በሲዳማ ብሐራዊ ክልላዊ መንግስት የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ በዘርፉ የቀጣይ 10 ዓመታት ዕቅድ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ ማካሄድ ጀመረ
Si/Da/Qo/Mootimma Hawaasi Quchumi Gashshooti Fayyimmate Biddishshi Aananno tonnu diri mixo aana la'annonsa bissa ledo amaalete bare harisa hananfi.
Barete afii fa'no hasaawa assinohu kalaa Katami Doobbihu Hawaasi Quchumi Gashshsooti Jireennu paarte borro mini Soreessi jaawa illacha tugatenni keeraanchonna loosaasincho wolqa kalaqatenni assinanni mixora la'annonsa bissa qeechansa jawaantetenni jeefissanno gede xawisino.
በሲዳማ ብሐራዊ ክልላዊ መንግስት የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ በዘርፉ የቀጣይ 10 ዓመታት ዕቅድ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ ማካሄድ ጀመረ።
ለሁለት ቀናት በሚካሄደው በዚህ መድረክ የ2012 በጀት ዓመትን ጨምሮ ያለፉት 5 ዓመታት የዘርፉ ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይትና ግምገማ የተካሄደ ሲሆን በቀጣይ 10 ዓመታት በዘርፉ የሚተገበር ዕቅድ ቀርቦ በባለድርሻ አካላት የሚገመገም ይሆናል።
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት አቶ ከተማ ዶባ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ጽ/ቤት ኃላፊ ለጤናው ዘርፍ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ጤናማና አምራች ዜጋ ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን በቁርጠኝነት ሊወጡ እንደሚገባ ገልፀዋል።
ጥልቀት ያለው ውይይት በማድረግ ባለፈው አፈፃፀም እና በቀጣይ ዕቅድ ዙሪያ የጋራ አቋም ለመያዝ የመድረኩ ሚና የጎላ መሆኑን የገለፁት አቶ ከተማ የጤና አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነትን ለማሳደግ በቅንጅት መስራት ያስፈልጋልም ብለዋል።
አቶ ሙንጣሻ ብርሀኑ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ ኃላፊ እንደከተማ ባለፉት 5 ዓመታት ሀገር አቀፍ የጤና ፕሮግራሞችን ከመተግበር አንፃር ውጤት መመዝገቡን ገልፀው በተወሰኑ ጉዳዮች ላይ ከቦታ ቦታ የአፈፃፀም ልዩነቶች መታየታቸውንም ጨምረው ገልፀዋል።
መከላከልን መሰረት ባደረገው የሀገራችን የጤና ፖሊሲ መሰረት እንደከተማ ሞዴል የጤና አደረጃጀቶችን በመፍጠር,መረጃን ለውሳኔ በመጠቀምና በጤናው ዘርፍ መልካም አስተዳድርን በማስፈን የጤና አገልግሎት ተደራሽነትና ጥራትን ከማሳደግ ረገድ ውጤታማ ስራ መሰራቱንም አቶ ሙንጠሻ ገልፀዋል።
ሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ መጠናቀቁን ተከትሎ የቀጣይ 10 ዓመት ዕቅድ መዘጋጀቱን የገለፁት የመምሪያው ልማት ዕቅድና ኢኮኖሚ ልማት አስተባባሪ አቶ አትክልት ሚካኤል በሁለተኛው የእድገትና ትራንሰፎርሜሽን ዕቅድ ትግበራ ዘመን የታዩ ውስንነቶች በቀጣይ 10 ዓመታት ዕቅድ በልዩ ትኩረት መታየታቸውን ገልፀዋል።
የእናቶችና ህፃናትን ሞት መቀነስ,ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች የሚያሳድሩትን ተፅዕኖ መቀነስ, የጤና ተቋማት ዝግጅትን ማሳደግ, እና የባለሞያ አቅም ማጎልበት በቀጣይ 10 ዓመት ልዩ ትኩረት ከተሰጣቸው አበይት የዘርፉ ጉዳዮች መካከል ተጠቃሽ እንደሆኑም ተመላክቷል።
Comments
Post a Comment