የ2013 የትምህርት ዘመን የኮቪድ በሸታን በመከላከል የመማር ማስተማር ሂደት ለመቀጠል አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት መደረጉ ተገለፀ
ይህ የተገለፀው የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ 2013 ዓ/ም የትምህርት ሥራ የህዝብ ንቅናቄ መድረክ ባካሄደበት ወቅት ነው።
በመድረኩ የ2012 ዓ/ም የትምህርት ዘመን የኮቪድ በሸታ በመከሠቱ ምክንያት የመማር ማስተማሩ መቋረጡን የተገለፀ ሲሆን ለተማሪዎች በሚያመች መንገድ ትምህርት በመስጠት ከ8ኛ እና 12 ክፍል ውጪ ካሉበት ክፍል ወደ ሚቀጠለው እንዲዛወሩ መደረጉን አቶ መልካሙ ወርቁ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ እና ቤቶችና ኮንስትራክሽን መምሪያ ሀላፊ ገልፀዋል ።
ም/ከንቲባው አክለውም በሸታው አብሮ በመቆየቱ ምክንያት አንደ ሀገር በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት በልዩ ጥንቃቄ ባስገዳጅ ሁኔታ የማር ማስተማሩ ህደት መቀጠል እንደሚገባ አስረድተዋል ።
ይህን በሸታ በመንግሥት ብቻ መከላከል ስለማይቻል ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መሠራት እንደሚገባ አክለዋል።
የ2013 የትምህርት ዘመን እደበፊቱ ቅደመ ዝግጅት ሳይደረግ ሳይሆን ት/ቤቶች በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት መሟላት መዘጋጀት እንደሚገባ የትምህርት መምሪያ ሀላፊ አቶ ደስታ ገልፀዋል።
በመማር ማስተማሩ ወቅት ትምህርት በፈረቃ በመሆኑ መግቢያ እና መውጫ ሰአት የተሻሻለ ሲሆን የተማሪዎች በሳምንት በፈረቃ 3 ቀን በግሩፕ ተከፍለው እንደሚማሩም ነው ሀላፊው ያስረዱት።
በዚህም አንደኛው ግሩፕ ሰኞ፣ ረቡዕ እና አርብ ጥዋትና ከሰዓት በፈረቃ የሚማሩ ሲሆን በተመሳሳይም ሌላኛው ግሩፕ ማክሰኞ፣ ሀሙስና ቅዳሜ ትምህርታቸውን የሚከታተሉ እንደሆነም አቶ ደስታ አስረድተዋል።
የመማሪያ ክፍሎችን በተመከተ የክፍል ስፋታቸው 56 ካሬ የሆነ 25 ተማሪ ብቻ የሚማር ሆኖ በአንድ መቀመጫ አንድ ተማሪ ብቻ በማስቀመጥ ተግባራዊ እንደሚሆንም ገልጸዋል።
ሌላዉ የትቤት ክፍያ በሚመለከት የመንግስት ትምህርት 1-12 ክፍል በነፃ እንዲሆን የተገለፁት ሀላፊው የግል ትምህርት ቤቶች በ2013 የትምህርት ዘመን ምንም አይነት የክፍያ ጭማሬ ሳያደርጉ ተማሪዎችን ተቀብለው ማስተማር እንደሚገባ አመላክተዋል።
ዜናው የከተማ አስተዳደሩ ህዝብ ግንኙነት ነው
Comments
Post a Comment