Skip to main content

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት ቅዳሜ ግማሽ ቀን መደበኛ የስራ ቀን ማድረጉን አስታወቀ

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት ቅዳሜ ግማሽ ቀን መደበኛ የስራ ቀን ማድረጉን አስታወቀቅርንጫፍ መስሪያ ቤቱ በ2 ወራት ብቻ 500 ሚሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ማቀዱን ገልጿል።
የቅርንጫፉ ዋና ስራ አስኪጅ አቶ ታምሩ ተፈሪ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት በበጀት አመቱ የታቀደውን ገቢ በተሳካ ሁኔታ ለመሰብበሰብ እና ለተገልጋዩ ቀላጣፋ አገልግሎት መስጠት ይቻል ዘንድ መስሪያ ቤቱ ቅዳሜን ግማሽ ቀን የስራ ቀን አድርጓል ብለዋል፡፡
እንደ ስራ አስኪያጁ ገለጻ አሰራሩን በዚህ መልክ ማድረግ መቻሉ የበጀት አመቱን እንቅድ በተሻለ ደረጃ ከማሳካት ባሻገር የአገልግሎት አሰጣጡን ይበልጥ የተሳለጠ እና በተገልጋዩ ዘንድ አመኔታ ያለው አገልግሎትን እውን ማድረግ ያስችላል፡፡
ውሳኔው በበጀት አመቱ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ተግባራትን ከዳር በማድረስ የቆዩ የህዝብ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ምላሽ ለመስጠት መስሪያ ቤቱ እያደረገ ያለው ጥረት አካል መሆኑንም ነው ስራ አስኪያጁ የገለጹት፡፡
በዚህም ቅርንጫፍ መስሪ ቤቱ በተያዘው በጀት አመት ባደረገው ርብርብ በሀምሌ እና ነሀሴ ወራት ብቻ ከደረጃ 'ሐ' እና 'ለ' ግብር ከፋዮች ብቻ ከ280 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የገለጹት አቶ ታምሩ ይህም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከ80 ሚሊዮን ብር በላይ ብልጫ ያለው ገቢ እንደሆነ በማስረዳት ነው፡፡
በበጀት አመቱ የከተማዋን ገቢ አሟጦ ለመሰብሰብ ይቻል ዘንድም በገቢ አሰባሰብ ስርዓቱ ዙሪያ የሚስተዋሉ ችግሮችን የሚፈትሽ ጥናት ማድረግን ጨምሮ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የጋራ መግባባት ላይ የደረሰ ቅንጅታዊ አሰራርን እውን ማድረግ ስለመቻሉም ነው ስራ አስኪያጁ የገለጹት፡፡
በዚህ ሁሉ ውስጥ በተለይም ከአገልግሎት አሰጣጡ ጋር የሚስተዋሉ መጨናነቆችን ለመቅረፍ ከቅርንጫፍ መስሪያ ቤቱ ባለሙያዎች ጋር የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ ቅዳሜን ግማሽ ቀን የስራ ቀን ለማድረግ መወሰኑን ስራ አስኪጁ አያይዘው አስረድተዋል፡፡
በመሆኑም ከመጪው ጥቅምት 1 ቀን 2013 ዓም ጀምሮ በመደበኛ የስራ ቀናት በተለያዩ ምክንያቶች በተቋሙ አገልግሎት ማግኘት ያልቻሉ ተገልጋዮች ቅዳሜን ተጠቅመው የዜግነት ግዴታቸውን እንዲወጡም ነው አቶ ታምሩ ያስታወቁት፡፡
በቅርንጫፍ መስሪያ ቤቱ ባለሙያ የሆኑት ወ/ሮ ሰራዊት አለሙ እና አቶ ሲሳይ አየለ በበኩላቸው በከተማዋ የሚገኙ ግብር ከፋዮች ያሉባቸውን ጫናዎች ለመቅረፍ ቅዳሜን ግማሽ ቀን በመስራት ሙያዊ ግዴታቸውን ለመወጣት መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል፡፡
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በ2013 በጀት አመት 2 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ በማቀድ እንየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ከመስሪያ ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያስረዳል፡:
©የከተማዋ ህዝብ ግኑኝነት ቢሮ ነው

Comments

Popular posts from this blog

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

የለበሰው ያደፈ ቁምጣና ሹራብ ከቅዝቃዜው አላዳነውም፡፡ ካፊያው ልብሱን አርሶታል፡፡ ሽው እያለ ከሐይቁ የሚነሳው ነፋስ የሚፈጥረው ቅዝቃዜ ያንቀጠቅጠዋል፡፡ የተጫማው ያረጀ ሲሊፐር እግሩን ከምንም አላዳነውም፡፡ በባዶ እግሩ የሚራመድ ያህል ጨቅይቷል፡፡ ተደባዳቢ ይመስል ፊቱ የተሞነጫጨረ ነው፡፡ ገና 12 ዓመቱ ቢሆንም፣ ቁመናው እንደ ትልቅ ሰው ግዙፍ ነው፡፡ የሚለብሰውን እንደ ልቡ ባያገኝም፣ የሚያስፈልገውን ነገር ለማሟላት ቤሳቢስቲን የሌላቸው ወላጆቹን አያስቸግርም፡፡ ከቤተሰቦቹ ጋር ከሚኖሩበት ታቦር ተራራ ጀርባ ወዳለው ሐዋሳ ሐይቅ ከወረደ እንኳንስ የራሱን የቤተሰቦቹንም የዕለት ጉርስ የሚሸፍንበት ገንዘብ አያጣም፡፡ የአስጎብኚነት ዕውቀት፣ ከሐይቁም ውስጥ ዓሳ የሚያጠምድበት መረብም ሆነ ፈቃድ የለውም፡፡ ሙሉቀን (ስሙ ተቀይሯል) እና ጓደኞቹ ሐይቁን ለመጎብኘት የሚሄዱ ጎብኚዎች በካሜራቸው ጥሩ ፎቶ እንዲያስቀሩ ድባቡን የማሳመር ሥራ ይሠራሉ፡፡ ካሜራውን ይዞ ቁጭ ብድግ እያለ ጥሩ ፎቶ ለማንሳት ጥረት የሚያደርግ ሲያዩ፣ ቆርጠው የያዙትን የዓሳ ሥጋ ይዘው ጠጋ ጠጋ ይላሉ፡፡ ቁርጥራጩን የዓሳ ሥጋ ምግብ ለሚቀሙት አባኮዳዎች ሻሞ ይላሉ፡፡ የተወረወረላቸውን ቀድመው ለመቅለብ አባኮዳዎቹ ክንፋቸውን እየመቱ ወደ ላይ ብድግ ይላሉ፡፡ የናሽናል ጆግሪፊ የፎቶግራፍ ባለሙያዎች ያነሱት ዓይነት ፎቶዎች ሳያስቡት ያነሳሉ፡፡ በሁኔታው ተደስተው ደጋግመው ድንቅ ፎቶዎችን ለመውሰድ ሲዘጋጁ እነ ሙሉቀንም አጀንዳቸውን ይፋ ማድረግ ይጀምራሉ፡፡ አቶ ዳዊት አብርሃም ‹‹አንዱን ዓሳ በአሥር ብር ገዝቼ ነው እንዲህ የማዘጋጀው፤›› በማለት በቅድሚያ  መረጃ ይሰጣሉ፡፡ ለቀጣዩ ዜና በዚህ መልኩ እንዲዘጋጁ ካደረጉ በኋላ፣ ሌሎች ሰዎች መቶም ሁለት መቶም ብር እንደሚሰጧቸው ቀለል

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የመንግሥት ስልጠና የምርጫ ቅስቀሳ አካል ነው ብሏል  የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ለምን ወጣ መባሉ ተገቢ አይደለም - ምርጫ ቦርድ ምርጫ ቦርድ ከኢህአዴግ ተፅዕኖ ሙሉ ለሙሉ ነፃ መሆኑ ሳይረጋገጥና የምርጫ አፈፃፀም ችግሮች ሳይወገዱ የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ለማወጅ መዘጋጀቱ ተገቢ አይደለም ሲል ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ የሚመሩት ኢማዴ-ደህአፓ ተቃወመ፡፡ መንግስት፤ የዩኒቨርሲቲ መምህራንና ተማሪዎችን ጨምሮ ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየሰጠ ያለው ስልጠና የምርጫ ቅስቀሳ አካል ነው ሲልም ፓርቲው ኮንኗል፡፡  የኢትዮጵያ ማህበረ ዴሞክራሲ ደቡብ ህዝቦች አንድነት ፓርቲ ሰሞኑን ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ባስገባው ግልፅ ደብዳቤ፤ ያለፉት አገር አቀፍና የአካባቢ ምርጫዎች ከመካሄዳቸው በፊት በምርጫ ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው ዙሪያ ኢህአዴግ ከተቃዋሚዎች ጋር የሚወያይበት መድረክ እንዲዘጋጅ በተደጋጋሚ ብንጠይቅም እስካሁን ከቦርዱ የተሰጠ ተግባራዊ ምላሽ የለም ብሏል፡፡  ሃገሪቱ “በአንድ አውራ ፓርቲ” ብቸኛ ቁጥጥር ስር መውደቋ አደገኛና አሳሳቢ ነው ያለው ፓርቲው፤ የመድብለ ፓርቲ ስርአት የመገንባት ተስፋችን ጨርሶ እንዳይከስም ቦርዱ ሃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት አሳስቧል፡፡ ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ የሚካሄድበትን ሁኔታ ለመፍጠር ገዥው ፓርቲና ሃቀኛ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚወያዩበት መድረክ እንዲያመቻች በህግ ስልጣን የተሰጠው ምርጫ ቦርድ የገባውን ቃል በማጠፍ መድረኩን ሳያመቻች የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማዘጋጀቱ ፋይዳ የለውም ብሏል - ፓርቲው፡፡  ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ በተሻሻለው የምርጫ ህግ፣ ለቦርዱ የተሰጠውን የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ መድረክ የማስተባበር ስልጣን ለመቀማት ታማኝ ፓርቲዎችን በተቃዋሚ ስም አሰባስቦ “የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ መድረክ” በመፍጠር የምርጫ ውድድር አሯሯጭ አሰልፏል ሲ

29 ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ የጫነ አንድ ተሸከርካሪ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ገልፀ

29 ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ የጫነ አንድ ተሸከርካሪ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ገልፀ፡፡ በጉዳዩ ዙሪያ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ ኮለኔል ሮዳሞ ኪአ እንዲሁም ኮማንደር ኢዮብ አቤቶ የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ዛሬ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በዚህም መሰረት ትላንት ምሽት 5፡00 አካባቢ ኮድ 3/ 34480 አ.አ ታርጋ ቁጥር በለጠፈ አይሱዙ ኤፍ.ኤስ.አር ተሸከርካሪ 29 ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ በመኪናው ከፋብሪካ ውጭ በተሰራ በቀላሉ የማይገኝ ሚስጥራዊ ቦታ ተደብቆ ሲጓዝ በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልፀዋል፡፡ ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያውን ሲያጓጉዙ የነበሩት የመኪናው አሽከርካሪ፣ የህገ-ወጥ ጦር መሳሪያው ባለቤት እና የመኪናው እረዳት በቁጥጥር ስር መዋላቸውም ተገልጿል፡፡ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር መረጃው ከሳምንት በፊት አስቀድሞ በደረሰ ጥቆማ የታወቀ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ብቃት ያለቸውን የፖሊስ አመራሮች በመመደብ ጉዳዩ በሚስጥር ሲጣራ ቆይቶ ትላንት ምሽት በቁጥጥር ስር መዋሉ ነው የተገለፀው፡፡ የጦር መሳሪያው ከየት ተነስቶ ወደየት እንደሚሄድ ለምን ዓላማ ሊውል እንደተፈለገ ጭምር መረጃዎች መኖራቸው የተገለፀ ሲሆን ጉዳዩ በምርመራ ሂደት ላይ በመሆኑ ሳይገለፅ ቀርቷል፡፡ ከተማ አስተዳደሩ የፀጥታ ሀይሉን አቅም በማጠናከር እና ከህዝብ ጋር በመቀናጀት ማንኛውንም አይነት ህገ-ወጥ እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር በቁርጠኝነት እየሰራ እንደሚገኝ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ ኮሎኔል ሮዳሞ ኪአ ገልፀዋል፡፡ በዚህም የከተማዋ ሰላም እና የፀጥታ ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ እና እየተጠናከረ መምጣቱን ኮለኔል ሮዳሞ ገልፀው