ጠ/ሚ ዐቢይ ከሲዳማ የሀገር ሽማግሌዎች ጋር ተወያዩ


አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሲዳማ የሀገር ሽማግሌዎች ጋር ተወያዩ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ከሰዓት ከሲዳማ የሀገር ሽማግሌዎች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በመወያየታቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል።
የሀገር ሽማግሌዎቹ መንግሥት የሚያካሂደውን የለውጥ ሥራዎች በመደገፍ በጽናት ለመቆም ያላቸው አቋም የሚደነቅ መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገፃቸው አስፍረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሀገር ሽማግሌዎች ምርቃት የበረከት ደጅ መክፈቻ ነው ሲሉም ጠቁመዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚህ ቀደም ከህዝብ ተወካዮችና የሃገር ሽማግሌዎች ጋር ውይይት ማድረጋቸው የሚታወስ ነው።

No comments