Skip to main content

‹‹ በክልል ብቻ ሳንታጠር እንደ አገር የተቃጣብንን አደጋ በጋራ ለመወጣት ዝግጁዎች ነን›› አቶ አለማየሁ ጢሞቴዎስ የሲዳማ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ

 


ሃዋሳ፡- ሰሞኑን የህወሓት ጥገኛ ቡድን በአገር መከላከያ ሠራዊት ላይ ያደረሰውን ጥቃት በክልል ሳንታጠር እንደ አገር የተቃጣብንን አደጋ በጋራ ለመወጣት ዝግጁዎች ነን ሲሉ የሲዳማ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቴዎስ አስታወቁ።በክልሉ እብድ በማስመሰል የላኩትን ሰው ማሰራቸውንና በጥገኛ ቡድኑ በንግድ ተቋማቱ በኩል ገንዘብ ሲያሰራጩ የነበሩ አካላትን መያዛቸውን ገለጹ።

የሲዳማ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊው አቶ አለማየሁ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳስታወቁት፤ ሰሞኑን የተፈጠረው ነገር በአገር መከላከያ ሠራዊት ላይ ሆነ እንጂ የሚጠበቅ ነበር።ጽንፈኛው ቡድን በመከላከያ ሠራዊት ላይ ያደረሰው ጥቃት የመከላከያ ሠራዊቱ ጥቃት ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ ህልውና እና በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የደረሰ ጥቃት ነው።በመሆኑም በክልል መታጠር ሳይኖር በጽንፈኛ ቡድኑ የተቃጣውን ጦርነት እንደ አገር በጋራ ለመወጣት ዝግጁዎች ነን፡፡

ለማንኛውንም ግዳጅ ሆነ ሀገራዊ ተልዕኮ የክልሉ ሠራዊት ሙሉ በሙሉ ዝግጁ መሆኑን የተናገሩት ኃላፊው፣ መቀሌ በመገኘት ጥገኛ ቡድኑን በመፋለም ብቻ ሳይሆን ባሉበት ቦታ ሆነውም እነርሱ ያላቸውን ኔትዎርክ በሙሉ ለመበጣጠስም ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።ሥራቸውን ለማክሸፍም በመንቀሳቀስ ላይ ከመሆናቸውም በተጨማሪ የህዝብ ንቃናቄውን በአጭር ጊዜ ውስጥ መፍጠራቸውን አመልክተዋል፡፡

ከጫፍ እስከ ጫፍ መንግሥት እየወሰደ ባለው ዕርምጃም ደስተኛ መሆናቸውን ተመልክተው፣ በተለይ ከሲዳማ ክልል ህዝብ ጋር ከጫፍ እስከጫፍ ባመቻቹት መድረኮች በሙሉ ህዝባዊ ተሳትፎ ካስፈለገ ህዝቡ ዝግጁ ነው ብለዋል፣ ከአገር በላይ እንደሌለም ገልጸዋል፡፡

እንደ አቶ አለማየሁ ገለጻ፤ ኢትዮጵያ ጽንፈኛው ቡድን ጠፍጥፎ የሠራት አገር ሳትሆን፤ ኢትዮጵያ የምትባለዋ አገር በዜጎቿ ብርታት ለአገር ውስጥ ጠላት ቀርቶ ለውጭ ጠላት ተንበርክካ አታውቅም። ይህን ማንነቷን ዛሬም ይዛ ትቀጥላለች፤ በኢትዮጵያ ህልውና የመጣ ማንኛውም እንቅስቃሴ ለኢትዮጵያ ህዝብ ጠላት ነው፡፡

የትግራይ ህዝብ መረዳት ያለበት ማዕከላዊ መንግሥት እየወሰደ ያለው ዕርምጃ ሀገርና ህዝብን የመታደግ ተልዕኮ ያነገበ ነው።ግጭቱ ፀረ ሰላም ኃይሎች ለህዝብ ለውጥ የሚሠራ ኃይል ሲመጣ እኔ ካልመራሁ ኢትዮጵያ ትፍረስ ብለው በማሰባቸው የመጣ ነው።እንዲህ ማሰብ በራሱ ሌሎችን የኢትዮጵያን ህዝብ እንደባሪያ እንደማየት የሚቆጠር ቢሆንም ከዚህ በኋላ ግን ማንም የማይንበረከክ መሆኑን መረዳት አለባቸው ብለዋል።የሲዳማ ክልል አስፈላጊ ነው በሚባል ነገር ሁሉ በፋይናንስም ሆነ በሰው ኃይልም እንዲሁም ሎጂስቲክም በቀጥታ ገብቶ ጥገኛውን ቡድን ለመዋጋት ዝግጁ መሆኑንም አረጋግጠዋል፡፡

ኃላፊው እንዳሉት፤ ወጣቱ የሽብር ቡድኑ በንጹሐን ዜጎች ደም የራሱን ትርፍ ማራመድ የሚፈልግ መሆኑን መረዳት አለበት።ባለፉት 27 ዓመታት የወጣቱን አካል ሲያጎድል፣ ሲገድል የነበረና ዛሬም ተጨማሪ ደም ለማፍሰስ በየቦታው የሽብር ጥቃት እያደረሰ መሆኑን ማስተዋል ይጠበቅበታል ብለዋል።

ህወሓት ለትግራይ ወጣት ጠንቅና ጠላት ነው። የትግራይ ወጣት በውስን ቡድን ተሳስቶ ወደ ጦርነት መግባት የለበትም፤ ለወጣቱ የሚያስፈልገው ጦርነት ሳይሆን ሥራ ፈጠራና መማር ነው።ህወሓት ግን ይህን ማድረግ ሳይሆን ለጦርነት እንዲነሳሳ ነው እያደረገ ያለው።ስለዚህ የትኛውም ክልል ያለ ወጣት ይህን እኩይ ሥራ መቃወም እንዳለበት አስታውቀዋል።ይህን ጊዜ በብልሃት በመሻገር መጻዒ ዕድላቸውን መልካም እንዲሆን ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አመልክተዋል፡፡

መንግሥት አሁን እየወሰደ ባለው ዕርምጃ ደስተኛ ነው።ቀጣይም በየትኛውም በኩል በሚደረግለት ጥሪ ድጋፉን ለማበርከት ዝግጁ ነው።ጉዳዩ እንደተከሰተ ጀምሮ ከጫፍ እስከ ጫፍ ከህዝብ ጋር ውይይት በመደረጉ ህዝቡም ራሱን መንደር በመንደር እንዲጠብቅም መረጃ ደርሶታል።ለየት ያለ ነገር ቢያጋጥም እንኳ ጥቆማ እንዲሰጥም ሁኔታዎች ተመቻችተዋል።ጥቆማ ቢመጣ ደግሞ ተመጣጣኝ ዕርምጃ መውሰድ የሚያስችል ዝግጅት መደረጉን አስታውቀዋል፡፡

“ጥገኛ ቡድኑ አስቀድሞ ባሰለጠነው ቡድኑ በርካታ ቦታ ላይ በርካታ ሙከራ በማድረግ ላይ ነው፤ ይህን ሁሉ ግን በተባበረ ክንዳችን እየመከትን ነው ብለዋል።እኛ ዘንድ እብድ በማስመሰል የላኩትን ሰው አስረናል።በእነሱ በንግድ ተቋማቱ በኩል ገንዘብ ሲያሰራጭ የነበረም ግለሰብ ይዘናል ብለዋል፡፡”

አዲስ ዘመን ህዳር 1/2013

Comments

Popular posts from this blog

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

የለበሰው ያደፈ ቁምጣና ሹራብ ከቅዝቃዜው አላዳነውም፡፡ ካፊያው ልብሱን አርሶታል፡፡ ሽው እያለ ከሐይቁ የሚነሳው ነፋስ የሚፈጥረው ቅዝቃዜ ያንቀጠቅጠዋል፡፡ የተጫማው ያረጀ ሲሊፐር እግሩን ከምንም አላዳነውም፡፡ በባዶ እግሩ የሚራመድ ያህል ጨቅይቷል፡፡ ተደባዳቢ ይመስል ፊቱ የተሞነጫጨረ ነው፡፡ ገና 12 ዓመቱ ቢሆንም፣ ቁመናው እንደ ትልቅ ሰው ግዙፍ ነው፡፡ የሚለብሰውን እንደ ልቡ ባያገኝም፣ የሚያስፈልገውን ነገር ለማሟላት ቤሳቢስቲን የሌላቸው ወላጆቹን አያስቸግርም፡፡ ከቤተሰቦቹ ጋር ከሚኖሩበት ታቦር ተራራ ጀርባ ወዳለው ሐዋሳ ሐይቅ ከወረደ እንኳንስ የራሱን የቤተሰቦቹንም የዕለት ጉርስ የሚሸፍንበት ገንዘብ አያጣም፡፡ የአስጎብኚነት ዕውቀት፣ ከሐይቁም ውስጥ ዓሳ የሚያጠምድበት መረብም ሆነ ፈቃድ የለውም፡፡ ሙሉቀን (ስሙ ተቀይሯል) እና ጓደኞቹ ሐይቁን ለመጎብኘት የሚሄዱ ጎብኚዎች በካሜራቸው ጥሩ ፎቶ እንዲያስቀሩ ድባቡን የማሳመር ሥራ ይሠራሉ፡፡ ካሜራውን ይዞ ቁጭ ብድግ እያለ ጥሩ ፎቶ ለማንሳት ጥረት የሚያደርግ ሲያዩ፣ ቆርጠው የያዙትን የዓሳ ሥጋ ይዘው ጠጋ ጠጋ ይላሉ፡፡ ቁርጥራጩን የዓሳ ሥጋ ምግብ ለሚቀሙት አባኮዳዎች ሻሞ ይላሉ፡፡ የተወረወረላቸውን ቀድመው ለመቅለብ አባኮዳዎቹ ክንፋቸውን እየመቱ ወደ ላይ ብድግ ይላሉ፡፡ የናሽናል ጆግሪፊ የፎቶግራፍ ባለሙያዎች ያነሱት ዓይነት ፎቶዎች ሳያስቡት ያነሳሉ፡፡ በሁኔታው ተደስተው ደጋግመው ድንቅ ፎቶዎችን ለመውሰድ ሲዘጋጁ እነ ሙሉቀንም አጀንዳቸውን ይፋ ማድረግ ይጀምራሉ፡፡ አቶ ዳዊት አብርሃም ‹‹አንዱን ዓሳ በአሥር ብር ገዝቼ ነው እንዲህ የማዘጋጀው፤›› በማለት በቅድሚያ  መረጃ ይሰጣሉ፡፡ ለቀጣዩ ዜና በዚህ መልኩ እንዲዘጋጁ ካደረጉ በኋላ፣ ሌሎች ሰዎች መቶም ሁለት መቶም ብር እንደሚሰጧቸው ቀለል

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የመንግሥት ስልጠና የምርጫ ቅስቀሳ አካል ነው ብሏል  የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ለምን ወጣ መባሉ ተገቢ አይደለም - ምርጫ ቦርድ ምርጫ ቦርድ ከኢህአዴግ ተፅዕኖ ሙሉ ለሙሉ ነፃ መሆኑ ሳይረጋገጥና የምርጫ አፈፃፀም ችግሮች ሳይወገዱ የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ለማወጅ መዘጋጀቱ ተገቢ አይደለም ሲል ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ የሚመሩት ኢማዴ-ደህአፓ ተቃወመ፡፡ መንግስት፤ የዩኒቨርሲቲ መምህራንና ተማሪዎችን ጨምሮ ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየሰጠ ያለው ስልጠና የምርጫ ቅስቀሳ አካል ነው ሲልም ፓርቲው ኮንኗል፡፡  የኢትዮጵያ ማህበረ ዴሞክራሲ ደቡብ ህዝቦች አንድነት ፓርቲ ሰሞኑን ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ባስገባው ግልፅ ደብዳቤ፤ ያለፉት አገር አቀፍና የአካባቢ ምርጫዎች ከመካሄዳቸው በፊት በምርጫ ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው ዙሪያ ኢህአዴግ ከተቃዋሚዎች ጋር የሚወያይበት መድረክ እንዲዘጋጅ በተደጋጋሚ ብንጠይቅም እስካሁን ከቦርዱ የተሰጠ ተግባራዊ ምላሽ የለም ብሏል፡፡  ሃገሪቱ “በአንድ አውራ ፓርቲ” ብቸኛ ቁጥጥር ስር መውደቋ አደገኛና አሳሳቢ ነው ያለው ፓርቲው፤ የመድብለ ፓርቲ ስርአት የመገንባት ተስፋችን ጨርሶ እንዳይከስም ቦርዱ ሃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት አሳስቧል፡፡ ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ የሚካሄድበትን ሁኔታ ለመፍጠር ገዥው ፓርቲና ሃቀኛ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚወያዩበት መድረክ እንዲያመቻች በህግ ስልጣን የተሰጠው ምርጫ ቦርድ የገባውን ቃል በማጠፍ መድረኩን ሳያመቻች የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማዘጋጀቱ ፋይዳ የለውም ብሏል - ፓርቲው፡፡  ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ በተሻሻለው የምርጫ ህግ፣ ለቦርዱ የተሰጠውን የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ መድረክ የማስተባበር ስልጣን ለመቀማት ታማኝ ፓርቲዎችን በተቃዋሚ ስም አሰባስቦ “የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ መድረክ” በመፍጠር የምርጫ ውድድር አሯሯጭ አሰልፏል ሲ

የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል ማለፊያ ነጥብ ውጤት ነገ ይፋ ይሆናል

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 23 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) የ10ኛ ክፍል ማጠቃለያና የ12ኛ ክፍል መሰናዶ ማለፊያ ነጥብ ውጤትን ነገ ይፋ እንደሚያደርግ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። የዩኒቨርስቲ መግቢያና ወደ መሰናዶ ማለፊያ ነጥብን ለመወሰን  ፥ የዩኒቨርስቲዎችን ቀጣይ የመቀበል አቅም ከግምት ውስጥ በማስገባት መወሰኑንም ነው ሚኒስቴሩ የገለጸው። በአጠቃላይ 548 ሺህ 138 ተማሪዎች የ10 ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተናውን ወስደው 70 በመቶዎቹ 2 ነጥብ እና ካዛ በላይ ውጤት ሲያስመዘግቡ ፥ በተመሳሳይም የ12ኛ ክፍልን የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተናን ከወሰዱት መካከል 70 በመቶ የሚሆኑት ተፈታኞች ከ350 ነጥብ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውን ቀደም ሲል  የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና የፈተናዎች ኤጀንሲ አስታውሷል ። በነገው እለትም የሁለቱም ፈተናዎች የመቁረጫ ውጤት ይፋ ይደረጋል ተብሏል።