በሲዳማ ክልል የአመራር ቁርጠኝነት ችግር በመኖሩ የተነሳ የኮሮና ስርጭት በከፍተኛ ደረጃ በመሰራጨት ላይ መሆኑ እንዳሳሰበው የክልሉ የብልጽግና ፓርቲ አመራር ተናገሩ
የሲዳማ ክልል የብልጽግና ፓርቲ አመራር የሆኑት ካላ አብርሃም ማርሻሎ በሀዋሳ ከተማ በመካሄድ ላይ ባለው ጉባኤ ላይ እንደተናገሩት፤
የክልሉ አመራሮች የኮሮናን በሽታ ስርጭት ለመከላከት በመውሰድ ላይ ያሉት እርምጃ ከሚጠበቀው በታች በመሆኑ ውጤት እያስገኘ አይደለም።
የሲዳማ ህዝብ ቁጥር ወደ አምስት ሚሊዮን ብቻ ሆኖ ሳለ፤ በክልሉ ያለው የኮሮና በሽታ ስርጭት ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ በክልሉ ውስጥ ከበሽታው ነጻ የሆነ ከተማ እና ወረዳ የትኛው ነው ብባል በእርግጠኝነት መናገር ከማይቻልበት ደረጃ ላይ ተደርሷል ብለዋል።
አክለውም ከደቡብ ክልል አንጻር እንኳን ብወዳደር ወደ 16 ሚሊዮን ህዝብ በሚኖርበት ክልል ውስጥ በኮሮና የተያዘው ቁጥር
30 ሰው ብቻ ሲሆን፤ ወደ አምስት ሚሊዮን ነዋሪ ባለባት የሲዳማ ክልል ውስጥ ግን ወደ 107 መሆኑ ግለሰቦች በበሽታው መያዛቸው፤
የበሽታው ስርጭት ምን ያህል አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሆነ ያሳያል ተብለዋል።
ለአብነትም በሲዳማ ክልል ውስጥ በሽታውን ለመከላከል መደረግ ባለባቸው የጥንቃቀ ጉድለት የተነሳ በርካታ ሰዎች በየቀኑ በኮሮና
ቫይሬስ በመጠቃት ላይ ቢሆኑም፤ ጉዳዪ የሚመለከታቸው የየብልጽግና ፓርቲ አባላት የሚጠበቅባቸውን መስራት ላይ እንዳልሆኑ ታውቋል።
አያይዝውም በቤተሰብ ደረጃ እና በጓደኝነት ደረጃ የሚያውቃቸው ግለሰቦች በበሽታው ተይዘው መገኘታቸውን በምርመራ ያረጋገጠ
ያሉ ብሆንም፤ በርካታዎቹ ግን ያለምርመራ ከበሽታው ጋር እንደሚኖሩ በመገመት እራሳቸውን በየቤቶቻቸው አግለው እንደሚገኙ ተናግረዋል።
እራሳቸውን ያለ ምርመራ አግለው የሚገኙ ግለሰቦች፤ ያሉበት ሁኔታ ምን እንደሚመስል እና ከማን ጋር እንዳሉ ሰለማይታወቅ፤
የበሽታውን ቁጥጥር አስቸጋር እንዳደረገው አመልክተዋል።
የክልሉ መንግስት በተለይ በሀዋሳ ከተማ እና በሌሎች የክልሉ ትላልቅ ከተሞች የቤት ለቤት አሰሳ በማድረግ፤ የቤት ለቤት
የኮሮና ምርመራ ማድረግ ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ እንዳልሆኑ አጽናኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
Comments
Post a Comment