የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ሰዎች በውሃ ሙላት ምክንያት እንዳይጎዱ እና እንዳይፈናቀሉ የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑ ተገለጸ
አቶ ወርቁ ስጋት የሆኑ ቦታዎቾ ተለይተው ነባርና አዲስ የግድብ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።
የግድቡ ስራ የሚሸፍናቸው ከአዲሱ ቤተመንግስት እስከ ፍቅር ሀይቅ፣ ከአሞራ ገደል እስከ ኖሬዥያን መኖሪያ፣ ከአድናቆሬ እስከ ቡሽሎ፣ ዋዮ እና ዳቱ እንደሚገነኙ ገልጸዋል።
እስከ አሁን ለሀይቁ ግድብ ስራ 830 መኪና ሬዳሽ፣ ድንጋይና ሰሌክት ለስራው የዋለ ሲሆን 8 ከባድ ማሽነሪዎችና 20 ሴኖትራክ መኪና በስራ ላይ መሳተፋቸውን ነው አቶ ወርቁ የገለጹት።
የሀይቁ ዳርቻ በተለያዩ ማህበራት የጋቢዮን ስራ እየተከናወነ ሲሆን ህብረተሰቡ ከከተማ አስተዳደሩ ጎን መቆም እንዳለትም አቶ ወርቁ ተናግረዋል።
ከተማ አስተዳደሩ የተጎዱትን የማዳንና በጊዛዊነት የማቋቋም ስራ እያከናወነ መሆኑንም አክለዋል።
ህብረተሰቡ ቅድመ ጥንቃቄ በማድረጉ ረገድም ትኩረት መስጠት እንዳለበት ነው አቶ ወርቁ መልእክት ያስተላለፉት።
ዘንድሮ በአገሪቱ ብሎም በሲዳማ እየጣለ ባለው ከፍተኛ ዝናብ የተነሳ የሐዋሳ ሀይቅ ሞልቶ በመፍሰሱ፤ በአከባቢዋ የሚኖሩ የገጠር እና የከተማ ነዋሪዎችን ላለፉት በርካታ ሳምንታት ከቤት ንብረታቸው ማፈናቀሉ የሚታወቅ ሲሆን፤ በችግሩ ዙሪያ የከተማዋ አስተዳደር ምላሽ ለመስጠት ብዘገይም፣ የግድብ ስራውን ጨምሮ አንዳንድ ማስተካኪያ ስራዎችን በመስራት ላይ መሆኑን ስምተናል።
ReplyDelete