የሐዋሳ ከተማ በላፉት አምስት አመታት ብቻ በከፍተኛ ደረጃ እድገት ማሳየቷል የሳታላይት ምስሎች አመለከቱ።
ZOOM earth historical satellite image በተባለው ድረገጽ ማየት እንደሚቻለው የሐዋሳ እንደ አውሮፓውያን ዘመን አቆጣጠር ከ2013 ጀምሮ እስከ 2018 ባለው አምስት አመት ጊዜ ውስጥ፤ በተለይ የከተማዋ ገጠራማ እና የእርሻ መሬቶች በመኖሪያ ቤቶች ተሞልተው ታይተዋል።
በዚህ historical
satellite image የተከማቹ ምስሎች ከተማይቱ በግምት ከ20 እስከ 22% ወደ ጎን ማደጓን ያሳያሉ።
በተለይ ወደ ከተማዋ
መግቢያ ዳቶ ኦዳሄ፣ ከሪፈራል ሆስቲታል ጅምሮ እስከ ሎቄ ያለው፣ ከአላሙራ ተራራ ፍትለፊት እንዲሁም ከሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጀርባ ያለው
አከባቢዎች በሚገርም ሁኔታ ወደ ከተማነት በጥቂት አመታት ውስጥ ብቻ ተቀይረው ታይተዋል።
የሐዋሳ ከተማ አድገት
መቼም ለማንም ግልጽ ብሆንም፤ የከተማዋ እድገት በዚሁ ፍጥነት የሚቀጥል ከሆነ በውሃ፣ በመንገድ፣ በሃይል እና በሌሎች መሰረታዊ አቅርቦቶች
ላይ ከፍተኛ ጫና መፍጠሩ አይቀርም።
የከተማዋ አስተዳደር
ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሚመጡትን እና አሁንም አንዳንድ የከተማዋ አከባቢዎች ነዋሪዎቹን በማማረር ላይ ያሉትን የመሰረታዊ አቅርቦት
መጓደልን ለመቅረፍ ከመቼውም ጊዜ በላይ መስራት የሚጠበቅበት ሲሆን፤ የከተማዋን እድገት የማሳደጉ ስራዎች ከተማዋ ወደ ከጎ እንድትሰፋ
ብቻ ሳይሆን ወደ ላይ እንድታድ የሚያደርጋት ቢሆን መልካም ነው።
https://zoom.earth/#view=7.018119,38.484099,16z/layers=esri
Comments
Post a Comment