66 ኪ.ሜ የሚረዝመው የሀዋሳ - ጭኮ አስፋልት ኮንክሪት የመንገድ ግንባታ ተጠናቀቀ
መንገዱ የሞምባሳ - ናይሮቢ - አዲስ አበባ የመንገድ ኮሪደር አካል መሆኑም ታውቋል፡፡
በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ የተገነባው የሀዋሳ - ጭኮ መንገድ በመስመሩ ላይ የሚገኙትን ከተሞች ፣ የእርሻና የኢንዱስትሪ ዞኖች እንዲሁም የቱሪስት መስህብ የሆኑ ስፍራዎችን ዘመናዊ በሆነ መንገድ በማስተሳሰር የጉዞ ጊዜንና ወጪን በመቀነስ ረገድ ፋይዳው የጎላ እንደሆነም ተገልጿል፡፡
እንዲሁም በደቡብ የኢትዮጵያ የሃገሪቱ ክፍል የሚመረቱ የግብርና እና የኢንደስትሪ ምርት ውጤቶችን ወደ አዲስ አበባም ሆነ ወደ ኬንያ ሞንባሳ ወደብ ለማድረስ እና የገቢ ምርቶችን ከወደቡ ወደ ተቀረው ኢትዮጵያ ክፍል ለማዳረስ ፣የቡና ምርት ውጤቶችን በአፋጣኝ ወደ አለም አቀፍ ገበያ ለማድረስ፣ ሚና እንዳለው ተነግሯል፡፡
በተጨማሪም የሁለቱን ጎረቤት ሀገራት ህዝቦችን እርስ በርስ በማስተሳሰር ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን ከማሳደግ ባሻገር ቀጠናዊ ሚናውን ከፍ ያለ ነው ተብሏል።
ግንባታው በቻይናው አለም አቀፍ ተቋራጭ ድርጅት ሲኖ ሀይድሮ ኮርፖሬሽን ሊሚትድ የተከናወነ ሲሆን ከአፍሪካ ልማት ባንክ በተገኘ 1 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ብድር መከናወኑ ታውቋል።
የመንገድ ስራውን ጥራት በመቆጣጠር እና በማማከር የሰራው ደግሞ ኤ አይ ሲ ፕሮጊቲ ኤስ.ፒ.ኤ የተባለ የውጭ አማካሪ ድርጅት ነው ተብሏል።
የዚሁ መንገድ ቀጣይ ክፍል የሆነው ጭኮ - ይርጋጨፌ 60 ኪሎ ሜትር አስፋልት ኮንክሪት ግንባታ ስራ እየተካሄደ እንደሚገኝ ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ላለፉት በርካታ አመታት በኝባታ ስራ ላይ ተኝቶበት የነበረው 66 ኪ.ሜ የሚረዝመው የሀዋሳ - ጭኮ አስፋልት ኮንክሪት የመንገድ ግንባታ መጠናቀቁን ዜና ላይ አይተናል።
ReplyDelete