የሀዋሳ ከተማን ጨምሮ በሲዳማ ክልል የተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በነገው እለት የሚከበረውን ዓመታዊ የቅዱስ ገብርኤል በዓል በየቤታቸው አንዲያከብሩ የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አሳሰበ

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር መሳፍንት ሙሉጌታ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በአገራችን በተለይም በሀዋሳ ከተማ በተህዋሲው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመር በመምጣቱ ህብረተሰቡ ንክኪ ሊያስከትል ከሚችል መሰባሰብ ሊቆጠብ ይገባል ብለዋል።
በነገው እለት የሚከበረው ዓመታዊ የቁዱስ ገብርኤል በዓልም የአምነቱ ተከታዮች በየቤታቸው አንዲያከብሩት ከእምነቱ የሃይማኖት አባቶች ጋር ከስምምነት ላይ መደረሱን ኮሚሽነር መሳፍንት ተናግረዋል።
አገሪቱ በኮረና ወረርሽኝ ምክንያት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ ትገኛለች ያሉት ኮሚሽነሩ ህብረተሰቡ የወጣውን አዋጅ በማክበር ራሱን ፣ ቤተሰቡንና ማህበረሰቡን ሊጠብቅ ይገባል ብለዋል ።
©DW
Comments
Post a Comment