‘‘ ሲዳማ “ የሚለውን ስም በአብዘኛዎቹ የአትዮጵያ እና የውጭ አገራት መጣጥፎች ውስጥ የወቅቱን የሲዳማ ብሔር ብቻ ሳይሆን፤ ሌሎች በርካታ ብሔር እና ብሔረሰቦች መጠሪያ ሆኖ ማየቱ አዲስ ነገር አይደለም። ነገሩን ይበልጥ የሚያወሳስበው ደግሞ፤ በሲዳማ ላይ የተለያዩ ጽሁፎችን ያቀረቡ ጻሃፍት፤ሲዳማ እያሉ የሚጠሯቸው ህዝቦች አንዱ ከሌላው በባህል እና ቋንቋ የተለያዩ እና ከቀድሞው የባሌ ክፍለሃገር ጀምሮ እስከ ጅማ ድረስ ስፍረው የነበሩ መሆናቸው ነው። እኔም ስለ ሲዳማ ታሪክ ባነበብኩ ቁጥር፣ ስለ ሲያሜው የተለያዩ ጥያቄዎችን ማንሳተ ስላልቀረ፤ ‘‘ ሲዳማ “ በሚለው ሲያሜ ላይ ታሪክ አገላብጨ ያገኘሁትን መረጃ ከእናንተ ጋር ለመጋራት ያህል እንደሚከተለው አቀርበዋለሁ። በእርግጠኝነት ማረጋገጥ ባይቻልም፤ ‘‘ሲዳማ“ የሚለው ሲያሜ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ታሪክ ጸሃፍት ዘንድ የተጠቀሰው ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ325 እስከ 50 ድረስ አክሱምን በአስተዳደሩት ንጉስ ኢዛና ዘመን ነው። የታሪክ ጸሃፊ የሆኑት፤ ፕላዚኮቪስኪ/ Plazikowksy በአክሱማይት ዘመን ስለነበሩ ኩሽ ዘሮች በጻፋቸው ጽሁፎች ውስጥ እንደገለጹት ከሆነ፤ የአክሱም ንጉስ የሆኑት ኢዛና ከነበሯቸው የስልጣን ስሞች መካከል „King of Siyamo“ የሚለው አንዱ ነው። በርግጥ ይህ “ሲያሞ” የሚለው ሲያሜ “ሲዳማ” ከሚለው ጋር ይገናኝ አይገናኝ ማረጋገጥ ባይቻልም፤ በርካታ ጸሃፍት ግን የዘር ግንዱ ከሃይማቲክ/ “proto-Hamitic” የሆነ እና በሰሜን ምስራቅ አፍሪካ የሰፈረ ህዝብ መጠረያ ነው በማለት ይከራከራሉ። በርግጥ ሲያሜውን ከብሔር ትርጉም ጋር አያይዞ ለመግለጽ አስቸጋር እና አከራካሪ ቢሆንም፤ የ20ኛው ክፍለ ዘመን ጸሃፍዎች ግን ሲዳማ የሚለውን ስም፣ ለበርካታ በደቡብ ኢት
It's about Sidaama!