ሲዳማ አሁንም አጥር ላይ መንጠልጠሉን ቀጥሏል

ሲዳማ አሁንም አጥር ላይ መንጠላጠሉን ቀጥሏል። ህዝቡ ለክልልነት ድምጹን ብሰጥም ከሲዳማ ዞን አስተዳደር አቅም በላይ በሆኑ ጉዳዮች የተነሳ እየተጓተተ ይገኛል። ከመጓተቱ በላይ የሲዳማ ክልልነትን ጉዳይ ከማንም በላይ በብቃት እና ትጋት በመመራት ያለውን የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር በእንቅልፋሙ የዞኑ አስተዳደር ስር እንዲሆን የሚል ደብዳቤ በደቡብ ክልል ተጽፎ አይተናል። ለማንኛውም  በJustice Post የfacebook ገጽ ላይ ያነበብነውን በዚሁ ጉዳይ ላይ የተጻፌ ጽሁፍ ጀባ ብለናል። 


የደቡብ ክልል ምክር ቤት ለሲዳማ ክልል ስልጣን እንድያስረክብ በስዳማ አመራሮች በኩል ከሰሞኑ ከፍተኛ ጫና ሲደረግ እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን የደቡብ ክልል ምክር ቤት አፈ ጊባኤ ወ/ሮ ሄለን ደበበ ምክር ቤቱ ሳይሰበሰብ የስልጣን ርክክቡን እንደማይፈጽሙ ማሳወቃቸውን ገልጸን ነበር። እንግዲህ የስልጣን ርክክቡ ሂደት የሲዳማ አስተዳደሮች ባሰቡት መልኩ ሊሄድ ባለመቻሉ ምክንያት "ሀዋሳ ከተማን ያቀፈ ዞን" ሆናችኋል የሚል አንድምታ ያለው ህጋዊነት የጎደለው ደብዳቤ በትላንትናው እለት ከደቡብ ክልል በኩል መጻፉን ተመልክተናል።
የሲዳማ ህዝብን የዘመናት እራስን በእራስ የማስተዳደር ጥያቄን የሀዋሳ ከተማ ጥያቄ አድርጎ ለሚያስብ ሰው የትላንቱ ደብዳቤ በእራሱ ሙሉ መስሎ ሊታየው ይችላል። በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የክልል መንግስት ምንነትና ጥቅም ለተረዳ ሰው ግን የትላንቱ የደቡብ ክልል ደብዳቤ የሚያሳየው የሲዳማ አስተዳደር በጀት ከደቡብ ክልል እየተሰፈረለት፥አማርኛን የስራ ቋንቋ አድርጎ፥የክልል ልዩ ሀይል ሳያቋቋም፥ባንድራውን በመሬቱ ሳይተክል እንዲው ዞንም ክልልም ሳይሆን የማንም መቀለጃ እንደሆነ ይቀጥል የሚል መሆኑን ይረዳል።
#ምክር_ለሲዳማ_አስተዳደር የሲዳማ አስተዳደር ከሪፍረንደሙ መካሄድ በኋላ አውቶማቲካሊ የክልል መንግስትነቱን ያገኘ ብሆንም የክልል ምስርታው ጉዳይ ፍጹም ህጋዊ እና በቀጣይነትም የሁለቱን ክልል ግንኙነት በማይጎዳ መልኩ እንዲሆን ለማድረግ ስትሉ ያደረጋችሁት ህጋዊነት እና ትዕግስት የሚደነቅ ቢሆንም ከደቡብ ክልል በኩል በተደጋጋሚ የሚሰሩ ሸሮች እና የቅንነት ጉድለት ምክንያት ሰላማዊው የስልጣን ርክክብ ሊካሄድ አልቻለም። ስለሆነም የሲዳማ ዞን እና የሀዋሳ ከተማን ምክት ቤት አንድ/merge በማድረግ ለክልላዊ መንግስት አወቃቀር መሰረታዊ የሆኑ ጉዳዮችን በፍጥነት በማጠናቀቅ ከዚህ በኋላ እንደ ክልል መንግስት አክት ማድረግ መጀመር ይጠበቅባችኋል። ይህን በማድረጋችሁ ከየትኛውም አካል የሚመጣባችሁ ህጋዊ እና ፒለቲካዊ ጫን ቢኖር እንኳን መላው የሲዳማ ህዝብ ከጎናችሁ ሆኖ እንደሚሰለፍ እናረጋግጥላችኋለን።

No comments