ለመሆኑ ከአቢሲኒያ ወረራ በፊት የሲዳማ ነጻ ግዛት ምን ይመስል ነበር?11ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ እስከ 13ኛው ክፍለ ዘመን የነበረው የእስልምና መስፋፋት እና መነሳት በቀይ ባህር ላይ የኢትዮጵያ ንጉሳን፤ ከግርክ እና ከ መኻከለኛ ባሕር Mediterranean አከባቢ ግዛቶች ጋር የነበራቸውን የንግድ በማቆሙ፤ ከሌላው አለም በንግድ እንድገለሉ አድርጓል። በተለይ ቀይ ባህርን ተከትሎ ይኖሩ የነበሩ የኩሽ ቋንቋ ተናጋሪ እንደ ሳኦ፣ አፋር እና ሶማሌ የመሳሰሉ ህዝቦች ወደ እስልምና ሃይማኖት ተከታይነት መቀየራቸው፤  ንጉሳኑ በቀይ ባህር ላይ ያደርጉ የነበሩት ንግድ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ምንጫቸው የበለጠ በማድረቁ፤ የወቀውን ኢኮኖሚያቸውን ለመደገፍ ስሉ ፊታቸውን ከአከባቢያቸው ወደሚገኙት ነጻ ንጉሳዊ ግዛቶች በማዞራር፣ የአባይን ወንዝ ተሻግረው ወደ ደቡባዊ ክልል መስፋፋት መጀመራቸው እና በአሁኑ ደቡባዊ የኢትዮጵያ ክፍል የነበሩትን ሃድያን እና ባሌን ጨምሮ ሌሎች የእስላም ግዛቶችን መውረር መጀመራቸው ይነገራል። በዚህም ሰሜናዊው የክርስቲያን መንግስት ኩሽ ተናጋሪው ከሆነው ከሲዳማ ነጻ ግዛት ጋር የመጀመሪያውን ግኙኝነት ለማድረግ ብቅቷልው።

የሲዳማ ነጻ ግዛት ከክርሲቲያን መንግስት፤ ከኦሮሞ መስፋፋት እና በአዳሉ መሪ በአሃመድ ኢብን ኢብሪሃም ግራን  Ahmad ibn lbrahim Gran (1507-42)of Adal በተለምዶ ግራኝ አሃመድ ወረራ ከመመታቱ በፊት፤ በ1613 እስከ 1614 ወደ ሲዳማ ያቀኑት ጄሱት አንቶኒዮ ፌርደናንድ የተባሉ ፖርቱጋላዊ እንደጻፉት ከሆነ፤ ሲዳማዎች ከብት አርብዎች ከመሆናቸው በላይ፤ ከጥታዊውን የግብጻውያን አስተራረስ ጋር የሚመሳሰል የእርሻ አስተራረስ ተጠቅመው፤ ቡናና ጥጥን ጨምሮ በርካታ የምግብ እህሎችን ያመርቱ እንደነበር ገልጸዋል። አክለውም ሲዳማዎች ከአከባቢያቸው ርቀው ከምገኙ ህዝቦች ጋር ከብት፤ አልባሳት፤ አሞሌ፣ እና የወርቅ ምርቶችን ይነግዱ የነበረ ሲሆን፣ ለመገበያያም ከብረት የተሰራ አናቱ ላይ ክብ የሆነ ጠፍጣፋ ብረት እንደገንዘብ ይጠቀሙ ነበር ስል ገልጸዋል። በአገዛዝ ስርአቱም፤ የሲዳማ ንጉስ እና የንጉሱ ምስት እናት ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወቱ የገለጹ ሲሆን፤ ንጉስ ስሞት በበሬ ቆዳ ጠቅልለው እንደሚቀብሩ እና በለቅሶውም ጊዜ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ከብት እንደሚያርዱ አመልክተዋል። 

መልካም የስራ ሳምንት ይሁንላችሁ!! 

ኖሞናኖቶ ነኝ

No comments