‘‘ሲዳማ“ የሚለውን ስም በአብዘኛዎቹ የአትዮጵያ እና የውጭ አገራት መጣጥፎች ውስጥ የወቅቱን የሲዳማ
ብሔር ብቻ ሳይሆን፤ ሌሎች በርካታ ብሔር እና ብሔረሰቦች መጠሪያ ሆኖ ማየቱ አዲስ ነገር አይደለም። ነገሩን ይበልጥ የሚያወሳስበው
ደግሞ፤ በሲዳማ ላይ የተለያዩ ጽሁፎችን ያቀረቡ ጻሃፍት፤ሲዳማ እያሉ የሚጠሯቸው ህዝቦች አንዱ ከሌላው በባህል እና ቋንቋ የተለያዩ
እና ከቀድሞው የባሌ ክፍለሃገር ጀምሮ እስከ ጅማ ድረስ ስፍረው የነበሩ መሆናቸው ነው።
እኔም ስለ ሲዳማ ታሪክ ባነበብኩ ቁጥር፣ ስለ ሲያሜው የተለያዩ ጥያቄዎችን ማንሳተ
ስላልቀረ፤ ‘‘ሲዳማ“ በሚለው ሲያሜ ላይ ታሪክ አገላብጨ ያገኘሁትን መረጃ ከእናንተ ጋር ለመጋራት ያህል እንደሚከተለው
አቀርበዋለሁ።
በእርግጠኝነት ማረጋገጥ ባይቻልም፤ ‘‘ሲዳማ“ የሚለው ሲያሜ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ታሪክ ጸሃፍት ዘንድ የተጠቀሰው ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ325 እስከ 50 ድረስ አክሱምን በአስተዳደሩት ንጉስ ኢዛና ዘመን ነው። የታሪክ ጸሃፊ የሆኑት፤ ፕላዚኮቪስኪ/ Plazikowksy በአክሱማይት ዘመን ስለነበሩ ኩሽ ዘሮች በጻፋቸው ጽሁፎች ውስጥ እንደገለጹት ከሆነ፤ የአክሱም ንጉስ የሆኑት ኢዛና ከነበሯቸው የስልጣን ስሞች መካከል „King of Siyamo“ የሚለው አንዱ ነው። በርግጥ ይህ “ሲያሞ” የሚለው ሲያሜ “ሲዳማ” ከሚለው ጋር ይገናኝ አይገናኝ ማረጋገጥ ባይቻልም፤ በርካታ ጸሃፍት ግን የዘር ግንዱ ከሃይማቲክ/ “proto-Hamitic” የሆነ እና በሰሜን ምስራቅ አፍሪካ የሰፈረ ህዝብ መጠረያ ነው በማለት ይከራከራሉ።
በርግጥ ሲያሜውን ከብሔር ትርጉም ጋር አያይዞ ለመግለጽ አስቸጋር እና አከራካሪ ቢሆንም፤ የ20ኛው ክፍለ ዘመን ጸሃፍዎች
ግን ሲዳማ የሚለውን ስም፣ ለበርካታ በደቡብ ኢትዮጵያ ለሚገኙ፣ አንዱ ከሌላው በባህል እና ቋንቋ የተለያዩ
ነገር ግን ኩሽ
ቋንቋ ተናጋሪ ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች መጠሪያነት ስጠቀሙ ይስተዋላል።
እነዚሁ በርካታ ጽሃፍት እንደሚስማሙት ከሆነ፤ ሲዳማ የሚለው ሲያሜ በስፋት ከ16ኛው ክፍል ዘመን ጀምሮ በተለይ በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ በጥቅም ላይ የዋለ ሲሆን፤ በኦሮሞ መስፋፋት ጋር ተያይዞ፣ ኦሮሞ ያልሆነ ሌሎች ብሔር፣ብሔረሰባች እና ህዝቦች በጅምላ “ሲዳማ” ተብሎ ይጠሩ ነበር። በዚሁም የተነሳ ኦሞቲክ ቋንቋ ተናጋሪዎችን ሳይጨምር፤ ከገናሌ ወንዝ ሽለቆ አንስቶ እስከ ምእራባዊ የኢሉባቦር ተራራዎች ድረስ ተበታትኖ የሰፈሩ ህዝቦች “ሲዳማ” በሚል ሲያሜ መጠሪያቸው ሆኗል።
ይህ ይባል እንጂ፤ “ሲዳማ” የሚለው ሲያሜ በተለይ የተወሰኑ በቋንቋ እና በባህል ተወራራሽነት ያላቸው እንደ፤ ሃድያ፣ ቀቤና፣ ካምባታ፣ ጣምባሮ፣ አላባ፣ ጌደኦ፣ ቡርጂ የመሳሰሉ ብሄሮች በአንድነት የሚጠሩበት ሲያሜ መሆኑ ሌላው አጨቃጫቂ ጉዳይ ነው።
በታሪክ እንደተጻፈው ከሆነ፤ እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ብሔሮች በአንድ ወቅት ሃድያ ኪንግዴም በሚባለው ግዛት ውስጥ የነበሩ
ናቸው። ነገር ግን የሲዳማን ህዝብ አመጠጥ በተመለከተ Ulrich Braukämper Islamic Principalities in
Southeast Ethiopia Between Thietheenth and Sixteenth centuries በሚለው እና እንደ አውሮፓውያን
ዘመን አቆጣጠር በ1973 ባሳተሙት መጻፍ ውስጥ፤ የአሁኑ ሲዳማ ሁለት የተለያዩ የዘር ግንድ ያላቸው ህዝቦች ጥምረት ውጤት ነው
ብለዋል። አክለውም፤ አንደኛው ከሃረርጌ ታራራዎች ዳዋ ከተባለ ቦታ ተነስቶ በባሌ አድርጎ ወደዚህ የመጣ የኩሽ ቋንቋ ተናጋሪ የሆኑ
የቡሼ ዝሪያ ያለው ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ከጉራ (ጉራጌ አከባቢ ያለ) ተራራማ አከባቢ ሚጆ ከተባለ ቦታ ላይ ተነስተው ወደ አሁኑ
ሲዳማ የመጡ የሴም ቋንቋ ተናጋሪ የነበሩ የማዴያ ዝሪያ ያላቸው ናቸው*።
እንግዲህ እነዚህ ሁለት የተለያዩ የዘር ግንድ ያላቸው ህዝቦች አንድ ሆነው፣ ሲዳማ የሚለውን ስያሜ መውሰዳቸው በዚሁ ጽሁፍ
ውስጥ የተጠቀሰ ሲሆን፤ በሲያሜ አወራረሳቸው ላይ ግን አሁንም ግልጽነት ይጎድለዋል።
በርካታዎች እንደሚያምኑት ከሆነ፤ በ16ኛው ክፍለ ዘመን የነበረው የግራኝ መሃመድ ወረራ እና የኦሮሞ ህዝብ ወደ ደቡብ ምእራብ፣
በመሃል አድርጎ ወደ መካከለኛው ምእራብ የኢትዮጵያ ክፍል ያደረገው መስፋፋት፤ ቀድሞው በአከባቢዎቹ ሰፍረው የነበሩ ህዝቦችን ከአከባቢያቸው
ያፈናቀለ እና ለስዴት የዳረገ ከመሆኑ በላይ፤ ታሪካዊ ዳራቸውን ለማወቅ አስቸጋሪ አድርገዋል። ሲዴ በሚል ይታወቁ የነበሩ እና ከአባያ ሐይቅ ምእራብ መስፈራቸው የሚነገርላቸው እነዚህ ሁለቱ
የሲዳማ ነገዶች፤ በጊዜ ህዴት ”ሲዴ”ን “ሲዳማ” ወደሚለው ስያሜ አሳድገዋል።
በቀጣይነትም፤ በሲዳማ ህዝብ ታሪካዊ አመጠጥ ላይ ከ13ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ በተለያዩ አውሮፓውያን ተጓዦች እና ሚስዮናውያን
በፈረንሳይኛ፣ በጀርመንኛ፣ በፖርቱጊዝ እና በኢጣሊያንኛ የጻፏቸው መጣጥፎችን እየተረጎሞኩ በ www.worancha.com
ላይ የሚያቀርብ
መሆነን ለውድ አንባቢያን መግለጽ እወዳለሁ።
ቸር እንስብት
ኖሞናኖቶ ነኝ
*በዚህ ጉዳይ ላይ ወደፊት ዝርዝር ያለ መረጃ አቀርባለሁ።
Comments
Post a Comment