ12ኛ ክፍል መሰናዶ ማለፊያ ነጥብ ውጤትን ነገ ይፋ እንደሚያደርግ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። የዩኒቨርስቲ መግቢያና ወደ መሰናዶ ማለፊያ ነጥብን ለመወሰን  ፥ የዩኒቨርስቲዎችን ቀጣይ የመቀበል አቅም ከግምት ውስጥ በማስገባት መወሰኑንም ነው ሚኒስቴሩ የገለጸው። በአጠቃላይ 548 ሺህ 138 ተማሪዎች የ10 ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተናውን ወስደው 70 በመቶዎቹ 2 ነጥብ እና ካዛ በላይ ውጤት ሲያስመዘግቡ ፥ በተመሳሳይም የ12ኛ ክፍልን የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተናን ከወሰዱት መካከል 70 በመቶ የሚሆኑት ተፈታኞች ከ350 ነጥብ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውን ቀደም ሲል  የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና የፈተናዎች ኤጀንሲ አስታውሷል ። በነገው እለትም የሁለቱም ፈተናዎች የመቁረጫ ውጤት ይፋ ይደረጋል ተብሏል።