የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ከሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጋር በዳያስፖራ ጉዳዮች ላይ በጋራ በሚሰራበት ሁኔታ ላይ ተወያየ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት ከሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ ጋር በዳያስፖራ ጉዳዮች ላይ በጋራ መስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያዩ። በውይይቱ ከተዳሰሱ ርዕሰ ጉዳዮች መካከል የክልሉ ተወላጅ የሆኑ የዳያስፖራ አባላትን በኢንቨስትመንት ስራ ላይ ለማሰማራት በጋራ ስለሚሰራበት ሁኔታ፣ በክልሉ መዋዕለ ንዋያቸውን ላፈሰሱ የዳያስፖራ አባላት የሚሰጠው ድጋፍ ተጠናክሮ ስለሚቀጥልበት መንገድ እንዲሁም በክልሉ በኢንቨስትመንት ዘርፍ የተሰማሩ የዳያስፖራ ኢንቨስተሮች የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች በጋራ መፍታት የሚያስችሉ ስልቶች ይገኙባቸዋል። በተጨማሪም በውይይቱ ወቅት ክልሉ በኤጀንሲው የቀረበውን የዳያስፖራ አደረጃጀት ጥያቄ ተቀብሎ የፈታበት ፍጥነትና አደረጃጀቱን በሰው ሃይል ለማሟላት የሄደበት ርቀት የሚደነቅ መሆኑ የተጠቀሰ ሲሆን፣ ሁለቱም አካላት በዳያስፖራ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት ዝግጁነት እንዳላቸው ገልጸዋል። © Ethiopian Diaspora Agency
It's about Sidaama!