በኢትዮጵያ ተጨማሪ 555ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።
ዛሬ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን በቦታ ደረጃ ስንመለከት
ከአዲስ አበባ ከተማ 376፣
ከጋምቤላ ክልል 27፣
ከኦሮሚያ ክልል 37፣
ከትግራይ ክልል 28፣
ድሬደዋ 16፣
ደቡብ ክልል 15፣
ከሐረሪ ክልል 0
ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 23፣
ሲዳማ ክልል 8፣
ከአማራ ክልል 2፣
ከሶማሌ ክልል 8 እና
ከአፋር ክልል 15 ናቸው።
-------------------------------
ባለፉት 24 ሰአታት በተደረገ 8,490 የላቦራቶሪ ምርመራ 555 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ፡፡ዶክተር ሊያ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ባለፉት 24 ሰአታት የ9 ሰዎች ህይወት ማለፉን አስታውቀዋል፡፡
በአጠቃላይ በኢትዮጵያ 372 ሺህ 812 የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 13 ሺህ 812 መድረሱን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። በአጠቃላይ በቫይረሱ ሕይወታቸው ያለፉ ቁጥር 209 ደርሷል። 66 የኮሮና ቫይረስ ታካሚዎች ደግሞ በፅኑ ሕክምና መከታታያ ክፍል ውስጥ ይገኛሉ።
ምንጭ : EBC
Comments
Post a Comment