የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር ከሰሞኑ በአፋር የጎርፍ አደጋ ለተጠቁ ወገኖች የ5 ሚልዮን ብር ድጋፍ ያደረገ ሲሆን በዛሬው እለት ደግሞ በቅርቡ በሻሸመኔው ጥቃት ለተጎዱ መልሶ ማቋቋምያ የ3.5 ሚልዮን ብር ድጋፍ አድርጓል።የሲዳማ ክልል እያደረገ ያለው ድጋፍ ከሞራልም ሆነ ከዲፕሎማሲ አንጻር ሲታይ ትክክለኛ እና የሚበረታታ ተግባር ነው።ሆኖም ግን ለተጎዱት ድጋፍ የማድረጉ ስራ ከቤት ቢጀመር የበለጠ ጥሩ ይሆናል።
*በ1971-73 ዓም ሱማሊያ ሞቃዲሾ ድረስ በእግር ተጉዘው ወታደራዊ ስልጠና ወስደው በመመለስ ከአምባገነኑ የደርግ ሰራዊ ጋር እልህ አስጨራሽ ትግል በማድረግ ሲዳማን ነጻ ያወጡ የቀድሞ የሲዓን አባላት/ወታደሮች እና ቤተሰቦቻቸው።
*በ1994 የሲዳማን የክልል ጥያቄ አንግበው ሀዋሳ ሎቄ ላይ ሰላማዊ ሰልፈው ወጥተው በፌደራል ፖሊስ ቶክስ ተከፍቶባቸው ለሞቱ እና ለቆሰሉ የሎቄ ሰማዕታት እና ቤተሰቦቻቸው።
*በ11/11/11 ህዝባዊ ተቃውሞ ወቅት በመንግስት ወታደሮች ለተገደሉ እና ለቆሰሉ ሰማዕታት እና ቤተሰቦቻቸው።
*ከአጎራባች ክልል ተፈናቅለው በበሌላ መጠልያ ካምፕ ውስጥ ለ3 ዓመታት ተጠልለው ለሚገኙ 39,000 የሲዳማ ተወላጆች።
*በሎካ አባያ እና በሀዋሳ ሀይቅ ዙርያ የሚገኙ መኖርያ ቤታቸው እንዲሁም የእርሻ መሬታቸው በውሀ መሙላት ለተጥለቀለቀባቸው እና ሌሎች መሰል እርዳታ ለሚሹ ወገኖቻችንም ትኩረት ቢሰጥ እንላለን።
©ማሳንቱ
Comments
Post a Comment