Skip to main content

Posts

Showing posts from March, 2020

በሀዋሳ ዋና ዋና መንገዶች ላይ የኬሚካል ርጭት ተካሄደ

በሀዋሳ ከተማ በሚገኙ ዋና ዋና መንገዶች ላይ የፀረ ተዋህስ መድሃኒት ርጭት ተከናውናል። መጋቢት 22 ቀን 2012 ዓ.ም ከማለዳ 12 ሰዓት ጀምሮ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የበሽታ አምጪ ጸረ ተዋህስያን ኬሚካል ርጭትን በዋና ዋና ጎዳናዎች ላይ አድርጓል፡፡ የርጭት መርሀ ግብሩ እስከ ረፋዱ 4፡00 የቆየ ሲሆን በእነዚህ ሰዓታት ዋና ዋና መንገዶቹ ለማንኛውም ተሸከርካሪ ተዘግቶ ቆይቷል። በከተማው 36 ኪሎ ሜትር  በሚሽፍኑ  ዋና ዋና መንገዶች ላይ 360 ኪሎ ግራም የጸረ ተህዋስያን ኬሚካል ጥቅም ላይ መዋሉን  የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ቡሪሶ ቡላሾ   ተናግረዋል።

የኮሮና ቫይረስን የመከላከል አቅም የሚጨምር መድኃኒት በኢትዮጵያ ማግኘት እንደተቻለ ተገለጸ

እ.ኤ.አ. በጃንዋሪ 2020 በቻይና ሁቤይ ግዛት ውሃን ከተማ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19) ከተገኘበት ጊዜ አንስቶ ዓለም ቫይረሱን ለመከላከያ፣ ለማከሚያና ለማዳኛ የሚሆኑ መድኃኒቶችን ለማግኘት እየተረባረበ ባለበት ወቅት፣ የጤና ሚኒስቴርና የኤኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በመቀናጀት ከባህላዊ መድኃኒት የተቀመመና የኮሮና ቫይረስን የመከላከል አቅም የሚጨምር ማከሚያ መድኃኒት ማግኘታቸውን አስታወቁ፡፡ ቫይረሱ በዓለም መስፋፋቱ ከተነገረበት ጊዜ አንስቶ ምርምር ሲደረግበት እንደቆየ፣ የባህል ሕክምና ባለሙያዎች በአገር ውስጥና በውጭ አገር ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተመራማሪዎች ጋር በመጣመር አበረታች ውጤት የታየበት መድኃኒት መገኘቱ ተገልጿል፡፡ ‹‹ቫይረሱን ለማከም የተሠራው መድኃኒት መሠረታዊ የምርምር ሒደት በማለፍ ተደጋጋሚ የቤተ ሙከራ ሞዴሊንግ ሒደቶችን በስኬት አልፏል፤›› በማለትም ተገልጿል፡፡ ‹‹ምርምሩ የኮሮና ቫይረስ በዓለም ላይ መከሰቱ ከተሰማ ጊዜ ጀምሮ ከተለያዩ በአገር ውስጥና በውጭ ከሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን ሲካሄድ የቆየ ሲሆን፣ ተደጋጋሚ የምርምር ሒደት አልፎ ወደ ምርትና ቀጣይ የእንስሳት ፍተሻና ክሊኒካል ፍተሻ ሥራዎች እንዲሸጋገር ተደርጓል፤›› ሲል የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያወጣው መግለጫ ያትታል፡፡ ክሊኒካል ፍተሻ በሰዎች ላይ የሚደረግ እንደሆነ የአሜሪካ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን ያስረዳል፡፡ በኢትዮጵያ ተገኘ የተባለው መድኃኒት የመከላከል አቅምን የሚጨምር፣ መርዛማነት የሌለውና አዋጭነቱ የተረጋገጠ ነው ሲልም መግለጫው አክሏል፡፡ በአሜሪካ የመድኃኒትና የምግብ ባለሥልጣን መመርያ መሠረት አንድ መድኃኒት ከምርምር አንስቶ እስከ ጥቅም ላይ መዋል ሊከተላቸው የሚገቡ አምስት ደረጃዎችን ማለፍ እንዳለበት ይጠቁማል፡፡ የመጀ

ኢትዮጵያ ለኢኮኖሚ ማነቃቂያና ለሸቀጦች ግዥ 20 ቢሊዮን ብር መድባለች

ዳዊት ታዬ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በፍጥነት የመዛመቱና ከግማሽ ሚሊዮን በላይ በዓለም የሚገኙ ሰዎችን በማዳረስ በሺዎች የሚቆጠሩትን ለሞት አብቅቷል፡፡ አሁንም በመዛመት ላይ ይገኛል፡፡ የወረርሽኙ አስፈሪ ሥርጭት ግን የሰዎችን ሕይወት ከመቅጠፍ አልፎ ኢኮኖሚያዊ ጥቃቱም ከሚገመተው በላይ እየሆነ መጥቷል፡፡ አብዛኞቹን የበለፀጉ አገሮችን እያመሰ የሚገኘው ኮሮና፣ ወደ አፍሪካና ሌሎች ድሆች ሕዝቦች የሚያደርገው ጉዞ እያየለ ሲመጣ ሊያደርስ የሚችለው ሰብዓዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳት በቀላሉ የሚገለጽ አይደለም፡፡ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ዓለም አቀፋዊ ትስስር ያላቸው በመሆናቸው የዓለም የኢኮኖሚ ሥርዓት እየተመታና እየታመሰ በሚገኝበት በዚህ ወቅት፣ በርካታ አገሮችን አስቸኳይ የኢኮኖሚ ማነቃቂያ፣ የንግድ ዘርፍ ድጋፍ እንዲሁም ሌሎች የማገገሚያ ዕርምጃዎች ከወዲሁ እየተዘረጉ ነው፡፡ አሜሪካ የቫይረሱን ወረርሽኝ ለመከላከልና ኢኮኖሚዋን ለመታደግ የ2.2 ትሪሊዮን ዶላር የአደጋ ጊዜ በጀት አፅድቃለች፡፡ ሌሎችም በርካታ አገሮች ተመሳሳይ ዕርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ይገኛሉ፡፡ ኢትዮጵያም ከጥቂት ሳምንታት በፊት በጊዜያዊነት 300 ሚሊዮን ብር መድባ ነበር፡፡ ይህ ለበሽታው መከላከያነት የተመደበው ገንዘብ ብዙም ሳይቆይ ወደ 500 ሚሊዮን ብር እንዲያድግ ቢወሰንም፣ የበሽታው አያያዝና ወደ ኢትዮጵያ ያቀናው ዱካው ቀስ በቀስ እየጠነከረ በመምጣቱ ሳቢያ፣ ኢኮኖሚውም ከወዲሁ አጣብቂኝ ውስጥ የመግባቱ ጉዳይ የማያጠያይቅ ሆኖ በመገኘቱ በድጋሚ አምስት ቢሊዮን ብር በጀት እንዲመደብ ተደርጎ ነበር፡፡ ወረርሽኙ የአገሪቱን ኢኮኖሚ እየደቆሰ መሆኑ ከየዘርፉ ከተገኙ መረጃዎች የተገነዘው መንግሥት፣ በባንኮች በኩል ለግሉ ዘርፍ ድጋፍ የሚውል ከፍተኛ ገንዘብ ለመመደብ ተገዷል፡፡ ዓርብ፣ መጋ

Coordinated response can protect African garments industry from coronavirus fallout

Workers sew clothes inside the Indochine Apparel PLC textile factory in Hawassa Industrial Park in Southern Nations, Nationalities and Peoples region, Ethiopia REUTERS/Tiksa Negeri - Exports of African textiles and garments have grown rapidly over the past decade, but US and European orders for African garments have dried up as a result of the coronavirus pandemic. As we have argued in a   recent paper , there are three main options to protect African workers who face the prospect of extreme hardship. These are: to subsidise wages for workers,  a subsidised training package to retain manufacturing capabilities  a retooling of garment factories to produce garments for medical needs Each option requires different commitments from buyers, factories, workers, the public sector and donors. In Kenyan, each garment firm on average needs $400,000 per month to pay workers. This could be financed through a  combination of commitments from buyers, factories, workers, the pub

Many of Africa’s economies are doing well

But there are questions about the best road to long-term growth P assing through  the gate leading into the Hawassa industrial park feels a bit like crossing a boundary between Africa’s past and a vision of its future. On one side three-wheeled tuk-tuks beep their horns as they swerve around pot holes on the main road running through this southern Ethiopian town. On the other side smooth asphalt forms geometric grids around the rows of new factory buildings that represent one of Africa’s boldest attempts to industrialise by following in the footsteps of Asia. The park opened three years ago, yet it already employs almost 30,000 people and has plans to double. Most of the young women working in it make clothing for companies such as  pvh , which owns brands including Tommy Hilfiger and Calvin Klein. Selamawit Malkato, 20, had never seen a factory until she came to Hawassa. But last year she stood with scores of other hopefuls outside the park’s gates. Her sister already had a jo

ሲዳማ አሁንም አጥር ላይ መንጠልጠሉን ቀጥሏል

ሲዳማ አሁንም አጥር ላይ መንጠላጠሉን ቀጥሏል። ህዝቡ ለክልልነት ድምጹን ብሰጥም ከሲዳማ ዞን አስተዳደር አቅም በላይ በሆኑ ጉዳዮች የተነሳ እየተጓተተ ይገኛል። ከመጓተቱ በላይ የሲዳማ ክልልነትን ጉዳይ ከማንም በላይ በብቃት እና ትጋት በመመራት ያለውን የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር በእንቅልፋሙ የዞኑ አስተዳደር ስር እንዲሆን የሚል ደብዳቤ በደቡብ ክልል ተጽፎ አይተናል። ለማንኛውም  በ Justice Post  የfacebook ገጽ ላይ ያነበብነውን በዚሁ ጉዳይ ላይ የተጻፌ ጽሁፍ ጀባ ብለናል።  # ሀዋሳ_ከተማን_ያቀፈ_ዞን_ሆናችኋል_ተብለናል !! የደቡብ ክልል ምክር ቤት ለሲዳማ ክልል ስልጣን እንድያስረክብ በስዳማ አመራሮች በኩል ከሰሞኑ ከፍተኛ ጫና ሲደረግ እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን የደቡብ ክልል ምክር ቤት አፈ ጊባኤ ወ/ሮ ሄለን ደበበ ምክር ቤቱ ሳይሰበሰብ የስልጣን ርክክቡን እንደማይፈጽሙ ማሳወቃቸውን ገልጸን ነበር። እንግዲህ የስልጣን ርክክቡ ሂደት የሲዳማ አስተዳደሮች ባሰቡት መልኩ ሊሄድ ባለመቻሉ ምክንያት "ሀዋሳ ከተማን ያቀፈ ዞን" ሆናችኋል የሚል አንድምታ ያለው ህጋዊነት የጎደለው ደብዳቤ በትላንትናው እለት ከደቡብ ክልል በኩል መጻፉን ተመልክተናል። የሲዳማ ህዝብን የዘመናት እራስን በእራስ የማስተዳደር ጥያቄን የሀዋሳ ከተማ ጥያቄ አድርጎ ለሚያስብ ሰው የትላንቱ ደብዳቤ በእራሱ ሙሉ መስሎ ሊታየው ይችላል። በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ  የክልል መንግስት ምንነትና ጥቅም ለተረዳ ሰው ግን የትላንቱ የደቡብ ክልል ደብዳቤ የሚያሳየው የሲዳማ አስተዳደር በጀት ከደቡብ ክልል እየተሰፈረለት፥አማርኛን የስራ ቋንቋ አድርጎ፥የክልል ልዩ ሀይል ሳያቋቋም፥ባንድራውን በመሬቱ ሳይተክል እንዲው ዞንም ክልልም ሳይሆን የማንም መቀለጃ እንደሆነ ይቀጥ

ያለፍትህ በእስር ላይ የሚገኙ ኤጄቶዎችን በተመለከተ ከቤተሰቦቻቸው የቀረበ አቤቶታ

The JESUS Movie in Sidaamu Afoo

የሃዋሳ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አገልግሎት አሰጣጡን ዲጂታላይዜሽን እያደረገ መሆኑን አስታወቀ፡፡ |etv

የሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሥራ እንቅስቃሴ

የኢትዮጵያ መንግስት ግዙፍ መዕዋለ ንዋይ በመመደብ በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የኢንዱስትሪ ፓርኮች ግንባታ አከናውኗል። ከሶስት ዓመታት በፊት ተገንብተው ወደ ምርት ተግባር ከተሸጋገሩት መካከል የሀዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ በቀዳሚነት ይጠቀሳል ። የዛሬው ከኢኮኖሚው አለም ዝግጅታችንም በዚሁ ኢንዱስትሪያል ፓርክ የስራ እንቅስቃሴ ላይ ያተኩራል። ወጣት ወይኒቱ ቦካንሳ ነዋሪነቷ በሲዳማ ዞን ዳራ ወረዳ ነው። ወይኒቱ እንደ አብዛኞቹ የኢትዮጵያ የገጠር ሴቶች የስራ ጫና ሳይበግራት በትምህርቷ የተወሰነ ደረጃ ለመግፋት ጥረት ማድረጓን ትናገራለች ። ይሁን እንጂ በአስረኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ወደ መሰናዶ ትምህርት ለማለፍ የሚበቃትን ውጤት ለማግኘት እንዳልቻለች የምታስታውሰው ወይኒቱ በዚህም የተነሳ ለዓመታት በቤት ከመዋል ውጪ አማራጭ አልነበረኝም ትላለች ። በኃላ ላይ ግን በሀዋሳ ከተማ የተከፈተው የአንዱስትሪ ፓርክ ለሰራተኝነት ከመለመላቸው ሴቶች መካከል አንዷ ሆና መቀላቀሏን የምትናገረው ወይኒቱ ይህ አጋጣሚ ቤተሰቤን እንድረዳ ፣ ትምህርቴንም እንድቀጥል ምክንያት ሆኖኛል ትላለች ። በአገሪቱ በቀዳሚነት ከተገነቡት ፓርኮች አንዱ የሆነው የሀዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ የምርት አገልግሎቱን የጀመረው ከዛሬ ሶስት ዓመት በፊት ነበር። ፓርኩ በእነኝሁ ዓመታት በዜጎች የስራ እድል ፈጠራና በምርት አቅርቦት ረገደ አከናውኗል ያሏቸውን ስራዎች  የፓርኩ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ፍጹም ከተማ ይገልጻል ። በአሁኑ ወቅት በሀዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ የማምረቻ ቬድ ወስደው በስራ ላይ የሚገኙት ኩባንያዎች በአብዛኛው በጨርቃ ጨርቅ ምርቶች ላይ የተሰማሩ ናቸው። ከእነኝሁ ኩባንያዎች መካከል የካንቤቢ ዳይፐር አምራቹ ኦን ቴክስ ኩባንያ፣ የአሜሪካው ፒቪ ኤች እና የህንዱ ሬይ መንድ ይ

የቀድሞ የሲዳማ አርነት ንቅናቄ ታጋይ ካላ ሳሙኤል ሂሎ ሲምባሶ፤ ለሲዳማ ህዝብ አርነት ስታገሉ የተሰው ሰማእታት እና የትጥቅ አጋሮቻቸውን በዚህ መልኩ ያስታውሷቸዋል

ከESAT የሲዳማ አፎ ልዩ ፕሮግራም ላይ ተቀንጭቦ የተወሰደ ስለ ሲዳማ የትጥቅ ትግል የሚያወሳ ቃለ መጠይቅ የቀድሞ የሲዳማ አርነት ንቅናቄ ታጋይ ካላ ሳሙኤል ሂሎ ሲምባሶ፤ ለሲዳማ ህዝብ አርነት ስታገሉ ስለተሰው ሰማእታት እና ስለትጥቅ አጋሮቻቸው የአይን እማኝ ምስክርነታቸውን በዚህ መልኩ ስጥተዋል። አዲሱ የሲዳማ ትውልድ ከቀድሞ ታጋዮች በመማር በአንድነት የህዝቡን የዘመናት የፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጥያቄዎችን ምላሽ እንዲያገኙ ቀን ከሌሊት ልሰራ ይገባል። የሲዳማ የመብት ጥያቄ ብዙ ደም የፈሰሰበት እና አያሌዎች የተሰውበት ነው። የስልጣን ርክብክቡ ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም።

ሲዳማ የስልጣን ርክብክቡን በተመለከተ አንድ አርምጃ መራመድ ባለመቻሉ በዘንድሮው ብሄራዊ ምርጫ በክልልነት የምርጫ ካርታ ልያገኝ አልቻለም።

2ኛው ሀገር አቀፍ የሆቴልና ቱሪዝም ኮንፈረንስ በሀዋሳ ከተማ ይካሄዳል

2ኛው ሀገር አቀፍ የሆቴልና ቱሪዝም ኮንፈረንስ በሀዋሳ ከተማ ይካሄዳል አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 2፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) 2ኛው ሀገር አቀፍ የሆቴልና ቱሪዝም ኮንፈረንስ የፊታችን መጋቢት 7 ቀን 2012 ዓ.ም በሀዋሳ ከተማ እንደሚካሄድ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ። በኮንፈረንሱ የሀገር መሪዎች፣ ሚኒስትሮች፣ የዘርፉ መሪዎችና ባለሙያዎች፣ የሆቴል ባለቤቶች፣ አስጎብኝዎች፣ የምስራቅ አፍሪካ የዘርፉ መሪዎችና ባለሃብቶች፣ አምባሳደሮች፣ አማካሪ ድርጅቶች እና ሌሎችም ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል። በፕሮግራሙ ከሚደረጉ ኮንፈረንሶች በተጨማሪ ልዩ ልዩ ዝግጅቶች እንደሚካሄዱ ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላከታል። በዚህ መሰረት የእግር ጉዞ፣ ጉብኝቶች፣ የምርትና ኢንቨስትመንት ትውውቅ ፕሮግራሞች፣ የእውቅና ስነ ስርዓቶችን ጨምሮ ሌሎች ዝግጅቶች ይካሄዳሉ። ኮንፈረንሱን የኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደርና ከኢትዮጵያ ሆቴል አሰሪዎች ፌደሬሽን ጋር በጋራ ያዘጋጁት ነው። ኮንፈረንሱ የሀገር ውስጥ እና የሀዋሳ ከተማን የቱሪዝም እንቅስቃሴ ከማነቃቃት ባለፈ ሰላምና የዘርፉን ኢንቨስትመንት ለማጠናከር ያለመ መሆኑ ተመላክቷል።

ጠ/ሚ ዐቢይ ከሲዳማ የሀገር ሽማግሌዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሲዳማ የሀገር ሽማግሌዎች ጋር ተወያዩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ከሰዓት ከሲዳማ የሀገር ሽማግሌዎች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በመወያየታቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል። የሀገር ሽማግሌዎቹ መንግሥት የሚያካሂደውን የለውጥ ሥራዎች በመደገፍ በጽናት ለመቆም ያላቸው አቋም የሚደነቅ መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገፃቸው አስፍረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሀገር ሽማግሌዎች ምርቃት የበረከት ደጅ መክፈቻ ነው ሲሉም ጠቁመዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚህ ቀደም ከህዝብ ተወካዮችና የሃገር ሽማግሌዎች ጋር ውይይት ማድረጋቸው የሚታወስ ነው።

የሲዳማ ህዝብ ከ ደ/ር አብይ አህመድ ጋር ያረገው ውይይት 12 10 2010 ዓ/ ም ካደረጉት ወይይት ላይ የተወሰደ

Ethiopian water bottling company ventures into the UK market

ETHIOPIA – Garanba Bottling, a subsidiary of B&C Aluminum Plc that bottles South Spring Water in Ethiopia, has closed a deal with a UK-based company to export US$1m worth of bottled water to England. Garanba Bottling was established with an investment of 410 million Br (US$12.5m) in Aregobena Wereda of Sidama Zone. It operates with 310 employees and has the capacity to produce 16,000 bottles of water an hour. The Bottling company signed the deal with the British company on January 1, 2020 and they will ship 1,200tn of bottled water as a trial this March. The first shipment will take five 20-foot equivalent units, which will constitute one million bottles. South Spring Water will mainly be delivered in 0.6lt and 1.2lt bottles. Before inking the deal, the two parties completed the testing and sampling process, which took close to three months. “Following the first round, we’ll seal a long-term agreement to ship 50 containers a month,” said Berhanu Getahun, board chairperson of

ዛሬ የሲዳማን ህዝብ ድምጽ ያፈነው የፌዴራል መንግስት፤ ነገ የአንተን የምርጫ ድምጽ ላለማፈኑ ምንም ማረጋገጫ የለም

ለሲዳማ እና ለሲዳማውያን የወቅቱ አንገብጋብ አጄንዳ የስልጣን ርክብክብ ነው። እንደሚታወቀው የስልጣን ርክብክቡ ከሲዳማ አመራሮች እና የደቡብ ክልል ባለስልጣናት አቅም በላይ ሆኗል። ሰሞኑን እንደሰማነው ከሆነው፤ ደቡብ ተብዬውን ክልል ለአራት ለመክፈል ህዝቡን ለማሳመን የቀድሞ የደኢህዴን ካድሬዎች፤ ብሎም ያሁኑ የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ቀን ከሌሊት በመስራት ላይ ናቸው። በዚሁ ፕሮግራም ውስጥ ሲዳማም እንደ አዲስ ክልል ሳይሆን በቀድሞ ደረጃው ከጌዴኦ ዞን ጋር አንድ በሚሆንበት ሁኔታ ላይ ህዝብን ለማወያየት እቅድ ተይዞአል። እቅዱ ተግባራዊ መሆን አለመሆኑ በሲዳማ ህዝብ ምላሽ እና አሁን በስልጠና ላይ ባሉት የሲዳማ ተወካዮች ይሁንታ ይወሰናል የሚል እምነት አለኝ። የአገሪቱ መንግስት ለህገ መንግስቱ ያለው ንቀት፤ እንደህዝብ የሲዳማን ጥያቄ በዴሞክራሲያዊ መንገድ ለመመለስ የወጣውን ከፍተኛ የአገር ሀብት ማለትም፤ ከፍተኛ ገንዘብ እና ጊዜ የፈሰሰባቸውን ዴሞክራሲያዊ ተግባራትን በምሳሌነት መውሰድ እና በተቀሩት ዴሞክራሲያዊ እርከኖች ተግባራዊ ማድረግ ሲገባ፤ በተቃራኒው በመስራት ላይ ይገኛል። የኢትዮጵያ ህዝብ በሚቀጥለው አገር አቀፍ ምርጫ ላይ ምንም አይነት ዴሞክራሲያዊ መንገድ ተከትሎ መብቱን በድምጹ ብያረጋግጥ እንኳን መብቱ ልከበርለት እንደማይችል የሲዳማ ክልል ህዝበ ወሳኔ አንድ ማሳያ እየሆነ ነው። የሲዳማን ህዝብ የክልል አስተዳደር ምስረታን ለማኮላሽት ማእከላዊ መንግስት ያልፈነቀለው ድንጓይ የለም። አሁን አሁንማ በሃይማኖት አማካኝነት ለሲዳማ ህዝብ መብት እና አርነት የሚታገሉትን ታጋዮች፤ በሀይማኖት ሰበብ መንቀሳቀሻ በማሳጣት እና በሚቆጣጠራቸው እና በሚታዘዙት ፌክ ፓስተሮች አማካይነት ከፍተኛ ክትትል እንዲደረግባቸው በማድ