የዘንድሮ ዓመት የብሔር ብሔረሰቦች በዓል በኮረና ቫይረስ ምክንያት የአከባበር ለውጥ እንደተደረገበት የፌደሬሽን ምክርቤት አስታወቀ
***********************************************************
በዘህም መሰረት ህዳር 15 በትግራይ ፣ ህዳር 16 በደቡብ ፣ ህዳር 17 ሱማሌ ፣ ህዳር 18 ቤኒሻንጉል ህዳር 19 አማራ፣ ህዳር 20 አዲስ አበባ ፣ህዳር 21 ሐረር ፣ ህዳር 22 ጋምቤላ፣ህዳር 23 አፋር ፣ህዳር 24 ኦሮሚያ ፣ህዳር 25 ፣2013 በሲዳማ ይከበራል።
የህዝብ አንድነትና ትብብርን ለመፍጠር ዓለማ አድርጎ በሚከበረው በዚህ በዓል ላይ የተለያዩ ማህበራዊ ተግባራት እንደሚከወኑ ተገልጿል ።
ኢትዮጵያውያን በደም የተሳሰሩ መሆኑን ለማመልከት የአንዱ ክልል ወደ ሌላ ክልል በመሄድ ደም መለገስ ከሚከወኑ ተግባራት አንዱ ነው።
የውይይት መድረኮችና ሲምፖዚየሞችም እንደሚካሄዱ በፌደሬሽን ምክር ቤት የግጭት አፈታት የሰላም ግንበታ ዳይሬክተር አቶ ሙስጠፋ ናስር ገልፀዋል።
Comments
Post a Comment