በሀዋሳ ዋና ዋና መንገዶች ላይ የኬሚካል ርጭት ተካሄደ


በሀዋሳ ከተማ በሚገኙ ዋና ዋና መንገዶች ላይ የፀረ ተዋህስ መድሃኒት ርጭት ተከናውናል።
መጋቢት 22 ቀን 2012 ዓ.ም ከማለዳ 12 ሰዓት ጀምሮ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የበሽታ አምጪ ጸረ ተዋህስያን ኬሚካል ርጭትን በዋና ዋና ጎዳናዎች ላይ አድርጓል፡፡
የርጭት መርሀ ግብሩ እስከ ረፋዱ 4፡00 የቆየ ሲሆን በእነዚህ ሰዓታት ዋና ዋና መንገዶቹ ለማንኛውም ተሸከርካሪ ተዘግቶ ቆይቷል።

በከተማው 36 ኪሎ ሜትር  በሚሽፍኑ  ዋና ዋና መንገዶች ላይ 360 ኪሎ ግራም የጸረ ተህዋስያን ኬሚካል ጥቅም ላይ መዋሉን የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ቡሪሶ ቡላሾ ተናግረዋል።

No comments